Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትቀነኒሳና ጥሩነሽ በለንደን ማራቶን ይጠበቃሉ

ቀነኒሳና ጥሩነሽ በለንደን ማራቶን ይጠበቃሉ

ቀን:

የኢትዮጵያ የረዥም ርቀት ፈርጦች አትሌት ቀነኒሳ በቀለና አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በለንደን ማራቶን ውድድር ለድል ይጠበቃሉ፡፡ እሑድ ሚያዝያ 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ለ38ኛ ጊዜ በሚካሄደው የለንደን ማራቶን፣ በወንዶቹ ሞ ፋራ፣ ዳንኤል ዋንጂሩ፣ ኤሉድ ኪቾጊ፣ ቀነኒሳ በቀለና ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ጉዬ አዶላ የሚያደርጉት ፉክክር ትልቅ ግምት ተሰጥቶታል፡፡

በሴቶቹም አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ፣ ኬኒያዊቷ ቪቪያን ቺሮይት፣ ማሬ ዲባባ ከወዲሁ የአሸናፊነት ግምት ተሰጥቷቸዋል፡፡ በቅርቡ ወደ ጎዳና ሩጫ ፊቱን ያዞረው ኢንግሊዛዊው ሞ ፋራ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ሞ ፋራ ለመጀመርያ ጊዜ እ.ኤ.አ. በ2014 በለንደን ማራቶን መሳተፍ ቢችልም ስምንተኛ በመውጣት ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

አትሌቱ ለኬንያውያንና ለኢትዮጵውያን አትሌቶች ፈታኝ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2004 ወደ ማራቶን ፊቱን ያዞረው ቀነኒሳ፣ በበርሊን ማራቶን ያጠናቀቀበት የ2፡03፡03 ሠዓት የምንጊዜም የግል ሰዓቱ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በቅርቡም በለንደን በተከናወነ ማራቶን፣ ርቀቱን በ2፡05፡57 በማጠናቀቅ ዘጠኝ ሴኮንድ ብቻ በመዘግየት ሁለተኛ ሆኖ መጨረሱ አይዘነጋም፡፡

በሴቶቹም በኩል ኢትዮጵያዊቷ ጥሩነሽ ዲባባ ከፍተኛ ፉክክር እንደሚጠብቃት ይገመታል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2014 በለንደን ወደ ማራቶን ሩጫ የገባችው ጥሩነሽ፣ በ2፡20፡35 ሠዓት በመግባት ሦስተኛ ሆና ውድድሩን አጠናቃለች፡ እ.ኤ.አ. በ2017 በተደረገው የለንደን ውድድርም የግሏን ሦስተኛ ትልቅ ሰዓት ማምጣቷ ይታወሳል፡፡ በቺካጎ ማራቶንም በ2፡18፡30 ሠዓት በመግባት የወርቅ ሜዳልያ አጥልቃለች፡፡ በዘንድሮው የለንደን ማራቶንም ከኬንያዊቷ ሺቪያን ቺሮይት እንዲሁም ከአገሯ ልጅ ማሬ ዲባባ ከፍተኛ ፉክክር እንደሚጠብቃት ይገመታል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...