በድንገተኛ አደጋ ሕይወቱ ያለፈው የድምፃዊ ታምራት ደስታ የቀብር ሥነ ሥርዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ሚያዝያ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ተፈጽሟል፡፡
ድምፃዊው ሚያዝያ 10 ቀን 2010 ዓ.ም. የገጠመውን ሕመም ለመታከም ወደ ሕክምና ተቋም ሄዶ በዚያው በድንገት ሕይወቱ አልፏል፡፡ በድምፃዊ ታምራት የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ጨምሮ በርካታ ድምፃውያንና ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተዋል፡፡
ከድምፃዊ ታምራት የሙዚቃ ሥራዎች መካከል ሐኪሜ ነሽና አንለያይም የሚጠቀሱ ሲሆን፣ ሌሎች በርካታ የሙዚቃ ሥራዎችንም ለአድማጮች አድርሷል፡፡ ድምፃዊው ባለትዳርና የአምስት ልጆች አባት ነበር፡፡