Thursday, April 18, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ብቸኛው የወረቀት ፋብሪካ በኪሳራ ውስጥ እየተንከባለለ መሆኑን ይፋ አደረገ

ተዛማጅ ፅሁፎች

  • አገሪቱ በዓመት ስድስት ቢሊዮን ብር ገደማ የወረቀት ግዥ ትፈጽማለች

በአገሪቱ ብቸኛ የወረቀትና ፐልፕ ማምረቻ የሆነው ኢትዮጵያ ፐልፕና ወረቀት ማምረቻ አክሲዮን ማኅበር፣ በአገር ውስጥ ከፍተኛ የወረቀት ገበያ ቢኖርም ከዓመት ዓመት በኪሳራ ውስጥ በመንከባለል ላይ መሆኑ ታወቀ።

የመንግሥት የልማት ድርጅት የሆነው ይህ ተቋም 2010 ዓ.ም. የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸሙን፣ ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ነው ከኪሳራ መውጣት አለመቻሉን ያስታወቀው።

ተቋሙ በወረቀት ማምረት ማደራጀትና የካርቶን ማምረት ሥራ ላይ የተሰማራና ከተቋቋመ ረጅምመታትን ያስቆጠረ የልማት ድርጅት ነው። ባለፉት ዘጠኝ ወራት አጠቃላይ ምርቱ 40.6 በመቶ ብቻ ሲሆን፣ የሽያጭ ዕቅዱንም  38.95 በመቶ ብቻ ነው መፈጸም የቻለው። በዚህም ምክንያት 3.8 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ውስጥ መግባቱን የተቋሙ አመራሮች ገልጸዋል።

ኪሳራው እንደ ቀጠለ ቢሆንም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የኪሳራ መጠኑ መቀነሱን አመራሮቹ ጠቁመዋል፡፡

ለድርጅቱ አፈጻጸም ዝቅተኛነትም የጥሬ ዕቃ፣ የኬሚካል፣ የመለዋወጫ ዕቃዎች፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረት፣ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ፣ እንዲሁም የሠለጠነ የሰው ኃይል ፍልሰት ዋነኛ ምክንያቶች እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

በእነዚህ ችግሮች የተነሳ የድርጅቱ የማምረት ሒደት በተደጋጋሚ ጊዜ የሚቋረጥ መሆኑን፣ የማምረትደቱ በተቋረጠ ቁጥር የኪሳራ መጠኑም በሰዓታትናቀናት ልዩነት እየጨመረ እንደሚሄድ ተጠቁሟል።

ድርጅቱ በኢትዮጵያ ብቸኛ የወረቀትና ፐልፕ ማምረቻ ቢሆንም ይህንን ችግር ለመቅረፍ ከመንግሥት በኩል የተደረገው ድጋፍ በጣም አናሳ መሆኑ፣ ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም እያሳጣ እንደሆነም ኃላፊዎቹ አክለዋል፡፡

የአገር ውስጥ የወረቀት ፍላጎት ወደ 24 በመቶ ማደጉን የሚናገሩት ኃላፊዎቹ፣ የኢትዮጵያ የወረቀትና ፐልፕ አክሲዮን ማኅበር ከአጠቃላይ የገበያው ፍላጎት የያዘው ድርሻ አራት በመቶ ብቻ መሆኑን ተናግረዋል።

ተቋሙ የአገር ውስጥ የወረቀት ምርት ፍላጎትን ሙሉ በሙሉ እንኳን ባይሆን በከፍተኛ መጠን የመመለስ አቅም እያለውና ይህንንም ማድረግ እየተቻለ በኪሳራ ውስጥ ሲንከባለል፣ የገበያውን ፍላጎት ለመመለስ ሲባል ደግሞ አገሪቱ በየዓመቱ ስድስት ቢሊዮን ብር ገዳማ በማውጣት የውጭ ግዥ እንደምትፈጽም ታውቋል። ወረቀትን በዋነኝነት የሚጠቀሙት ደግሞ የመንግሥት የአገልግሎት ተቋማት መሆናቸውን በመግለጽ ተቃርኖውን ኃላፊዎቹ አሳይተዋል።

ቋሚ ኮሚቴው በአገር ውስጥ ማምረት እየተቻለ ትኩረት አለመሰጠቱንና ተቋሙም የውስጥ ችግር እንዳለበት ተችቷል። ቀደም ብሎ ከተነሳው ኪሳራና የውጭ ግዥ በተጨማሪ፣ በአገር ውስጥ መታተም የሚችሉ የኅትመት ሥራዎችም በውጭ አገሮች እንዲታተሙ በማድረግ አገሪቱን ለተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ እየዳረገ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ በተፈጠረው ነፃ ገበያ ተጠቅሞ ተወዳዳሪ በመሆን አሁን ከሚገኝበት ኪሳራ ለመውጣትና በኢኮኖሚው የመንግሥትን አቅም ለመደገፍ የሰውይል ብቃት ከማሳደግ፣ ከማቆየት፣ ከማብቃት፣ አማራጭ የኃይል ምንጭና ግብዓትን ከመጠቀም አንፃር ክፍተት እንዳለበትም አመልክቷል።

ከሌሎች ማምረቻ ድርጅቶችና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ግንኙነት ማሳደግ፣ ከተለያዩ ፋብሪካዎች የሚገኙ ተረፈ ምርቶችን በመጠቀም በስፋትና በተደራጀ መንገድ ጥናት በማድረግ ለቀጣይ በማቀድ መሥራት እንደሚጠበቅበት፣ የውስጥ ችግሮቹንም በመፍታት ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ በማሳደግ አገሪቱን ተጠቃሚ ማደረግ እንዳለበት አስተያየት ሰጥቷል።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች