Tuesday, February 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከ2.8 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች በብሔራዊና በክልል ፈተናዎች ላይ ይቀመጣሉ

ከ2.8 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች በብሔራዊና በክልል ፈተናዎች ላይ ይቀመጣሉ

ቀን:

  • ለብሔራዊ ፈተናው 250 ሚሊዮን ብር በጀት ተመድቧል

በመላ አገሪቱ በግንቦት መጨረሻና በሰኔ መግቢያ በሚካሄደው የብሔራዊና የክልል ፈተናዎች 2,864,913 ተማሪዎች ለመፈተን መመዝገባቸውን የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አስታወቁ፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አቶ አርዓያ ገብረ እግዚአብሔር ከሪፖርተር ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፣ ለተፈታኞች የፈተና መግቢያ (አድሚሽን) ካርድ የታደለ ሲሆን፣ ለብሔራዊ ፈተና ዝግጅትና ማስፈጸሚያ የሚውል 250 ሚሊዮን ብር በጀትም ተመድቧል፡፡

ፈተናውን ለመፈተን ከተመዘገቡት መካከል 1,369,448 የስምንተኛ፣ 1,206,839 የሁለተኛ ደረጃ የአጠቃላይ ትምህርት ማጠናቀቂያ እንዲሁም 288,626 የመሰናዶ ትምህርት መልቀቂያ ተፈታኞች ናቸው፡፡ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቁጥር ከአምናው በ40,000፣ የ10ኛ ክፍል ተፈታኞች ቁጥር ደግሞ በ200,000 ብልጫ አሳይቷል፡፡

ከታዳጊ ክልሎች በስተቀር የስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሒደትና አፈጻጸም በክልል ደረጃ የሚከናወን ሲሆን፣ የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል የፈተና ዝግጅትና አፈጻጸም በብሔራዊ ደረጃ ይከናወናል፡፡ የታዳጊ ክልሎች የስምንተኛ ክፍል ፈተና በብሔራዊ ደረጃ እንደተዘጋጀ፣ ሒደቱን የሚያስተዳድሩትና ፈተናውን አርመው ውጤት የሚሰጡት፣ ታዳጊ ክልሎቹ እንደሆኑና ይህ ዓይነቱ ድጋፍ የተደረገላቸው አቅም እስከሚኖራቸው  እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

በብሔራዊ ደረጃ የሚከናወነው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከግንቦት 28 ቀን እስከ ሰኔ 1 ቀን፣ የ10ኛ ክፍል ፈተና ከግንቦት 23 ቀን እስከ ግንቦት 25 ቀን፣ የስምንተኛ ክፍል ከሰኔ 7 ቀን እስከ ሰኔ 9 ቀን 2009 ዓ.ም. እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

ለብሔራዊ ተፈታኞች በፕላዝማና በፊት ለፊት ገለጻ የሚሰጥ ሲሆን፣ በፈተና ጣቢያ ኃላፊነት፣ በተቆጣጣሪነትና በፈታኝነት የሚሰማሩ 52,000 መምህራን ተመልምለዋል፡፡ በድጋፍ ሰጪነት በመሰማራት የፈተና መልስ ወረቀት የሚያደራጁ 20,000 ርዕሰ መምህራን፣ የወረዳ ጣቢያ ኃላፊዎችና ፖሊሶችም ተመርጠዋል፡፡

3,500 የፈተና ጣቢያዎች የተዘጋጁ ሲሆን፣ ከዚህም ውስጥ ወደ 1,000 የሚጠጉ ጣቢያዎች ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ይውላሉ፡፡ የቀሩት 2,500 ጣቢያዎች ደግሞ ለ10ኛ ክፍል ተፈታኞች የሚውሉ ናቸው፡፡

የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ተማሪዎች ቀደም ብሎ በነበረው የፈተና ዝግጅት ላይ አስተያየት እንዲሰጡ መደረጉንና ይህም አስተያየት ለዘንድሮ የፈተና ዝግጅት እንደ ግብዓት መወሰዱንም አክለዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቤተክህነት ባቀረበችው የይግባኝ አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለዕሮብ ተቀጠረ

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀገወጥ ነው በተባለው አዲሱ ሲኖዶስና...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...