Friday, March 31, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት የቅርንጫፍ ኃላፊዎች በሙስና ተጠርጥረው ተከሰሱ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

– ከባንኩ ደንበኞች ሒሳብ በመቀነስ ወደ ራሳቸው አካውንት አስገብተዋል ተብሏል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሠረት ደፋር ቅርንጫፍ የደንበኞች አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮናታን ኃይሉና የውስጥ ተቆጣጣሪ ኦዲተር የሆኑት አቶ ደሳለ አበራ፣ ሥልጣናቸውን ያላግባብ ተጠቅመው ለሌላ ሰው ጥቅም በማስገኘት ተጠርጥረው፣ ኅዳር 8 ቀን 2008 ዓ.ም. የሙስና ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመሠረተባቸው ክስ እንደሚያስረዳው፣ ሥራ አስኪያጁ አቶ መርሻ አጥናፉ ለተባሉ የባንኩ ደንበኛ ጥቅም ለማስገኘት በማሰብ የነበራቸው 792,887 ብር መሆኑን እያወቁ 1,292,887 ብር እንዳላቸው አድርገው ደብዳቤ ጽፈውላቸዋል፡፡ ደብዳቤውን የጻፉት ደግሞ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽሕፈት ቤት ነው፡፡

ያላቸውን ኃላፊነት ያላግባብ በመጠቀም ከባንኩ አሠራርና ሥነ ምግባር ውጪ ከተለያዩ ደንበኞች ጋር የጥቅም ግንኙነት ለማድረግ እንዲመቻቸው፣ የግል የባንክ ሒሳብ ቁጥር በመፍጠር ከ3,947,266 ብር በላይ ያንቀሳቀሱ እንደነበርም ዓቃቤ ሕግ ገልጿል፡፡ ያላግባብ የአቅም ማሳያ ለአስተዳደሩ ከጻፉላቸው ግለሰብ 18,400 ብር ወደ ግል ሒሳባቸው ማስገባታቸውንም አክሏል፡፡

በቅርንጫፉ የውስጥ ኦዲተር የሆኑት አቶ ደሳለ አበራ፣ ሥልጣናቸውን በመጠቀም የባንኩ ደንበኛ ከሆኑት አቶ ሐሰን ባቲ ከተባሉ ግለሰብ ሒሳብ ላይ 8,000 ብር ቀንሰው ወደ ራሳቸው አካውንት ገቢ ማድረጋቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡ አቶ ያሲን አብዱራሀማን ከሚባሉ የባንኩ ደንበኛ ሒሳብ ላይ 10,000 ብር፣ አቶ ባካል ተሾመ ከሚባሉ ደንበኛ ሒሳብ ላይ ደግሞ 7,000 ብር ቀንሰው ወደ ራሳቸው ሒሳብ ገቢ ማድረጋቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡

አቶ ደሳለ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሠረት ደፋር ቅርንጫፍ ደንበኞች ሒሳብ ላይ በአጠቃላይ 25,000 ብር ተቀናሽ በማድረግ ወደ ራሳቸው ሒሳብ በማስገባት፣ በሥልጣን ያላግባብ የመገልገል የሙስና ወንጀል መፈጸማቸውን ጠቅሶ፣ የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ክስ መሥርቶባቸዋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች