Saturday, November 26, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ኪንና ባህልበስደትና በአካባቢ ጥበቃ የሚያተኩር ፊልም ፌስቲቫል በሚያዝያ ይካሄዳል

  በስደትና በአካባቢ ጥበቃ የሚያተኩር ፊልም ፌስቲቫል በሚያዝያ ይካሄዳል

  ቀን:

  የዘንድሮው አዲስ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል ትኩረት በሕገወጥ ስደትና በአካባቢ ደኅንነት ጥበቃ ላይ መሆኑን ኢኒሽዬቲቭ አፍሪካ አስታውቋል፡፡

  እንደተቋሙ መግለጫ ለ12ኛ ጊዜ የሚካሄደው አዲስ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል ለዘጋቢ ፊልም አፍቃሪ ተመልካቾች ተወዳጅና መልዕክታቸው ሳቢ የሆኑ ዘጋቢ ፊልሞችን በማሰባሰብ ለዕይታ ያቀርባል፡፡ በዓለም ዙርያ በየዕለቱ የሚያጋጥሙትን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁነቶች እንዲሁም መልካም እሴቶችን የያዙ ዘጋቢ ፊልሞች ለተመልካቾች እንደሚደርሱም አስታውቋል፡፡

  ከሚያዝያ 23 ቀን እስከ ሚያዝያ 28 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በሚገኙ የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት፣ በጣሊያን የባህል ማዕከልና በቫምዳስ የባህል ሲኒማ በርካታ  ዘጋቢ ፊልሞች ለተመልካቾች ይደርሳሉ፡፡

  በፌስቲቫሉ ከሚቀርቡ ፊልሞች ውስጥ በዋናነት ስለ ሕገወጥ ስደትና ስለአካባቢ ጥበቃ ግንዛቤን ለማስፋት የሚረዱ አዝናኝና አስተማሪ ፊልሞች ሲሆኑ፣ እጅግ አንገብጋቢ የሆኑ ጉዳዮች በመሆናቸው ትኩረት ለማድረግ መገደዱንም ተቋሙ ሳይገልፅ አላለፈም፡፡ ዳይሬክተሮችንም በመጋበዝ በፊልማቸውና ፊልሞቹን የሠሩበትን ምክንያት ለተመልካቾች ማብራሪያ የሚሰጡበት ይሆናል፡፡

  ኢኒሽዬቲቭ አፍሪካ ይህንን እውነታ በመገንዘብ ከ1999 ዓ.ም. ጀምሮ በየዓመቱ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባበር ሲያዘጋጅ በቆየው የዘጋቢ ፊልሞች ፌስቲቫል እስካሁን ከ630 በላይ ወቅታዊና ማኅበራዊ ጉዳዮችን የሚዳስሱ የአገር ውስጥና የውጭ አገሮች ዘጋቢ ፊልሞች ለዕይታ ቀርበው በየፌስቲቫሉም ከ7000 በላይ የሚሆኑ ታዳሚዎችን ሲያሳትፍ መቆየቱንም ገልጿል፡፡

  ኢኒሽዬቲቭ አፍሪካ የፊልም ፌስቲቫል ማዘጋጀት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ዓላማው አድርጎ የተነሳው ኅብረተሰቡን በተለያዩ ማኅበረሰባዊ ተግዳሮቶቹ ዙሪያ እንዲወያይና ሐሳብ እንዲለዋወጥ፣ ብሎም የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ማብቃት ነው፡፡

   

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን 55 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ወሰነ

  የአዋሽ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ዛሬ ህዳር 17 ቀን 2015...

  ከብሔራዊ ባንክ እውቅና ያገኘው ፔይሊንክ አክሲዮን ማህበር ምሥረታውን አካሄደ

  ከገንዘብ ንክኪ ነፃ የሆነ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ለመተግበር ያቀደው...

  የተወሳሰበው ሰላም የማስፈን ሒደት

  የደቡብ አፍሪካ የሰላም ስምምነት ተፈርሞ ብዙም ሳይዘገይ የኬንያው ቀጣይ...