Thursday, March 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊፀረ ሙስና ኮሚሽን ለጊዳቦ ግድብ ያላግባብ ክፍያ ተፈጽሟል በመባሉ ማስረጃ ጠየቀ

ፀረ ሙስና ኮሚሽን ለጊዳቦ ግድብ ያላግባብ ክፍያ ተፈጽሟል በመባሉ ማስረጃ ጠየቀ

ቀን:

– ያልሠሩበትን ክፍያ ተቀብለዋል የተባሉ ከ17 በላይ ድርጅቶች ተጠቅሰዋል

የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የኢትዮጵያ ውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት በሚገነባው የጊዳቦ ግድብ ያላግባብ ክፍያ ፈጽሟል በመባሉ ማስረጃ ጠየቀው፡፡ ድርጅቱ ማስረጃ እንዲያቀርብ የተጠየቀው ለጊዳቦ ግድብና የመስኖ ፕሮጀክት ለማሽነሪዎች ኪራይና ለተሽከርካሪዎች የጭነት ምልልስ ክፍያ ሲፈጽም፣ ያልተሠራበትን እየጨመረ መሆኑ ጥቆማ ስላቀረበበት ነው፡፡

ከኅዳር ወር 2005 ዓ.ም. እስከ የካቲት ወር 2006 ዓ.ም. ቁጥራቸው ከ17 በላይ ለሚሆኑ የማሽኖችና የተሽከርካሪዎች አከራይ ድርጅቶች ከ1.1 ሚሊዮን ብር በላይ ያላግባብ ክፍያ መፈጸሙን ከማስረጃ ጋር ጥቆማ እንደደረሰው የጠቀሰው ኮሚሽኑ ምርመራውን እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቆ፣ ምርመራውን ለማጣራት ይጠቅማል የሚለውን ተጨማሪ ማስረጃ ድርጅቱ እንዲልክ በዝርዝር በደብዳቤ ልኮለታል፡፡

የኢትዮጵያ ውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ኦዲት መደረጉን ያስታወሰው ኮሚሽኑ ኦዲት ሲደረግ የነበሩ የኮሚቴ አባላት ስም ዝርዝር፣ ኮሚቴው የተፈራረመበትን ቃለ ጉባዔ፣ የዕለታዊ ሥራ እንቅስቃሴ መመዝገቢያና መቆጣጠሪያ መዝገብ፣ ከአከራይ ድርጅቶች ጋር ያደረገው የውል ስምምነት፣ የውስጥ አሠራር ደንብና መመርያ፣ የተጠርጣሪዎች ስም ዝርዝር፣ ለአከራዮች የተከፈሉ ክፍያዎች እንዴት እንደተከፈሉ የሚገልጽ ማስረጃና ሌሎችንም ማስረጃዎች እንዲልክለት ጠይቋል፡፡

በተሻሻለው የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 433/97 አንቀጽ 26 (3 እና 4) መሠረት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች ከኮሚሽኑ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ምላሽ የመስጠት ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡

የውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ገቢውን በትክክል ባለማሳወቅ፣ ያለቫት ደረሰኝ በካሽ ደረሰኝ ብቻ ገንዘብ በመሰብሰብና ባለድርሻ ከሆነበት ድርጅት የሚያገኘውን የአክሲዮን ትርፍ ባለማሳወቅ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የተጭበረበረ ግብርና ቀረጥ ተጠርጥሮ፣ የዶክመንቴሽን ክፍሉና የተወሰኑ ፋይል ካቢኔቶች መታሸጋቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ሰሞኑን ተጨማሪ እሸጋ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡  

   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...