‹‹ችግሮች ያሉባቸውን አካባቢዎች በመለየት በወቅቱ ለመፍታት እንሞክራለን፡፡ ሕዝብ በብዛት በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎችም ጠንካራ ቁጥጥር እናደርጋለን፡፡››
ዶ/ር ኢንጂነር ጌታቸው በትሩ፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ በዕለተ ሰንበት (መስከረም 9 ቀን 2008 ዓ.ም.) ሥራ የጀመረውን የአዲስ አበባ ከተማ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት በማስመልከት ስለሚደረጉ ጥንቃቄዎችና የአገልግሎት አሰጣጥ ከተናገሩት፡፡ የባቡሩን 17 ኪሎ ሜትር በመሸፈን ከዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ እስከ ቃሊቲ ማሠልጠኛ የተዘረጋው ቀላል ባቡር መስመር ከቻይና በተገኘ 475 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ የተገነባ ሲሆን፣ ለተሳፋሪዎች ከሁለት ብር እስከ ስድስት ብር ታሪፍ ወጥቶለት አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡