Tuesday, March 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአስከሬን ምርመራ ውጤት መዘግየት ችግር መፍጠሩ ተጠቆመ

የአስከሬን ምርመራ ውጤት መዘግየት ችግር መፍጠሩ ተጠቆመ

ቀን:

–  ችግሩ የተርጓሚ እጥረት ነው ተብሏል

ከአዲስ አበባ ከተማም ሆነ ከክልል ለሚመጣ በዳግማዊ ምንሊክ ሆስፒታል የሚደረገው የአስከሬን ምርመራ ውጤት መዘግየት ከፍተኛ ችግር መፍጠሩ ተጠቆመ፡፡

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በደረሱ የተለያዩ አደጋዎች ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎችን አስከሬን ምርመራ ውጤት ለማግኘት፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከሁለት ወራት በላይ እየጠበቀ መሆኑን የሰው መግደልና ወንጀል ምርመራ ዲቪዚዮን አባላት ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ከሰኔ ወር ጀምሮ የምርመራ ውጤት ማግኘት ባለመቻሉ፣ ለኢንሹራንስና ለተጨማሪ ምርመራ እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮች ማስረጃ ለማቅረብ የሟች ቤተሰቦች እየተንገላቱ መሆኑን የዲቪዚዮኑ ባልደረቦች ገልጸዋል፡፡

ብቸኛ በሆነው የዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል የሚደረገውን የአስከሬን ምርመራ ውጤት፣ ከስፓኒሽኛ ቋንቋ ወደ እንግሊዝኛና ወደ አማርኛ የሚተረጉም አንድ ባለሙያ ብቻ በመኖሩ፣ ለችግሩ ምክንያት መሆኑም ተገልጿል፡፡ የሆስፒታሉ አብዛኛዎቹ የአስከሬን ምርመራ ባለሙያዎች የኩባ ዜጎች መሆናቸው ይታወቃል፡፡

በተለይ ከክልል በሪፈራል ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ሕይወቱ ያለፈ ሰው፣ ቤተሰቦቹ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እየገቡና የፖሊስ ኮሚሽኑን በማስቸገር ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ይዘውት የመጡትን ገንዘብ በሕክምናና በምርመራ ውጤት በመጨረስ ወደ ልመና የሚገቡ እንዳሉም ተጠቁሟል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በተደጋጋሚ ደብዳቤ ከመጻፍ ባለፈ ምንም ማድረግ አለመቻሉንና ከአቅሙ በላይ እንደሆነበትም እየገለጸ ነው፡፡

የዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሪፖርተር አነጋግሯቸው፣ ‹‹እኔ እስከማውቀው ድረስ ምንም የተፈጠረ ችግር የለም፤›› በማለት አስተባብለዋል፡፡ የሆስፒታሉን ሜዲካል ዳይሬክተር ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...