Friday, March 24, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የእስራኤሉ ትድሃር ኮንስትራክሽን ኩባንያ ባለቤት በጉቦና ታክስ ስወራ ተጠርጥረው ተከሰሱ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

የእስራኤሉ ትድሃር ኤክስካቬሽን ኤንድ ኧርዝ ሙቪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ባለቤት፣ ጉቦ በመስጠትና ታክስ ስወራ ወንጀል ተጠርጥረው ሐምሌ 13 ቀን 2007 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ፣ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ክስ የመሠረተባቸው፣ የኩባንያው ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ሚናሼ ሌቪና ኩባንያቸው ትድሃር ኤክስካቬሽን ኤንድ ኧርዝ ሙቪግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ናቸው፡፡

ሚስተር ሌቪ ክስ የተመሠረተባቸው፣ ለኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሦስት ኦዲተሮች ለእያንዳንዳቸው 500 ሺሕ ብር በድምሩ 1.5 ሚሊዮን ብር በመስጠትና ለባለሥልጣኑ ሊከፍሉ ይገባ ከነበረው ታክስ 52,797,779 ብር ውስጥ 46,883,009 ብር ለግል ጥቅማቸው በማዋል ተጠርጥረው መሆኑን የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

የባለሥልጣኑ ኦዲተሮች ከግለሰቡ ጋር በመመሳጠር፣ ለመንግሥት ገቢ መደረግ የሚገባውን ገንዘብ ቀንሰው 6,114,770 ብር ብቻ እንዲከፍሉ በማድረግ በመንግሥት፣ በሕዝብ ጥቅም ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውንም ክሱ ይገልጻል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብታቸው ታልፎ በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ የድርጅቱ ባለቤት በአጠቃላይ ከ140 ሚሊዮን ብር በላይ የታክስ ገቢ አጭበርብረዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሲሆን፣ የወንጀሉን ዝርዝር ድርጊት የሚያስረዱ 11 ክሶች ቀርበውባቸዋል፡፡

ትድሃር ኤክስካቬሽን ኤንድ ኧርዝ ሙቪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ በአዲስ አበባ በመገንባት ላይ ከሚገኙት መንገዶች ውስጥ ከዊንጌት እስከ አቡነ ጴጥሮስ (ማዘጋጃ ቤት ድረስ) ከስድስት ኪሎ (አንበሳ ግቢ) እስከ ፈረንሳይ ጉራራና ከመገናኛ የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ድረስ ያሉትን መንገዶች በመገንባት ላይ ያለ ኩባንያ ነው፡፡

የክስ መቃወሚያ ካለ ለማሰማትና ክሱን ለማንበብ ለሐምሌ 23 ቀን 2007 ዓ.ም. ተቀጥሯል፡፡    

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች