Tuesday, March 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ በድጋሚ ትዕዛዝ ተሰጠ

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ በድጋሚ ትዕዛዝ ተሰጠ

ቀን:

–  የምስክሮች ቃል ከመዝገብ ጋር ባለመያያዙ ጦማሪያን ሌላ ቀጠሮ ተሰጣቸው

በሽብር ድርጊት ተጠርጥረው ክስ በተመሠረተባቸው በእነ ዘመኑ ካሴ የክስ መዝገብ በመከላከያ ምስክርነት የተቆጠሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ለሐምሌ 13 ቀን 2007 ዓ.ም. ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም፣ የመጥሪያው ትዕዛዝ ባመድረሱ ሐምሌ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. እንዲቀርቡ በድጋሚ ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡

የእነ ዘመኑ ካሴን የክስ መዝገብ እየመረመረ የሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት፣ ሐምሌ 7 ቀን 2007 ዓ.ም. በሰጠው ትዕዛዝ፣ አቶ አንዳርጋቸው የግንቦት 7 ድርጅት ከፍተኛ አመራር በነበሩበት ጊዜ ወደ ኤርትራ  ተጉዘው፣ አሁን በሽብር ድርጊት ክስ ተመሥርቶባቸው በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ሆነው በመከራከር ላይ ከሚገኙት ተጠርጣሪዎች አቶ አሸናፊ አካሉ፣ አቶ ደህናሁን ቤዛ፣ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን፣ አቶ አንሙት የኔዋስና፣ አቶ ደሳለኝ አሰፋ ጋር ይገናኙ እንደነበር ዓቃቤ ሕግ በክሱ በመግለጹ፣ እሱን እንዲያስረዱላቸው ነበር፡፡

ነገር ግን ለፌዴራል ማረሚያ ቤቶች እንዲደርሰው የተሰጠው የመጥሪያ ትዕዛዝ፣ በኢድ አልፈጥር በዓል ምክንያት መሥሪያ ቤቶች ዝግ በመሆናቸው ሊላክ አለመቻሉን (ትዕዛዝ የተሰጠው ሐምሌ 7 ሲሆን፣ በዓሉ ሐምሌ 10 ቀን 2007 ዓ.ም. ነበር) እንደተገለጸለት ፍርድ ቤቱ አስታውቆ፣ ሐምሌ 13 ቀን 2007 ዓ.ም. ትዕዛዙ እንዲላክና አቶ አንዳርጋቸው በድጋሚ እንዲቀርቡ አዟል፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ሌላው በዕለቱ ያየው የእነ ሶሊያና ሽመልስን የክስ መዝገብ ሲሆን፣ በዕለቱ መዝገቡ ተቀጥሮ በጦማሪያን በፍቃዱ ኃይሉ፣ አጥናፍ ብርሃኔ፣ ናትናኤል ፈለቀና አቤል ዋበላ ላይ ብይን ለመስጠት ነበር፡፡ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ቃል ከክስ መዝገቡ ጋር ባለመያያዙ ብይኑን ሊሠራ አለመቻሉን ፍርድ ቤቱ ገልጿል፡፡ የምስክሮቹ ቃል ለምን ከመዝገቡ ጋር ሊያያዝ እንዳልቻለ የፍርድ ቤቱ አስተዳደር ቀርቦ እንዲያስረዳም አዟል፡፡ የምስክሮቹ ቃል ከመዝገቡ ጋር መያያዙን ለመጠባበቅ ለሐምሌ 22 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ የምስክሮቹ ቃል ከተያያዘ በአጭር ቀናት ውስጥ ብይኑን ሠርቶ እንደሚነግራቸውም ፍርድ ቤቱ አስታውቋል፡፡

ሐምሌ 1 ቀን እና 2 ቀን 2007 ዓ.ም. በድንገት ክሳቸው መቋረጡ ተነግሯቸው ከእስር የተፈቱት ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ፣ ኤዶም ካሳዬ፣ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ እንዲሁም ጦማሪያን ዘለዓለም ክብረትና ማህሌት ፋንታሁን፣ ከአንድ ዓመት በፊት በቁጥጥር ሥር ሲውሉ ከቤታቸውና ከቢሮአቸው በፍተሻ የተወሰዱባቸውና በኤግዚቢትነት የተያዙ ንብረቶቻቸው እንዲመለሱላቸው ለፍርድ ቤቱ አመልክተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ትዕዛዝ እንደሚሰጥበት ነግሯቸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹ከኦነግ ሸኔ ጋር ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ከፍተኛ ፍላጎት አለን›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ

መንግሥት ከ‹‹ኦነግ ሸኔ››ጋር ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ከፍተኛ ፍላጎት...

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...