Sunday, June 4, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የአውሮፓ ኅብረት ለሴፍቲኔት ፕሮግራምና ለመንገድ ዘርፍ የ4.4 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ሰጠ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

በአዲስ አበባ የተካሄደውን ሦስተኛውን ፋይናንስ ለልማት ጉባዔ ሲታደሙ የሰነበቱት የአውሮፓ ኅብረት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ ለኢትዮጵያ የሴፍቲኔት ፕሮግራምና ለመንገድ ዘርፍ ልማት የሚውል የ4.4 ቢሊዮን ብር ወይም፣ የ190 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ኅብረቱ መስጠቱን በማስመልከት ከመንግሥት ጋር ስምምነት ፈረሙ፡፡

ሐምሌ 10 ቀን 2007 ዓ.ም. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ዋና መሥሪያ ቤት በተካሄዴው ስምምነት ወቅት እንደተገለጸው፣ ለውጤት ተኮር ሴፍቲኔት ፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ 1.1 ቢሊዮን ብር ወይም የ50 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ሲደረግ፣ ለመንገድ ኔትወርክ ማስፋፊያ እንዲውል የተሰጠው ደግሞ 3.3 ቢሊዮን ብር ወይም 140 ሚሊዮን ዩሮ ነው፡፡

በአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን የዓለም አቀፍ ትብብርና ልማት ኮሚሽነር ኔቨን ሚሚካ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ አቶ ሱፊያን አህመድ ጋር ዕርዳታ ስምምነቱን ተፈራርመዋል፡፡

የአውሮፓ ኅብረት በሴፍቲኔት በኩል የሰጠው ድጋፍ በኢትዮጵያ ተጨማሪ 4.7 ሚሊዮን የምግብ ዋስትና ችግር ላለባቸው ዜጎች የሚውል ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም ድጋፍ ሲያገኙ የነበሩ 3.6 ሚሊዮን ዜጎችን እንደሚያካትትም ሚሚካ አስታውቀዋል፡፡ አቶ ሱፊያን በሰጡት መግለጫ፣ የአውሮፓ ኅብረት እ.ኤ.አ. ከ2005 ጀምሮ 1.1 ቢሊዮን ዩሮ ለኢትዮጵያ የልማት ሥራዎች የፋይናንስ ድጋፍ መስጠቱን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ 40 ሚሊዮን ዩሮ ብድር መስጠቱን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ የባንኩ ኃላፊዎች በሰጡት መግለጫ መሠረት፣ ለኢትዮጵያ መንግሥት የተሰጠው ብድር በሃያ ዓመታት ወስጥ የሚከፈል ነው፡፡ ከዚህ ጎን ለጎንም የፈረንሳይና የጣልያን መንግሥታት በጋራ 40 ሚሊዮን ዩሮ በማቅረብ፣ በጠቅላላው የ80 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክና ከአባል አገሮቹ የተገኘው ገንዘብ ለመካከለኛና አነስተኛ ከተሞች የመጠጥ ውኃ አቅርቦትና የሳኒታሪ ሥራዎች ማስፋፊያ ይውላል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች