Tuesday, March 28, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የኤርፖርት ታክሲዎች በዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ሊቀየሩ ነው

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

–  አገልግሎቱንና ቁጥጥሩን የሚመለከት አዲስ መመርያ ወጣ

ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ የውጭ እንግዶችና ከውጭ ወደ አገር ውስጥ ለሚገቡ ዜጎች ደረጃውን የጠበቀ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት፣ በአሁኑ ጊዜ በኤርፖርት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ታክሲዎችን በዘመናዊ 2015 ሞዴል ተሽከርካሪዎች ሊቀየሩ ነው፡፡

በአምስት ማኅበራት የታቃፉ ቁጥራቸው ከ400 በላይ የሚሆኑ የታክሲ ባለንብረቶች ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት፣ ሥሪታቸው ጃፓን የሆኑና እስከ ስምንት ሰው የሚጭኑ ቶዮታ አቫንዛ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ ተፈቅዶላቸዋል፡፡

ወገባቸው ላይ ቀጭን አርንጓዴ ቀለም የተሰመረባቸው ሙሉ ቢጫ ታክሲዎችን የሚተኩት አዲሶቹ ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ መንግሥት የፈቀደ መሆኑን ትራንስፖርት ሚኒስቴር ያስታወቀ ሲሆን፣ አገልግሎት አሰጣጣቸውን ለመወሰንና ለመቆጣጠር አዲስ መመርያ (መመርያ ቁጥር 8/2007) አውጥቷል፡፡

በቱሪስት ታክሲነት የሚያገለግሉት ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ዓይነትና ሞዴል ተለይቶ በማለቁ፣ መመርያው በሚያዘው መረሠረት መሟላት የሚገባቸውን መሥፈርቶች አሟልተው በቅርቡ ወደ አገር ውስጥ እንደሚገቡ ሰነዶች ያመላክታሉ፡፡

ቋሚ የቱሪስት ታክሲ ሆነው የሚያገለግሉት ዘመናዊ አቫንዛ ተሽከርካሪዎች፣ በአውሮፕላን ማረፊያና በባለ ኮከብ ሆቴሎች በመቆም በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ዕውቅና ባገኙ ማኅበራት፣ በአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የሙያ ፈቃድ፣ ለቱሪስት በስምምነት በሚወሰን ታሪፍ በመሥራት አገልግሎት የሚሰጡ መሆናቸውን፣ በትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ተፈርሞ የወጣው መመርያ ይገልጻል፡፡

ማኅበራቱ ደረጃውን ጠብቀው ለሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ባስገቡት ‹‹ከቀረጥ ነፃ ይፈቀድልን›› ጥያቄ  መሠረት፣ ተቋማቱ የማኅበራቱ ጥያቄ ተገቢና በአገር ገጽታ ግንባታ ረገድ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን በማመን እንደተፈቀደላቸው ሰነዶቹ ያስረዳሉ፡፡

የኤርፖርት ታክሲዎች እንግዶች ለተለያዩ ጉዳዮች ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ የሚቀበሉ የመጀመሪያዎቹ አምባሳደሮች ተደርገው ሊታዩ እንደሚገባ፣ ጠያቂዎቹም እንደ ጀማሪ ኢንቨስተር ታይተው ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን እንዲያስገቡ እንዲፈቀድላቸው አስተያየታቸውን ከሰጡት የመንግሥት ተቋማት አንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው፡፡ ትራስፖርት ሚኒስቴርና ኢንቨስትመንት ኮሚሽንም ይሁንታውን በመስጠታቸው ተፈቅዶላቸዋል፡፡

የአገልግሎት አሰጣጥን ለመወሰንና ለመቆጣጠርም መመርያ ወጥቶ ተግባራዊ ሆኗል፡፡ ከ400 በላይ አባላት ያሉዋቸው ቦሌ አንድነት፣ ቁጥር አንድ ቦሌ፣ ስኬት ቦሌ፣ መቅደላ ህዳሴ የተባሉ አምስት ቋሚ የታክሲ ባለንብረቶች ማኅበራት ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች