የአገሪቱ የመጀመርያው እንደሆነ የተገለጸውና በጤናው ዘርፍ በተለይም አገልግሎትን በሚመለከት ዓይነተኛ ሚና እንደሚኖረው የታመነበት የአገልግሎት ማውጫ ሐሙስ ግንቦት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ተመርቋል፡፡
በደብሊው ኤች አሳታሚና አጋሮቹ ተዘጋጅቶ ለአገልግሎት የበቃው የጤና አገልግሎት ሰጭዎች ማውጫ በመንግሥትም ሆነ በግሉ ዘርፍ ያሉ ሆስፒታሎች፣ ክሊኒኮች፣ የሕክምና መገልገያ አስመጪዎችንና በዘርፉ ያሉ ሌሎች አካላትንም አድራሻ የያዘ ነው፡፡ ማውጫው በፌስቡክና በሞባይል አፕልኬሽንም ተደራሽ ይሆን ዘንድ ተዘጋጅቷል፡፡
ማውጫው በተመረቀበት ሥነ ሥርዓት ላይ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ልዩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር አዲስ ታምሬ ተገኝተዋል፡፡