ዘውዳዊውን ሥርዓት፣ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት መንበርን ያነቃነቀውና በመስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም. እንዲወገድ ያደረገው አብዮት በግብታዊነት የፈነዳው በየካቲት 1966 ዓ.ም. ነበር፡፡ ዘንድሮ 44ኛ ዓመቱ ላይ ደርሷል፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ዋና ዋና መንገዶችና አደባባዮች ዘውዳዊ ሥርዓቱን በመቃወም የተለያየ ትዕይንተ ሕዝብ ተካሂዷል፡፡ ከነዚህም በዩኒቨርሲቲና በሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችና መምህራን ሲቀነቀን የነበረው ‹‹ሕዝባዊ መንግሥት ይቋቋም›› በየአደባባዩ ከታዩት መፈክሮች መካከል ይጠቀሳል፡፡
ሔኖክ መደብር