Tuesday, December 6, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናበሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው ለዶ/ር መረራ ጉዲና አቀባበል አደረጉ

  በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው ለዶ/ር መረራ ጉዲና አቀባበል አደረጉ

  ቀን:

  ዛሬ ጥር 9 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀትር በኃላ ለዶ/ር መረራ ጉዲና ከእስር ቤት መለቀቃቸውን ተከትሎ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው በዶክተሩ መኖሪያ አካባቢ ተገኝተው አቀባበል አደረጉላቸው። የተጠረጠሩበት ክስ በመንግሥት ተቋርጦ ከእስር ቤት የተለቀቁት / መረራ፣አዲስ አበባ ወደ አምቦ በሚወስደው ዋና መንገድ አሸዋ ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ከቀትር በኃላ ገብተዋል፡፡ለዶክተር መረራ ከበርካታ ኪሎ ሜትሮች ጀምሮ እስከ መኖሪያ ቤታቸው ድረስ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው ጎዳና ወጥተው የሞቀ አባበል አድርገውላቸዋል።

  መኖሪያ አካባቢያቸው ተገኝተው አቀባበል ላደረጉላቸው ደጋፊዎቻቸውም / መረራ በኦሮሚኛ ቋንቋ ንግግር አድርገዋል። ወደ መኖሪያ ቤታቸው ከገቡ በኃላም ለአገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች አጭር መግለጫ አድርገዋል።

  በዚህ መግለጫቸውም ከእስር መለቀቃቸውን ያደነቁ ሲሆን፣ በቀጣይ ስለሚያደርጉት የፖለቲካ ትግል ከፓርቲያቸው ጋር በመመካከር እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል። ሌሎች ፖለቲከኞችም ይፈታሉ የሚል እምነታቸውንም ተናግረዋል።

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...