Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትኢሠማኮ በስፖርቱ ወንጂ ላይ ከትሟል

ኢሠማኮ በስፖርቱ ወንጂ ላይ ከትሟል

ቀን:

በዓመት ውስጥ ከሚደረጉ የስፖርት ውድድሮች በተለይ የክረምት ወቅትን ጠብቆ በሠራተኛው የሚደረገው አገር አቀፍ ውድድር ዋነኛው ነው፡፡ በተለይ ሠራተኛውን ለማገናኘትና ለማቀራረብ በሚደረጉ ውድድሮች አሁን ላይ ብዙም ትኩረት ያላገኙ ግን ታሪካዊ ዳራ የነበራቸው ጨዋታዎችን በዚህ የሠራተኞች ውድድር ላይ መመልከት የተለመደ ነው፡፡ በየዓመቱ በኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አዘጋጅነት በወንጂ ከተማ ስፖርታዊ ውድድሮች ይደረጋሉ፡፡ ሐምሌ 10 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ለ15 ቀናት በወንጂ ከተማ ለሚደረገው ስፖርታዊ ውድድር የተለያዩ ተከፋይ ድርጅቶች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል፡፡ በዚህ ዓመታዊ የአገር አቀፍ ስፖርት ውድድር ከባህላዊ ስፖርት ገበጣን ጨምሮ ፣ ዳርት፣ ዳማና ቼዝን፣ እንዲሁም እግር ኳስ፣ መረብ፣ ሩጫና ከረንቡላን አካቶ ለ15 ቀናት ይከናወናል፡፡ ዕድሜ ጠገቡ የሠራተኞች ዓመታዊ የስፖርት ዝግጅት የኢትዮጵያ አንበሳ አውቶበስ ድርጅትን፣ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎትና የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የመሳሰሉ አንጋፋ ድርጅቶች ከሚሳተፉት ግንባር ቀደሞቹ ናቸው፡፡ በውድድሩም በአጠቃላይ 1069 ወንዶችና 254 ሴቶች በድምሩ 1,323 ስፖርተኞች ተካፋይ ሆነዋል፡፡ አገር አቀፍ የሠራተኞች የቤተሰብ ስፖርት ውድድርን አስመልክቶ የኢሠማኮ የማኅበራዊ ጉዳዮች ኃላፊና የስፖርት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ፍሥሐጽዮን ቢያድግልኝ እንደተናገሩት ከሆነ፣ ‹‹ዓመታዊው የሠራተኞች አገር አቀፍ ውድድር ማካሄድ በማኅበራት ውስጥ ያለውን ቤተሰባዊ ግንኙነት ለማጠናከርና ሠራተኞቹ በሥራቸው ላይ የሚያሳዩትን ውጤታማነት የሚያጎለብት ነው፡፡›› ቀደም ብሎ በበጋ ወቅት በተደረገ ማጣሪያ ጨዋታ መሠረት በስኬት ያለፉ ማኅበራት ለአገር አቀፍ ውድድሮች የሚደርሱ ሲሆን፣ በተለይ በዚህ ውድድር ላይ የሚሳተፉ ማኅበራት ፉክክር ከፍተኛ እንደሆነ አቶ ፍሥሐ አክለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በዓመታዊ ውድድር ላይ በመረብ ኳስና በእግር ኳስ የመጀመርያ ተፎካካሪ ነው፡፡ በዘንድሮ ውድድር ከፍተኛ ዝግጅት አድርጎ መምጣቱን ጭምር የእግር ኳሱ ዋና አሠልጣኝ ሔኖክ አድማሱ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ በመክፈቻ ዕለት በተደረገው የእግር ኳስ ጨዋታ ማይጨው ችፑድ ፋብሪካ መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካን 2 ለ0 አሸንፏል፡፡ ቀደም ብሎ በውድድሩ ላይ ሲሳተፉ የነበሩ ተጨዋቾች ‹‹ሠራተኛ አይደሉም የሚል ቅሬታ፤›› ሲያስነሳ የነበረ ጉዳይ ቢሆንም በዘንድሮ ውድድር ሁለት ተጨዋቾች ብቻ ከሠራተኛ ውጪ እንዲሳተፉ መደረጉን ተሳታፊ ማኅበራት ገልጸው፣ ለዚህም እንደምክንያትነት የሚነሳው ደግሞ በየጊዜው ከሥራ የሚለቁ ሠራተኞችን ለመተካት በማሰብ እንደሆነም ተብራርቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...