Monday, December 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  ክቡር ሚኒስትር

  [የክቡር ሚኒስትሩ ሾፌር ፌስቡክ እያያ ይስቃል]

  • አንተ ሰውዬ አበድክ እንዴ?
  • ምነው ክቡር ሚኒስትር?
  • ብቻህን ምን ያስገለፍጥሃል?
  • ፌስቡክ እያየሁ ነው፡፡
  • እንዴ መቼ ተለቀቀ?
  • ደግሞ ማንን አስራችሁ ነበር?
  • ፌስቡክን ማን ለቀቀው?
  • ለነገሩ ፌስቡክ ራሱ ታስሮ ነበር ለካ፡፡
  • እኮ ማን ለቀቀው?
  • ትንሽ ቆየ እኮ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ምኑ ነው የቆየው?
  • ፌስቡክ ከተለቀቀ፡፡
  • ማነው ልቀቁ ያላቸው?
  • በነካ እጃችሁ ግን ሌሎቹንም ብትለቁ መልካም ነው፡፡
  • እነማንን?
  • በየጊዜው የምታጉሯቸውን ነዋ፡፡
  • ምን አልክ?
  • ግን ፌስቡክ ራሱ እንደ መብራትና ውኃ ልታደርጉት ነው ማለት ነው?
  • እንዴት ማለት?
  • በፈረቃ ነዋ፡፡
  • በፈረቃ ሳይሆን በጨረቃ ነው፡፡
  • እንዴት በጨረቃ?
  • ማታ ማታ ብቻ ነዋ የሚለቀቀው፡፡
  • እሷንም አታሳጣን ብንል ይሻላል፡፡
  • ለመሆኑ ምንድን ነው የሚያስቅህ?
  • እንኩ ይመልከቱት ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • የማነው ቦርጫም በእናትህ?
  • አዩት ዓሳ ነባሪውን?
  • የምን ዓሳ ነባሪ ነው?
  • ቅፅል ስሙ ነው፡፡
  • ይኼ ነው ያስገለፈጠህ?
  • እህሳ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ይኼ ያስለቅሳል እንጂ ምኑ ያስቃል?
  • ኢትዮጵያን ወክሎ ተወዳድሮ ነው እኮ፡፡
  • በምን?
  • በዋና፡፡
  • በዚህ ቦርጭ?
  • አይገርምዎትም ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እና እንዴት ሆነ?
  • አዋረደን ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ግን ሲታይ ልማታዊ ይመስላል፡፡
  • እንዴት ማለት?
  • ቦርጩ የአገሪቷን ልማት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡
  • ምን አሉኝ?
  • አታየውም እንዴ ቦርጩ ላይ የ11 በመቶ ዕድገቱን?
  • ይኼ የሚያሳየውማ ዕድገቱን ሳይሆን ውድቀቱን ነው፡፡
  • ስማ ሁሌ የመፍትሔ ሰው ነው መሆን ያለብህ፡፡
  • ምን ማለት ነው?
  • ይኼ ሰውዬ ኦሊምፒክ የላክነው ሆን ብለን ነው፡፡
  • ለምን ተላከ?
  • ለአገር ገጽታ ግንባታ፡፡
  • ይኼ ገጽታችንን ያፈርሰዋል እንጂ እንዴት ይገነባዋል?
  • ኢትዮጵያ ዓለም ላይ የምትታወቀው በረሃብና በድርቅ ነው፡፡
  • እሱማ ልክ ነው፡፡
  • እና ፈረንጆቹ በልተን ጠግበን የምናድር አይመስላቸውማ፡፡
  • አሁንም እኮ በልተው የጠገቡት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
  • ፖለቲካህን እዛው፡፡
  • እውነቴን ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ለማንኛውም እንደዚህ ዓይነት ቦርጫም ኢትዮጵያዊ ሲያዩ ፈረንጆቹ አመለካከታቸው ይቀየራል፡፡
  • እንዴት ይቀየራል?
  • ጠግበን እንደምናድር ያውቃሉ፡፡
  • ኧረ ክቡር ሚኒስትር ኦሎምፒኩን የተሳተፈው እኮ አባቱ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ስለሆኑ ነው ይባላል?
  • ታዲያ ቢሆኑ ምን አለበት?
  • እ . . .
  • አሁን የእኔ ዘመዶች ሁሉም የመንግሥት ባለሥልጣናት ናቸው፡፡
  • እሱስ ልክ ነው፡፡
  • ከባለሥልጣኖቹ ውጪ ነጋዴዎች ናቸው፡፡
  • ለነገሩ አገሪቷ በእጃችሁ ናት፡፡
  • ከእጃችን ልትወጣ አትችልም፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር ግን እንደዚህ እስከ መቼ ይቀጥላል?
  • ምን ማለት ነው?
  • በየቀበሌው ራሱ ሲኬድ ሁሉም በወንዝ ነው የተደራጀው፡፡
  • ኧረ አንተስ ወንዝ ይዞህ ይሂድ፡፡
  • ምን አደረኩ ክቡር ሚኒስትር?
  • ወሬ ታበዛለህ፡፡
  • አገራችን ተዋረደች እያልኩዎት እኮ ነው፡፡
  • ገጽታ ግንባታ ነው አልኩህ?
  • ታዲያ ሰውዬው ዋናተኛ መባል የለበትማ፡፡
  • ምን ይባል ታዲያ?
  • በላተኛ!

   

  [ለክቡር ሚኒስትሩ ከውጭ ስልክ ተደወለላቸው]

  • ምን እያደረጋችሁ ነው ክቡር ሚኒስትር?
  • እያደግን ነዋ፡፡
  • ኧረ ይኼ ያሳፍራል፡፡
  • ምኑ ነው የሚያሳፍረው?
  • እየሠራችሁት ያለው ነገር፡፡
  • አገራችንን ማሳደጋችን ነው የሚያሳፍረው?
  • እንደዚህ እየቀለዳችሁ ግን እስከ መቼ ነው የምትቀጥሉት?
  • ገና እየጀመርን አይደል እንዴ?
  • ቀልዱን ነው?
  • ምን ይላል ይኼ?
  • ክቡር ሚኒስትር ይህቺ የተከበረች አገር እያዋረዳችኋት ነው?
  • እያከበራችኋት ነው ማለትህ ነው?
  • ይኸው አንገታችንን አቀርቅረን እንድንሄድ አደረጋችሁን፡፡
  • ስማ አቀርቅረህ መሄድህ እኮ ጥሩ ነው፡፡
  • ምን እያሉ ነው?
  • እንቅፋት እንዳይመታህ ነዋ፡፡
  • ኧረ ይኼ ማላገጥ ይቅር ክቡር ሚኒስትር?
  • የምን ማላገጥ ነው?
  • ኦሊምፒክ የላካችሁት ሰውዬ ምንድን ነው?
  • የቱ ሰውዬ?
  • ዓሳ ነባሪው ነዋ፡፡
  • ሆን ብለን ነው የላክነው፡፡
  • ምን?
  • ለአገር ገጽታ ግንባታ ነው፡፡
  • ይኼ የአገር ገጽታን ያበላሻል እንጂ ምን ይገነባል?
  • አየህ ፈረንጆች የሚያውቁን በድርቅና በረሃብ ነው፡፡
  • አሁንስ ቢሆን ከእሱ መቼ ተላቀቅን?
  • ስለዚህ እንደዚህ ዓይነት ቦርጫም ዋናተኛ ትልክና አገሪቱ ውስጥ ጥጋብ መኖሩን ታሳያለህ፡፡
  • ግን እንደዚህ እየቀለዳችሁ የምትዘልቁ ይመስላችኋል?
  • ምን እያልክ ነው?
  • በዚህ ጉዳይ በዓለም ደረጃ አገራችን ነው የተዋረደችው፡፡
  • ለምንድን ነው የተዋረደችው?
  • ለነገሩ እናንተ ራሳችሁ አዋራጆች ናችሁ፡፡
  • ምን አድርገን?
  • ስንት ዓለም አቀፍ ውሎችና ውሳኔዎችን በሚገባ ማንበብና መረዳት አቅቷችሁ፣ አዋርዳችሁን የለ እንዴ?
  • ምን ትዘባርቃለህ?
  • እናንተ ፖለቲከኞቻችን ከዋናተኛው አትሻሉም፡፡
  • ምን እያልክ ነው?
  • እናንተም ከሌሎች የምዕራባውያን አገሮች ሚኒስትሮች ጋር ብትወዳደሩ እንደምታዋርዱ እርግጥ ነው፡፡
  • ሰውዬ አደብህን ግዛ፡፡
  • ለነገሩ እንደነገርኩዎ ከዚህ በፊትም አዋርዳችሁን ታውቃላችሁ፡፡
  • ምን ይላል ይኼ?
  • አሁን ዋናተኛው ምን እየተባለ እንደሆነ ያውቃሉ አይደል?
  • ምን ተባለ?
  • ሮቤል ዘ ዌል፡፡
  • እ . . .
  • እኔ ደግሞ ለእርስዎ ስም አውጥቼልዎታለሁ፡፡
  • ምን ልትለኝ?
  • ሚኒስትሩ ዘ ዌል!

  [ክቡር ሚኒስትሩ ከአማካሪያቸው ጋር እያወሩ ነው]

  • የተናደዱ ይመስላሉ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • አንዱ እኮ ሰድቦኝ ነው፡፡
  • ለምንድን ነው የሰደበዎት?
  • በዚህ በዋናተኛው የተነሳ ነዋ፡፡
  • ታዲያ እርስዎ ምን አደረጉ?
  • ፖለቲከኞቻችንም ያው ናችሁ ብሎ ነዋ፡፡
  • ምን ብሎ ሰደበዎት?
  • ሚኒስትሩ ዘ ዌል፡፡
  • ኪኪኪ . . .
  • ምን ያስገለፍጥሃል?
  • ስድቡ አስቆኝ ነው፡፡
  • ወይኔ፡፡
  • ወያኔ ነው ያሉኝ?
  • ምን ትቀባጥራለህ?
  • ግን ተዋረድን እኮ፡፡
  • በምንድን ነው የተዋረድነው?
  • በኦሊምፒክ ነዋ፡፡
  • እንዴት ሆኖ?
  • ይኸው በወንዶች አሥር ሺሕ ሜትር አሸነፈን እኮ፡፡
  • ማን ነው ያሸነፈን፡፡
  • ሞ ፋራህ ነዋ፡፡
  • ኃይሌ የት ሄዶ?
  • ክቡር ሚኒስትር እርሱ ውድድር ካቆመ ቆየ እኮ፡፡
  • ቀነኒሳስ?
  • እሱም የመመረጫ ውድድሩ ላይ አቋርጦ ወጣ፡፡
  • ታዲያ ማን ነበር የተሳተፈው?
  • አይ ክቡር ሚኒስትር በደንብ አላቃቸውም፡፡
  • እና ምንድን ነው ችግራቸው?
  • ያው በወንዶች እንደ ድሮ ማሸነፍ ተስኖናል፡፡
  • ለምንድን ነው ማሸነፍ የተሳነን?
  • እኔን’ጃ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ለመሆኑ ሯጮቻችን ልማታዊ ናቸው?
  • አዎን ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • በምን አወቅህ?
  • ሁሉም እኮ ሕንፃ እየገነቡ ነው፡፡
  • አየህ ውስጣቸው ግን ልማታዊ ላይሆን ይችላል፡፡
  • ምን እያሉ ነው?
  • ለመሆኑ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ተጠምቀዋል?
  • እነሱ እኮ ፖለቲከኞች ሳይሆኑ ሯጮች ናቸው፡፡
  • አየህ ችግሩ ይኼ ነው፡፡
  • የምኑ ችግር?
  • የማያሸንፉት ለዛ ነው፡፡
  • እንዴት ሆኖ?
  • አብዮታዊ ዴሞክራሲ ማለት ሌላ ትርጉሙ አሸናፊ ማለት ነው፡፡
  • በለው፡፡
  • እኛ በፓርላማ መቶ ፐርሰንት ያሸነፍነው ለዛ ነው፡፡
  • ይኼ እኮ ታይቶ የማይታወቅ ነው፡፡
  • አየህ አትሌቶቻችንም ታይቶ የማይታወቅ ድል እንዲያገኙ መጠመቅ አለባቸው፡፡
  • በምን?
  • በአብዮታዊ ዴሞክራሲ!

  [ክቡር ሚኒስትሩን የውጭ ጋዜጠኛ ኢንተርቪው ሊያደርጋቸው ቢሯቸው ገባ]

  • ይህንን ቃለ መጠየቅ ለማድረግ ስለተስማሙ አመሰግናለሁ፡፡
  • እኛ የምንደብቀው ነገር ስለሌለ ችግር የለውም፡፡
  • ጥያቄዬን መጀመር እችላለሁ?
  • ቀጥል፡፡
  • በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ሕዝቡ ድምፁን እያሰማ ነው፡፡
  • እንግዲህ አገራችን እያስመዘገበችው ባለው ዕድገት ሕዝቡ ደስተኛ ስለሆነ በየቦታው የደስታ ድምፅ ሊሰማ ይችላል፡፡
  • አልገባዎትም ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ምኑ ነው ያልገባኝ?
  • ሕዝቡ በተለያዩ አካባቢዎች የተቃውሞ ድምፅ እያሰማ ነው?
  • እንዳልኩህ አገሪቱ 11 በመቶ እያደገች ስለሆነ ሕዝብ የእልልታ ድምፅ በየቦታው ያሰማል፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር እኔ ሕዝብ ስለሚያሰማው ተቃውሞ ነው የምጠይቀዎት?
  • በመስኮት እንደምትመለከተው ይኼ ሁሉ የሕንፃ ጫካ የልማቱ መገለጫ ነው፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር የተግባባን አይመስለኝም፡፡
  • እንዴት እንግባባለን?
  • የጠየኩዎትን ጥያቄ ለምን አይመልሱልኝም?
  • መለስኩልህ እኮ፡፡
  • ምን ብለው?
  • እያደግን ነው፡፡
  • አሁን የሕዝብ ችግር እየገባኝ ነው፡፡
  • ምንድን ነው?
  • የሚያዳምጠው የለም!

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  ለካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ስድስት የቦርድ አባላት ተሾሙ

  ይናገር ደሴ (ዶ/ር) የቦርድ ሰብሳቢ ሆነዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

  የትጥቅ  መፍታት ሒደትና የሰላም እንቅፋቶች

  የትግራይ ተራሮች ከጦር መሣሪያ ጩኸት የተገላገሉ ይመስላል፡፡ በየምሽጉ አድፍጠው...

  በሙስና የተጠረጠሩ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ነው

  ብሔራዊ ፀረ ሙስና ኮሚቴ በክልሎችም ሊቋቋም ነው በቅርቡ ተቋቁሞ ወደ...

  የኢንሹራንስ ዘርፉን የሚመራና የሚቆጣጠር ራሱን የቻለ ተቋም የመመሥረት ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ

  የኢንሹራንስ (መድን) ዘርፍን የመቆጣጠርና የመከታተል ኃላፊነት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...

  ዘንድሮ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተናን በበይነ መረብ ለማድረግ ዝግጅት መጀመሩ ተገለጸ

  በሁሉም መደበኛና መደበኛ ባልሆኑ መርሐ ግብሮች የሚመረቁ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር! ቀድሜ ቀጠሮ እንዲያዝልኝ ስጠይቅ እንደገለጽኩት በተቋሙ ሠራተኛ ተወክዬ ነው የመጣሁት። እንዴ? አንተ የእኛ ተቋም ባልደረባ አይደለህም...

  [የተቃዋሚ ፓርቲው ትይዩ ሚኒስትር ክቡር ሚኒስትሩ ጋ ደውለው መንግሥት በሙሰኞች ላይ ለመውሰድ ስላሰበው የሕግ ዕርምጃ ሐሳብ እየተለዋወጡ ነው]

  ሄሎ… ማን ልበል? ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ጤና ይስጥልኝ… ማን ልበል? የእርስዎ ትይዩ ነኝ፡፡  አቤት? ያው ፓርቲዬን ወክዬ የፍትሕ ሚኒስትሩ ትይዩ ነኝ ማለቴ ነው፡፡ ኦ... ገባኝ… ገባኝ...  ትንሽ ግራ አገባሁዎት አይደል? ትይዩ...

   [ክቡር ሚኒስትሩ እራት እየበሉ መንግሥትን በሚተቹ ጋዜጠኞች ላይ እየተወሰደ ያለውን ዕርምጃ የተመለከተ መረጃ እየቀረበላቸው ነው]

  ለጋዜጠኞቹ መንግሥትን እንዲተቹ መረጃ የሚሰጧቸው ታሪካዊ ጠላቶቻችን ናቸው፡፡ እነሱ አይደሉም፡፡ እና የትኞቹ ናቸው? እዚሁ ከተማችን የሚገኙ ምዕራባውያን ናቸው። እንዴት ነው መረጃውን የሚያቀብሏቸው? እራት እያበሉ ነው። ምን? አዎ፣ እራት ግብዣ ይጠሯቸውና መተቸት...