Thursday, March 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊማኅበሩ ከስድስት ሚሊዮን በላይ የተዋልዶና የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት መስጠቱን ገለጸ

ማኅበሩ ከስድስት ሚሊዮን በላይ የተዋልዶና የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት መስጠቱን ገለጸ

ቀን:

–  በለጋሽ ድርጅቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ አቅዷል

የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኅበር ባለፈው ዓመት ብቻ ከስድስት ሚሊዮን በላይ የተዋልዶ ጤናና የቤተሰብ ዕቅድ ላይ ያተኮረ አገልግሎት መስጠቱን፣ ወ/ሮ ገነት መንግሥቱ የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ፡፡

ዋና ሥራ አስኪያጇ የማኅበሩን እንቅስቃሴ አስመልከተው ከሪፖርተር ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፣ ከተሰጡት አገልግሎቶች መካከል አራት ሚሊዮን ያህሉ የተዋልዶ ጤና ሲሆኑ፣ 2.5 ሚሊዮን ደግሞ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎቶች ናቸው፡፡

ማኅበሩ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች፣ በተዋልዶ ጤና ሥር ቅድመና ድኅረ ወሊድ፣ የአፍላ ሕፃናት ጤና ክትትልና እንክብካቤ፣ የተሟላና ደረጃቸውን የጠበቁ የጽንስ ማቋረጥ፣ ኤችአይቪን ጨምሮ በግብረ ሥጋ ግንኙነት አማካይነት የሚተላለፉ በሽታዎች ሕክምና፣ የማሕፀን በር ካንሰር ምርመራና የጤና ባለሙያዎች ሥልጠናና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ በቤተሰብ ዕቅድ ዙሪያም ኮንዶምና ፒልስን ጨምሮ በተለይ ዘላቂ የረዥም ጊዜ የወሊድ ቁጥጥር አገልግሎቶችን ይሰጣል፡፡

በአምስት ዓበይት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የሚያጠነጥን ሰባተኛውን ስትራቴጂክ ዕቅድ ነድፎ ወደ ተግባር የገባ ሲሆን፣ ዕቅዱ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ማለትም 2012 ዓ.ም. ድረስ የሚተገበር ይሆናል፡፡

በስትራቴጂክ ዕቅዱ ከሰፈሩት የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል በለጋሽ ድርጅቶች ላይ ያለውን የገንዘብ ጥገኝነት በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ፣ ተቋማዊ አቅሙን ማጎልበትና ገቢ ማስገኛ የቢዝነስ ስትራቴጂዎችን ቀርጾ መንቀሳቀስ የሚሉ ይገኙበታል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ማኅበሩ ከ1,000 በላይ በጎ ፈቃደኞች፣ ከ640 የሚበልጡ ሠራተኞች፣ ለሴተኛ አዳሪዎች ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ አሥር ምስጢራዊ ክሊኒኮች፣ በመላ የአገሪቱ ክፍሎች አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ 23 የወጣት ማዕከላት፣ 200 ውሎ ገብ አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችና 306 አጋር የግል ክሊኒኮች እንዳሉት ወ/ሮ ገነት ተናግረዋል፡፡

ማኅበሩ ከኔዘርላንድ ኤምባሲ፣ ከፓካርድ ፋውንዴሽን ከሲዲሲ፣ ከተባበሩት መንግሥታት የሥነ ሕዝብ ድርጅት (ኤፍፒኤ) እና ከሌሎች አጋር ድርጀቶች ጋር  ፕሮግራሞቹን በትብብር እየሠራ ይገኛል፡፡

በኢትዮጵያ 50 ዓመታትን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኅበር የተቋቋመው በ1958 ዓ.ም. በቀድሞው ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ውስጥ ነበር፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...