Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትሉሲዎቹ ለሴካፋ ውድድር ዑጋንዳ ገብተዋል

ሉሲዎቹ ለሴካፋ ውድድር ዑጋንዳ ገብተዋል

ቀን:

የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲ) በዑጋንዳ በሚካሄደው የሴካፋ ሴቶች የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ለመሳተፍ ወደ ስፍራው አቅንቷል፡፡

ቅዳሜ ጳጉሜን 5 ቀን 2008 ዓ.ም. 26 ልዑካን ቡድን በመያዝ ወደ ስፍራው ያቀናው ብሔራዊ ቡድኑ፣ የመጀመሪያ ጨዋታውን ረቡዕ መስከረም 4 ቀን 2009 ዓ.ም. ከሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር ሲያደርግ ዓርብ መስከረም 6 ቀን ከታንዛኒያ አቻው ጋር የሚያደርግ ይሆናል፡፡

በቀድሞ የድሬዳዋ እግር ኳስ ክለብ እንስት አሠልጣኝ መሠረት ማኔ የሚመራው የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን 15 ቀናት በድሬዳዋ፣ እንደ 3 ቀናትን አዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ልምምዱን ሲያደርግ ሰንብቷል፡፡ ሃያ ተጫዋቾችን በመያዝ ወደ ስፍራው ያቀኑት ሉሲዎቹ በ23 ተጫዋቾች ድሬዳዋ ላይ ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተው 20 ተጫዋቾች ብቻ ውድድሩ ላይ መካፈል እንደሚችል ሴካፋ ባወጣው ሕግ ሦስት ተጫዋቾች ተቀንሰዋል፡፡

- Advertisement -

ዋና አሠልጣኝ መሠረት ስለዝግጅቱ ስትናገር 15 ቀን ቆይታቸው ለቡድኑ አስፈላጊ ነው የተባሉትን ዝግጅቶች፣ ከአካል ብቃትና ከታክቲካዊ እንቅስቃሴ ጋር ዝግጅት እንዳደረጉ አብራርታለች፡፡ በተጨማሪም ሁለት የአቋም መለኪያ ጨዋታዎችን ከወንድ ቡድኖች ጋር ለማድረግ እንደቻሉም በሁለቱም ጨዋታ ላይ እያንዳንዱ ተጫዋች የነበረው እንቅስቃሴ በጣም ጥሩ እንደነበረ ገልጻለች፡፡

ተጋጣሚዎችም በተመለከተ ከሪፖርተር ለቀረበላት ጥያቄ የታንዛኒያና ኬንያ ቡድኖች መመልከት እንደቻለች ተጠቁማለች፡፡ የሴካፋ የሴቶች እግር ኳስ ውድድር እ.ኤ.አ. 1986 በዛንዚባር አዘጋጅነት የተካሄደ ሲሆን፣ አዘጋጇ አገርም ዋንጫውን እዛው ማስቀረት ችላለች፡፡ ለ20 ዓመት ውድድሩ ሳይካሄድ ቆይቶ አምና ድጋሚ ለማዘጋጀት ቢሞከርም ሊሳካ አልቻለም፡፡

የዘንድሮውን የሴካፋ የሴቶች እግር ኳስ ውድድር ለማዘጋጀት ዑጋንዳ ጥያቄ ስታቀርብ ማንም የተሻማት አገር አልነበረም፡፡ በውድድሩ ሰባት አገሮች ይሳተፋሉ፡፡ በምደብ ሀ ዑጋንዳ፣ ኬንያ ቡሩንዲና ዛንዚባር የሚካፈሉ ሲሆን፣ በምድብ ለ ኢትዮጵያ፣ ታንዛኒያና ሩዋንዳ ተቀምጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ሉሲ) ለ12ኛው የአፍሪካ ሴቶች እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሠራው ስህተት አማካይነት ከምድብ ማጣሪያ ውጪ ሆኖ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ሆኖም ፌዴሬሽኑ ባደረገው ድጋሚ ጥያቄ መሠረት የቶጎ ብሔራዊ ቡድን የገንዘብ ዕጥረት ምክንያት ኢትዮጵያ እንድትገባ ተደርጎ በማጣሪያው ከአልጄሪያ ጋር በተደረገ ጨዋታ 2ለ1 ድምር ውጤት ከውድድር ውጪ መሆኑ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...