Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትየኢትዮ ትሪያል የተራራ ላይ ሩጫ በዓዲግራት የመስቀል አከባበር አካል ሆነ

የኢትዮ ትሪያል የተራራ ላይ ሩጫ በዓዲግራት የመስቀል አከባበር አካል ሆነ

ቀን:

በኢትዮጵያ የሚገኙ የቱሪዝም መስህብ የሆኑ መልክዓ ምድራዊ ቦታዎችን ለማስተዋወቅ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ለማስመዝገብ የተለያዩ ዓመታዊ የሩጫ ውድድሮችና የባህል ዝግጅቶች በቅርቡ እየተለመዱ መጥተዋል፡፡

በተለይ ከቅርብ ጊዜ በኋላ በአትሌቲክሱ ዘርፍ እየታየ ያለው እንቅስቃሴ ተጠቃሽ ነው፡፡ የተራራ ላይ ሩጫን በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች በማስተናገድ የሚታወቀው ሪያ ኢትዮጵያ ስፖርትስ በዓመት ውስጥ ሊያከናወናቸው በዕቅድ ከያዛቸው አንዱ የሆነው የዓዲግራት ተራራ ላይ ሩጫ በከተማ ለሚከበረው የመስቀለ ባህል አከባበር ዋና አካል መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኢትዮ ትሪያል የተራራ ላይ ሩጫ በሰሜን ተራሮች ውድድሮችን ሲያዘጋጅ የመጀመሪያው ሲሆን፣ በዚህም ውድድር ከ80 በላይ ታዋቂ አትሌቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ከ600 በላይ የከተማው ነዋሪንም አሳትፏል፡፡ በሰሜን ተራሮች ላይ የተራራ ላይ ሩጫ ለማካሄድ ያቀደው ሪያ ዓዲግራትም አንዷ ቦታ በመሆንዋ ቀደም ብሎ በባለሞያዎች ጥናት እንደተደረገባት የሪያ ኢትዮጵያ ስፖርትስ ቦርድ ሰብሳቢ አትሌት ገብረ እግዚአብሔር ገብረ ማርያም ለሪፖርተር አብራርቷል፡፡ የከተማው አስተዳደር ከዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ያካሄደው ውድድሩ በ12 ኪሎ ሜትር ርቀትም ተወዳዳሪዎችን አሳትፏል፡፡

- Advertisement -

ሪያ አራት ውድድሮችን በዓመት ውስጥ ያካሂዳል፡፡ እነዚህም በአብዳታ ሻላ ሐይቆች፣ በወንጪ ሐይቆችና በዓዲግራት የተራራ ላይ ሩጫ እንዲሁም በላንጋኖ ሐይቅ ላይ የሚደረገው የትራይትሎን ውድድር ናቸው፡፡

መስከረም 15 ቀን 2009 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ በተደረገው የዓዲግራት ተራራ ላይ ሩጫ በታዋቂ አትሌቶች ውድድር በወንዶች ደስታ ብርሃኑ ከትግራይ ፖሊስ፣ ደመቀ ካሳሁን ከትራንስ ኢትዮጵያ እንዲሁም ሐጐስ አረጋዊ ከፖሊስ ዋልታ እንደየ ደረጃቸው ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ በመያዝ ሲያጠናቅቁ ከ10 ሺሕ እስከ 5,000 ሺሕ ብር ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

በሴቶች ፀዳል ገብረ ጻዲቅ በግል ከአዲስ አበባ፣ በለጡ ዓለማየሁ ከትራንስ ኢትዮጵያና ብርዛፍ ታረቅ ከጉና በተመሳሳይ ሁኔታ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ሦስተኛ በመያዝ ከ10,000 እስከ 5,000 ብር ተሸላሚ መሆን ችለዋል፡፡

የኢትዮ ትሪያል የተራራ ላይ ሩጫ ዘንድሮ ዓዲግራት ላይ መክተሙና ከመስቀል ባህል አንድ ቀን ቀደም ብሎ መደረጉ በከተማዋ የእንግዶች ትኩረት ለመሳብ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው አትሌት ገብረ እግዚአብሔር ተናግሯል፡፡ በቀጣይም እንጦጦ ላይ ውድድር ለማድረግ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀም አትሌቱ አክሏል፡፡

ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. ለሦስተኛ ጊዜ በአብያታ ሻላ ሐይቆችና ብሔራዊ ፓርክ ላይ የተደረገው የተራራ ላይ ሩጫ ‹‹በዱር እንሩጥ›› በሚል መሪ ቃል ማዘጋጀቱ ይታወሳል፡፡ በዚህም መሠረት በውድድሩ በርካታ ከውጭ አገር የመጡ የተለያዩ ዜጎችን ማሳተፍ መቻሉም ይታወቃል፡፡

ውድድሩ በአብያታ ሻላ ሐይቆችና ብሔራዊ ፓርክ ከተደቀነበት የመድረቅና የመጥፋት አደጋ ለመከላከል ያለመ ነው፡፡ የስፖርት ቱሪዝምን በአገሪቱ ለማስፋፋት አልሞ የተነሳ መሆኑ የሪያ ኢትዮጵያ ስፖርትስ ቦርድ ሰብሳቢ አብራርቷል፡፡

ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀውም የዓዲግራት ተራራ ላይ ሩጫ በቀጣይ የውጭ አገር ተሳታፊዎች በብዛት ለማሳተፍ እንደተዘጋጀና በቱሪዝም የራሱን አስተዋጽኦ ለማድረግ እንደሚሠራም ገልጿል፡፡          

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...