Monday, December 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  ክቡር ሚኒስትር

  [ክቡር ሚኒስትሩ ከአማካሪያቸው ጋር እያወሩ ነው]

  • ጠፍተዋል ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እንዴት አልጠፋ?
  • የት ሄደው ነው?
  • በአገር ውስጥ የለህም እንዴ?
  • ኧረ አለሁ፡፡
  • ቲቪ አትከታተልም?
  • ሰሞኑን መብራት ስለሌለ አይቼ አላውቅም፡፡
  • አንተ እኮ አፍራሽ መሆንህን አውቃለሁ፡፡
  • ምን አደረግኩ?
  • መብራት ያለበት ቦታ አትሄድም?
  • አይ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ምን ሆንክ?
  • መብራት ጠፍቶብኛል ስል አፍራሽ እያሉኝ እንዴት ልንግባባ እንችላለን?
  • ታዲያ ታዳሽ እንድልህ ጠብቀህ ነው?
  • ምንድን ነው እሱ?
  • የስብሰባችን ፍሬ ነዋ፡፡
  • የምን ስብሰባ?
  • ሰሞኑን የጠፋሁት ስብሰባ ገብቼ ነው፡፡
  • ማለት?
  • ለመታደስ ወስነን ነው የወጣነው፡፡
  • መታደስ ሲሉ?
  • ይኸውልህ አገሪቱ በአጠቃላይ መታደስ አለባት፡፡
  • እ…
  • ግን ቢያንስ ከራሳችን መጀመር አለብን፡፡
  • መታደስ ማለት ምን ማለት ነው?
  • ሁሉን ነገር በአዲስ መተካት፡፡
  • እሺ፡፡
  • እና መታደስ በእኔ ይጀምራል፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር በአዲስ ሰው ሊቀየሩ ነው እንዴ?
  • የለም የለም፡፡
  • መታደስ ከእኔ ይጀምራል ሲሉኝ ነዋ፡፡
  • እኮ ለምሳሌ የቢሮዬ ቀለም መቀየር አለበት፡፡
  • ምን?
  • ምንጣፌም መቀየር አለበት፡፡
  • ስድስት ወር አልሞላውም እኮ፡፡
  • ግን አዲስ አይደለም፡፡
  • እ…
  • የቢሮዬ ፈርኒቸርም ሙሉ ለሙሉ መቀየር አለበት፡፡
  • ኧረ ክቡር ሚኒስትር?
  • የእኔ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የመሥሪያ ቤቱ መቀየር አለበት፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር የገባዎት አልመሰለኝም፡፡
  • ምኑ?
  • መታደስ ማለት፡፡
  • ደግሞ ፖለቲካውን ልታስተምረኝ ነው?
  • የተሳሳቱ ስለመሰለኝ ነው፡፡
  • አልጨረስኩም እኮ፡፡
  • እሺ፡፡
  • መኪናዬም የ2017 ሞዴል መሆን አለበት፡፡
  • ምን?
  • ስልኬም አይፎን 7 ፕላስ ይሁንልኝ፡፡
  • ካሉ ምን ይደረጋል?
  • ነገርኩህ በተሃድሶ ሁሉም ነገር መታደስ አለበት፡፡
  • እርስዎ እንዳሉ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ስለዚህ ሁሉም ነገር በአዲስ ይለወጥ፡፡
  • ጨረታ ይውጣ?
  • አያስፈልግም፡፡
  • ለምን?
  • ሕዝብ ሰልችቶታል፡፡
  • ምኑ?
  • ቢሮክራሲው!

  [ክቡር ሚኒስትሩ ለምሳ ቤት ገብተው ከሚስታቸው ጋር እያወሩ ነው]

  • ዛሬ ቀጠሮ የለህም እንዴ?
  • የምን ቀጠሮ?
  • ለምሳ መጣህ ብዬ ነው፡፡
  • በቃ ተሰብስበን ጨረስን፡፡
  • ለዚያ ነው የመጣኸው?
  • መታደስ አለብን፡፡
  • ምን?
  • በቃ ዋናው መፍትሔ መታደስ ነው፡፡
  • ሰውዬ ይኼን እዚያው ስብሰባህ ላይ አውራ፡፡
  • አይ ቤተሰባችንም መታደስ አለበት፡፡
  • ስማ ልጆቼን ፖለቲካ ውስጥ እንዲገቡ አልፈልግም፡፡
  • ምን ነካሽ? ፖለቲካና ሕይወት እኮ የተሳሰሩ ናቸው፡፡
  • ነገርኩህ ሰውዬ፡፡
  • ለመሆኑ የቤቱን ቀለም አይተሽዋል?
  • አዎ ምን ሆነ?
  • እስቲ እይው፡፡
  • አየሁት እኮ ምንም አልሆነም፡፡
  • አዲስ ቀለም መቀባት አለበት፡፡
  • ከተቀባ እኮ ስድስት ወር አልሞላውም፡፡
  • ነገርኩሽ ይኼ ሶፋ፣ ዳይኒንግ ቴብሉ ምናምን ይቀየር፡፡
  • አብደሃል እንዴ?
  • ምን ሆንሽ?
  • ባለፈው ለሱቅ ፈርኒቸር ሳስጭን እኮ ነው የቤቱ ዕቃ የተገዛው፡፡
  • ቢሆንስ?
  • ሰባት ወሩ ነው ገና፡፡
  • መቀየር አለበት፡፡
  • እ…
  • ግቢውንስ አይተሽዋል?
  • አንደኛውኑ ቤቱ ፈርሶ ይሠራ ለምን አትልም?
  • እርሱም ጥሩ ሐሳብ ነው፡፡
  • ምን?
  • ቤቱ ለምን…
  • ምን?
  • ሙሉ ለሙሉ አይታደስም?
  • ምን ሆኖ?
  • የስብሰባችን ውሳኔ መታደስ አለብን የሚል ነው፡፡
  • መቼም አይገባህም አይደል?
  • ምኑ?
  • ሁሉም ነገር፡፡
  • ማለት?
  • ይታደስ የተባለው እኮ ሌላ ነገር ነው፡፡
  • ማለት?
  • ፖሊሲው፣ አሠራሩ፣ ቢሮክራሲው እኮ ነው ይታደስ የተባለው፡፡
  • ግን እኛም መታደስ አለብን፡፡
  • ከእናንተ የሚታደሰው ዕቃችሁ አይደለማ፡፡
  • ታዲያ ምናችን ነው የሚታደሰው?
  • አዕምሯችሁ!

  [የክቡር ሚኒስትሩ ሾፌር ከፍቶታል]

  • ምን ሆነሃል?
  • ምን አደረግኩዎት ክቡር ሚኒስትር?
  • እኮ ምን ሆንክ?
  • እኔ ለእርስዎ ታዛዥ አይደለሁም?
  • ምንድን ነው የምታወራው?
  • በጠዋት ቢጠሩኝ በሌሊት፣ ቅዳሜ ቢሉ እሑድ እምቢ ብዬ አውቃለሁ?
  • ሰውዬ ጤነኛ ነህ?
  • እኮ የድሃን ጉሮሮ ዘግተው እንቅልፍ ይወስድዎታል?
  • ምንድን ነው የምትቀባጥረው?
  • ከሥራ ሊያባርሩኝ መሆኑን ሰማሁ፡፡
  • ማን ነው የነገረህ?
  • የ2017 ሞዴል መኪና ሊገዙ አይደል?
  • አዎ ልገዛ ነው፡፡
  • የ2017 ሞዴል መኪና ከሆነ ያለሾፌር እንደሚሄድ የቲቪ ማስታወቂያ አይቻለሁ፡፡
  • ኪኪኪ…
  • ምን ያስቅዎታል?
  • ያለሾፌር የሚሄድ መኪና ቢሆን እኔ መቼ ይገባኛል?
  • ምኑ?
  • ቴክኖሎጂው!

  [ክቡር ሚኒስትሩ በቅርቡ ካሠሩት ሕንፃ ማኔጀር ጋር እያወሩ ነው]

  • እንዴት ነዎት ክቡር ሚኒስትር?
  • አንተ ስንቴ ነው የምነግርህ?
  • ምኑን ክቡር ሚኒስትር?
  • እዚህ ክቡር ሚኒስትር አትበለኝ አላልኩህም?
  • ማን ልበልዎት ታዲያ?
  • ክቡር ኢንቨስተር፡፡
  • እሺ ክቡር ኢንቨስተር፡፡
  • ስማ ሕንፃው መታደስ አለበት፡፡
  • አዲስ እኮ ነው፡፡
  • በቃ ተሃድሶ ማድረግ እንዳለብን ስለተስማማን፣ በአስቸኳይ ሕንፃው ይታደስ፡፡
  • እሺ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር አትበለኝ አልኩህ እኮ?
  • መታደስ ምናምን ሲሉ ረስቼው ነው፡፡
  • ስለዚህ ተከራዮቹ የቢሯቸውን ቀለም እንዲቀይሩ ንገራቸው፡፡
  • ችግር የለውም፡፡
  • የሚፈልጉትን ቀለም መምረጥ ይችላሉ፤ የማቀርበው ግን እኔ ነኝ፡፡
  • ከየት?
  • ከራሴ ፋብሪካ ነዋ፡፡
  • እሺ እንዳሉ፡፡
  • ፓርቲሽኖቻቸውን ከፈለጉ በአልሙኒየም፣ ከፈለጉ በፒቪሲ፡፡
  • አስተላልፋልሁ ጌታዬ፡፡
  • አቅራቢው ግን እኔ ነኝ፡፡
  • ከየት?
  • ኢምፖርት አደርጋለሁ አይደል እንዴ?
  • እሺ፡፡
  • ፈርኒቸሮቻቸውንም መምረጥ ይችላሉ፣ አቅራቢው ግን…
  • እርስዋ ነዎት!

  [ለክቡር ሚኒስትሩ አንድ ሚኒስትር ደወሉላቸው]

  • ኧረ ተው ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ምን አደረግኩ ደግሞ?
  • ይኸው ከተማው ውስጥ የፈርኒቸር ቢሉ የአልሙኒየም ግዥ እያጧጧፉት ነው አሉ፡፡
  • ምን ችግር አለው?
  • በቃ በአደባባይ አደረጉት?
  • በሰጣችሁኝ አቅጣጫ እኮ ነው እየተንቀሳቀስኩ ያለሁት፡፡
  • የምን አቅጣጫ?
  • የተሃድሶ አቅጣጫ፡፡
  • አልገባኝም ክቡር ሚኒስትር?
  • በቃ ቤቴም፣ ቢሮዬም፣ ሕንፃዬም እየታደሱ ናቸው፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር ለእርስዎ መታደስ አይደለም መፍትሔው?
  • እና ምንድን ነው?
  • መወገድ!

  [የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ቢሯቸው ገባ]

  • ክቡር ሚኒስትር ሰሙ እንዴ?
  • ስለምኑ?
  • ስለሹም ሽሩ?
  • እኔ ሳልሰማ አንተ እንዴት ሰማህ?
  • አይ እንዳይሰሙ ተፈልጐ ይሆናላ፡፡
  • ማለት?
  • ቴክኖክራቶች ሥልጣን ላይ ሊወጡ ነው አሉ፡፡
  • ይውጡ ምን ችግር አለው?
  • ከዛም ባለፈ ሌላ የሰማሁት ነገር አለ፡፡
  • ምን ሰማህ?
  • ከዳያስፖራም አገር ለመምራት የሚመጡ አሉ ተብሏል፡፡
  • ምን ችግር አለው ታዲያ?
  • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
  • እኛም እንሆናለና፡፡
  • ምን?
  • ዳያስፖራ!

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  ለካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ስድስት የቦርድ አባላት ተሾሙ

  ይናገር ደሴ (ዶ/ር) የቦርድ ሰብሳቢ ሆነዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

  የትጥቅ  መፍታት ሒደትና የሰላም እንቅፋቶች

  የትግራይ ተራሮች ከጦር መሣሪያ ጩኸት የተገላገሉ ይመስላል፡፡ በየምሽጉ አድፍጠው...

  በሙስና የተጠረጠሩ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ነው

  ብሔራዊ ፀረ ሙስና ኮሚቴ በክልሎችም ሊቋቋም ነው በቅርቡ ተቋቁሞ ወደ...

  የኢንሹራንስ ዘርፉን የሚመራና የሚቆጣጠር ራሱን የቻለ ተቋም የመመሥረት ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ

  የኢንሹራንስ (መድን) ዘርፍን የመቆጣጠርና የመከታተል ኃላፊነት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...

  ዘንድሮ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተናን በበይነ መረብ ለማድረግ ዝግጅት መጀመሩ ተገለጸ

  በሁሉም መደበኛና መደበኛ ባልሆኑ መርሐ ግብሮች የሚመረቁ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር! ቀድሜ ቀጠሮ እንዲያዝልኝ ስጠይቅ እንደገለጽኩት በተቋሙ ሠራተኛ ተወክዬ ነው የመጣሁት። እንዴ? አንተ የእኛ ተቋም ባልደረባ አይደለህም...

  [የተቃዋሚ ፓርቲው ትይዩ ሚኒስትር ክቡር ሚኒስትሩ ጋ ደውለው መንግሥት በሙሰኞች ላይ ለመውሰድ ስላሰበው የሕግ ዕርምጃ ሐሳብ እየተለዋወጡ ነው]

  ሄሎ… ማን ልበል? ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ጤና ይስጥልኝ… ማን ልበል? የእርስዎ ትይዩ ነኝ፡፡  አቤት? ያው ፓርቲዬን ወክዬ የፍትሕ ሚኒስትሩ ትይዩ ነኝ ማለቴ ነው፡፡ ኦ... ገባኝ… ገባኝ...  ትንሽ ግራ አገባሁዎት አይደል? ትይዩ...

   [ክቡር ሚኒስትሩ እራት እየበሉ መንግሥትን በሚተቹ ጋዜጠኞች ላይ እየተወሰደ ያለውን ዕርምጃ የተመለከተ መረጃ እየቀረበላቸው ነው]

  ለጋዜጠኞቹ መንግሥትን እንዲተቹ መረጃ የሚሰጧቸው ታሪካዊ ጠላቶቻችን ናቸው፡፡ እነሱ አይደሉም፡፡ እና የትኞቹ ናቸው? እዚሁ ከተማችን የሚገኙ ምዕራባውያን ናቸው። እንዴት ነው መረጃውን የሚያቀብሏቸው? እራት እያበሉ ነው። ምን? አዎ፣ እራት ግብዣ ይጠሯቸውና መተቸት...