Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት አዲስ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አዋቀሩ

የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት አዲስ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አዋቀሩ

ቀን:

መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም. በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ቅጥር ግቢ  ውስጥ በተከናወነ ጠቅላላ ጉባዔ የሰማያዊ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አዲስ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አዋቀሩ፡፡

ፕሬዚዳንቱ አዲሱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴያቸውን ጥቅምት 13 ቀን 2009 ዓ.ም. በተካሄደ የፓርቲው ስብሰባ ለፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት አቅርበው አፀድቀዋል፡፡

በዚህም መሠረት ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ምክትል ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ፣ ኢንጂነር ስሜነህ ፀሐይ የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ፣ አቶ ሰሎሞን ተሰማ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣ አቶ አበበ አካሉ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ፣ አቶ ነአሮን ሰይፉ የጥናትና ስትራቴጂ ኃላፊ፣ ወ/ሮ ቅድስት አሰበ የሕግ ጉዳይ ኃላፊ፣ አቶ ሰዒድ ኢብራሒም የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ፣ ኢንጂነር ዳዊት ዋለልኝ የአባላት መረጃና ደኅንነት ኃላፊ፣ ወ/ሪት ብሌን መስፍን የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ፣ እንዲሁም ወጣት አንተነህ ተረፈ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ በመሆን መመረጣቸውን ፓርቲው ለሪፖርተር በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው የተመረጡት የፓርቲው አመራሮችን ለመምረጥ የቀረቡት መመዘኛዎች ደግሞ ለሰላማዊ ትግሉና የኢትዮጵያ ሕዝብን የሥልጣን ባለቤት ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነትና ለትግሉ ቅድሚያ መስጠት፣ የፓርቲውን ደንብና ፕሮግራም ለማክበርና ፓርቲው ከገባበት ችግር ለማውጣት ያላቸው ፍላጐት፣ ለትብብርና ለውህደት ክፍት አመለካከት ያላቸው መሆንና በአጠቃላይ አንድ ትልቅ ተፎካካሪ ፓርቲ በመፍጠር ሒደት ያላቸው እምነት የሚሉት ይጠቀሳሉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የትምህርት ዝግጅታቸውና የሙያ ብቃታቸው፣ የተሻለ ሰው ቢመጣ የኃላፊነት ቦታን በፈቃደኝነት እስከ መልቀቅ የሚደርስ ቅንነት ያላቸው መሆኑ የሚታወቁና ላለፉት በርካታ ዓመታት በነፃነት ትግሉ ሜዳ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ መጫወታቸው፣ በቅንጅት ለመሥራት ያላቸው እምነት፣ እንዲሁም የሥራ አስፈጻሚ ለመሆን ያሳዩት ሙሉ ፍላጐትም እንዲሁ ከመመዘኛ መሥፈርቶቹ መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔውን መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም. ማከናወኑን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን፣ በዕለቱም ፕሬዚዳንትና የተጓደሉ የብሔራዊ ምክር ቤት አባላትን መርጧል፡፡

የቀድሞው የፓርቲው ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ግን፣ ‹‹የሰማያዊ ፓርቲ ደንቡ በሚያዘው መሠረት ጠቅላላ ጉባዔ አልተካሄደም፤›› ማለታቸውን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...