Saturday, November 26, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  ክቡር ሚኒስትር

   [ክቡር ሚኒስትሩ በጣም ተናደው የቤት ሠራተኛቸውን አስጠሯት]

  • አንቺ ምን ሆነሻል?
  • ምን ሆንኩ ጋሼ?
  • ለምንድን ነው ሸሚዜን ያልተኮሽው?
  • ሥራ ይዤ ነው ጋሼ?
  • ማታ አይደል እንዴ እንድትተኩሽው የነገርኩሽ?
  • እንጀራ ስጋግር ነበር፡፡
  • እና ምን ለብሼ ልሂድ?
  • አሁን እተኩስልዎታለሁ ጋሼ፡፡
  • በምንድን ነው የምትተኩሽው?
  • በካውያ ነዋ፡፡
  • የከሰል ካውያ አለን እንዴ?
  • ኧረ በኤሌክትሪክ ካውያ ነው የምተኩሰው፡፡
  • መብራት እኮ የለም፡፡
  • እነዚህ መብራት ኃይሎች ደግሞ ጀመራቸው፡፡
  • ያልተጠየቅሽውን አትቀባጥሪ፡፡
  • መቼ ነው እነሱ ግን የሚሻሻሉት?
  • ስለእነሱ አይመለከተኝም፡፡
  • እንዴት አይመለከትዎትም?
  • እኔ ምን አገባኝ?
  • እረሱት እንዴ ጋሼ?
  • ምኑን?
  • ሚኒስትር መሆንዎትን፡፡
  • እ…
  • ይኼ እኮ የመንግሥት ሥራ ነው፡፡
  • ምን እያልሽ ነው?
  • እኔ እኮ እርስዎ ሚኒስትር ሲሆኑ ተገላገልን ብዬ ነበር፡፡
  • ከምን?
  • ከዚህ መከራ ነዋ፡፡
  • ከየትኛው መከራ?
  • ዛሬ ፊልም ሊያመልጠኝ ነው ማለት ነው?
  • የምን ፊልም?
  • ዛራና ቻንድራ፡፡
  • አንቺ እሱ ነው የሚያስጨንቅሽ አይደል?
  • ስለሌላ ነገርማ እንዳልጨነቅ አዋጁ ከልክሎኛል፡፡
  • የትኛው አዋጅ?
  • ጋሼ እኔ ፖለቲካ አያስወሩኝ፡፡
  • የምን ፖለቲካ ነው?
  • ያመለጠኝን ፊልም በፌስቡክ እንኳን እንዳላይ እሱም ተዘግቷል፡፡
  • በፌስቡክ ፊልም ታያለሽ?
  • እኔማ እርስዎን ተስፋ አድርጌ ነበር፡፡
  • እንዴት?
  • ጋሼ እርስዎ ሚኒስትር ሲሆኑ ብዙ ነገር ጠብቄ ነበር፡፡
  • ማለት?
  • መብራት የሚጠፋብን አልመሰለኝም ነበር፡፡
  • ሌላስ?
  • ውኃም እናጣለን ብዬ አላስብም፡፡
  • እሺ፡፡
  • ጋሼ የአክስቴ ልጅ እኮ የቀድሞ ሚኒስትር ቤት ነው የምትሠራው፡፡
  • እና?
  • በቃ ዓረብ አገር ያሉ ዘመዶቻችን ጋ ስልክ እንደፈለግን ነበር የምንደውለው?
  • እ…
  • እዚህም እንደዛ ይሆናል ብዬ አስቤ ነበር፡፡
  • እንደዛ ብታደርጊ የሚከተልሽን ታውቂያለሽ፡፡
  • ምንድን ነው የሚከተለኝ?
  • ጣትሽን ነው የምቆርጠው፡፡
  • ጋሼ መቼም እኔ ላይ አይጨክኑም?
  • ነገርኩሽ ሴትዮ፡፡
  • እና ጋሼ ሌሎቹ ሚኒስትሮች ቤት የሚገኘው ጥቅም እዚህ አይገኝም እያሉኝ ነው?
  • እኔ እንደዚህ ዓይነት ነገር ውስጥ አልገባም፡፡
  • እኔ የምለው ጋሼ፡፡
  • ምንድን ነው?
  • ሰዎቹ እርስዎን አልተቀበሉዎትም እንዴ?
  • እንደ ምን?
  • እንደ ሚኒስትር!

  [ክቡር ሚኒስትሩ ቢሮ ሲገቡ አማካሪያቸውን አስጠሩት]

  • አቤት ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • አንዳንድ ነገሮች ላይ መወያየት አለብን፡፡
  • እሺ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ያው እኔ ብዙ ጊዜ ምርምሩ ላይ ነው የቆየሁት፡፡
  • አውቃለሁ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እና እዚህ መሥሪያ ቤት ስላለው የአስተዳደር ሥራ ማወቅ እፈልጋለሁ፡፡
  • ምን ልንገርዎት ክቡር ሚኒስትር?
  • መሥሪያ ቤቱ ውስጥ ያለው ዋሻ ምንድን ነው?
  • የምን ዋሻ ነው?
  • መሥሪያ ቤቱ በየፍሎሩ በፓርቲሽን የተሠራ ዋሻ አለው፡፡
  • እ…
  • ለምንድን ነው ሁሉም በፓርቲሽን ተከፋፍሎ የራሱን ቢሮ የያዘው?
  • ያው…
  • አውቃለሁ ለምን እንደዛ እንደሆነ፡፡
  • ማለት?
  • ሁሉም ጉቦ መቀባበሉ እንዲመቸው ነው፡፡
  • እ…
  • የመሥሪያ ቤቱ ዋና ዓላማ ሕዝቡን ማገልገል አይደል እንዴ?
  • በሚገባ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ስለዚህ ለተገልጋዮች የሚመች ቢሮ ነው ሊኖረን የሚገባው፡፡
  • የሚመች ሲሉ?
  • በቃ ተገልጋዮች በየቢሮው መግባት ሳይጠበቅባቸው በአንድ ፍሎር ላይ ተገልግለው መሄድ አለባቸው፡፡
  • ምን እያሉ ነው?
  • ዋሻዎቹ መፍረስ አለባቸው፡፡
  • እ…
  • አዎ ሁሉም ፓርቲሽኖች ፈርሰው ልቅ ቢሮ ይሁን፡፡
  • እርስዎ ካሉ እሺ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እሱ ብቻ አይደለም፡፡
  • ሌላ ምን አለ?
  • ካሜራ መገጠም አለበት፡፡
  • እ…
  • እያንዳንዱ ሠራተኛ እንዴት አገልግሎት እንደሚሰጥ በካሜራ ይታያል፡፡
  • እንዳሉ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ስለዚህ ጉቦ መቀባበልም ይቀራል ማለት ነው፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር ጉቦን ለማስቀረት ስንቱ ቦታ ካሜራ ይተከላል?
  • ሁሉም ቦታ፡፡
  • እሱማ አይቻልም፡፡
  • ለምን አይቻልም?
  • አብዛኛው ድርድር የሚካሄደው እኮ በየመጠጥ ቤቱና በየሆቴሉ ነው፡፡
  • እ…
  • እና ከቢሮ ውጪ በርካታ ድርድር ይደረጋል፡፡
  • ለእሱም ዘዴ ይፈለግለታል፡፡
  • እሺ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ብቻ አሁን በአስቸኳይ ፓርቲሽኑ ይፍረስ፡፡
  • በአስቸኳይማ መፍረስ አይችልም፡፡
  • ለምን?
  • ጨረታ መውጣት አለበት፡፡
  • የምን ጨረታ?
  • የማፍረስ!

  [የቀድሞ ክቡር ሚኒስትር አዲሱ ሚኒስትር በመሥሪያ ቤቱ ውስጥ ሊያመጡ ያቀዱትን ለውጥ ሰምተው ስልክ ደወሉላቸው]

  • ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ሰላም ማን ልበል?
  • እንዴት ነው አዲሱ ሥራ?
  • ጥሩ ነው፣ ማን ልበል?
  • የቀድሞ ሚኒስትር ነኝ፡፡
  • እንዴት ነዎት የቀድሞ ክቡር ሚኒስትር?
  • በጣም ደህና ነኝ፡፡
  • ምን እያደረጉ ነው አሁን?
  • እኔማ ኢንቨስተር ልሁን ወይስ አምባሳደር በሚለው ሐሳብ ግራ እየተጋባሁ ነው፡፡
  • እ…
  • ኢንቨስተር ብሆን ጥሩ እንደምሠራ አውቃለሁ፡፡
  • እሺ፡፡
  • አምባሳደርም ብሆን ሁሉ ወጪዬ በመንግሥት ተችሎ ስለምኖር ለእኔ ዕረፍት ነው፡፡
  • እ…
  • ግን አምባሳደር ብሆን የኢንቨስተር ሥራዬን ሊጎዳው ይችላል ብዬ ስላሰብኩ ግራ ተጋብቻለሁ፡፡
  • በጣም ያሳዝናል፡፡
  • ምኑ ነው የሚያሳዝነው?
  • አሁንም ስለራስዎት ነው የሚያስቡት?
  • ታዲያ ስለማን ላስብ?
  • ከቦታዎት ያስነሳዎት እኮ ይኼ አስተሳሰብዎ ነው፡፡
  • እኔ ከቦታዬ ብነሳም መውደቂያዬን አሳምሬ ነው፡፡
  • እ…
  • መጀመሪያዬ መቀመጫዬን አለች ስንጀሮ ሲባል አልሰሙም?
  • አሁንም እንደዚህ ዓይነት የወረደ አስተሳሰብ ነው ያለዎት ማለት ነው?
  • ለማንኛውም አሁን የደወልኩት ልመክርዎት ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • የምን ምክር?
  • መሥሪያ ቤቱ ውስጥ ሊያመጡ ያሰቡትን ለውጥ ሰምቻለሁ፡፡
  • እና ምን ይሁን?
  • ብዙ ባይለፉ መልካም ነው፡፡
  • ለምን?
  • ፓርቲሽን በማፍረስ ለውጥ ማምጣት አይቻልም፡፡
  • እርሱን ለእኔ ተውት፡፡
  • እና እርስዎም ቢያስቡበት ጥሩ ነው፡፡
  • ምንድን ነው የማስብበት?
  • ሹመትዎን ይጠቀሙበት፡፡
  • የተሾምኩት ለእኔ ጥቅም አይደለም፡፡
  • ታዲያ ለማን ነው?
  • ለአገር!

  [ክቡር ሚኒስትሩ ከሾፌራቸው ጋር ወደ ቤት እየሄዱ ነው]

  • የደካከሙ ይመስላሉ ክቡር ሚኒስትር?
  • አዎን ትንሽ ደክሞኛል፡፡
  • ታላቁን ሩጫ ሮጡ እንዴ?
  • አይ አልሮጥኩም፡፡
  • ዊኬንድ ላይ ኳስ አዩ?
  • እኔ እንደዚህ ዓይነት ነገር አይመቸኝም፡፡
  • የቀድሞ ክቡር ሚኒስትር እኮ ኳስ ሕይወታቸው ነበር፡፡
  • እንዴት?
  • ስብሰባ አቋርጠው ራሱ ደውለው ውጤት ይጠይቁኝ ነበር፡፡
  • ለዚህ ነዋ ቤቱን እንደዚህ ያበሰበሱት፡፡
  • ለነገሩ እኔም አልወዳቸውም ነበር፡፡
  • ለምን?
  • ራስ ወዳድ ናቸው፡፡
  • ማለት?
  • ራሴ ብቻ በልቼ ልሙት ነው የሚሉት፡፡
  • አልገባኝም፡፡
  • ስንትና ስንት ደላላና ባለሀብት ነው ያገናኘኋቸው፡፡
  • እና፡፡
  • በቃ ይኼው ስንት ፎቅና ፋብሪካ ለራሳቸው ሠርተው፣ እኔ ጎጆ እንኳን የለኝም፡፡
  • እ…
  • መቼም ክቡር ሚኒስትር እርስዎ እንደ እሳቸው አይደሉም?
  • ማለት?
  • እርስዎም ተጠቅመው እኔን ይጠቅሙኛል፡፡
  • ምን?
  • በርካታ ደላላና ባለሀብት አውቃለሁ፡፡
  • እና?
  • የሚኒስትር ጥቅሙ ምን ሆነና?
  • እ…
  • ደመወዝዎት እኮ ትታወቃለች፡፡
  • ምን?
  • ቶሎ ብለው ፎቅዎትን ይሥሩ ግን…
  • ግን ምን?
  • እኔንም ያስቡኝ፡፡
  • አንተ መባረር አለብህ፡፡
  • እ…
  • ከእኔ ጋር መሥራት አትችልም፡፡
  • ምን አደረግኩ?
  • የእኔ ሾፌር መሆን አትችልም፡፡
  • የእርስዎስ ካልሆንኩ የእርሳቸው መሆን እችላለሁ፡፡
  • የማን?
  • የቀድሞው ክቡር ሚኒስትር!

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  ሰርጌ ላቭሮቭ ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ በአዲስ አበባ በሰጡት መግለጫ ምዕራባውያንን አጣጣሉ 

  የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ለአፍሪካ አገሮች ላደረጉት...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...

  አሜሪካ ሕወሓትን በማሳመንና በመጫን በሰላም ሒደቱ ትልቅ ሚና መጫወቷን የኢትዮጵያ ዋና ተደራዳሪ አስታወቁ

  የተመድና የአውሮፓ ኅብረት አበርክቶ አሉታዊ እንደነበር ጠቁመዋል በመንግሥትና በሕወሓት መካከል...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን 55 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ወሰነ

  የአዋሽ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ዛሬ ህዳር 17 ቀን 2015...

  ከብሔራዊ ባንክ እውቅና ያገኘው ፔይሊንክ አክሲዮን ማህበር ምሥረታውን አካሄደ

  ከገንዘብ ንክኪ ነፃ የሆነ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ለመተግበር ያቀደው...

  የተወሳሰበው ሰላም የማስፈን ሒደት

  የደቡብ አፍሪካ የሰላም ስምምነት ተፈርሞ ብዙም ሳይዘገይ የኬንያው ቀጣይ...

  በግብርና ዘርፍ ለመሰማራት ያቀደው ድርዜማ

  ከፋይናንስ ተቋማት ውጪ ባሉ የተለያዩ የቢዝነስ ዘርፎች በአክሲዮን ኩባንያ...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  [የተቃዋሚ ፓርቲው ትይዩ ሚኒስትር ክቡር ሚኒስትሩ ጋ ደውለው መንግሥት በሙሰኞች ላይ ለመውሰድ ስላሰበው የሕግ ዕርምጃ ሐሳብ እየተለዋወጡ ነው]

  ሄሎ… ማን ልበል? ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ጤና ይስጥልኝ… ማን ልበል? የእርስዎ ትይዩ ነኝ፡፡  አቤት? ያው ፓርቲዬን ወክዬ የፍትሕ ሚኒስትሩ ትይዩ ነኝ ማለቴ ነው፡፡ ኦ... ገባኝ… ገባኝ...  ትንሽ ግራ አገባሁዎት አይደል? ትይዩ...

   [ክቡር ሚኒስትሩ እራት እየበሉ መንግሥትን በሚተቹ ጋዜጠኞች ላይ እየተወሰደ ያለውን ዕርምጃ የተመለከተ መረጃ እየቀረበላቸው ነው]

  ለጋዜጠኞቹ መንግሥትን እንዲተቹ መረጃ የሚሰጧቸው ታሪካዊ ጠላቶቻችን ናቸው፡፡ እነሱ አይደሉም፡፡ እና የትኞቹ ናቸው? እዚሁ ከተማችን የሚገኙ ምዕራባውያን ናቸው። እንዴት ነው መረጃውን የሚያቀብሏቸው? እራት እያበሉ ነው። ምን? አዎ፣ እራት ግብዣ ይጠሯቸውና መተቸት...

  [ክቡር ሚኒስትሩ ከፕሮፓጋንዳ ጉዳዮች ኮሚቴ ሰብሳቢው ጋር ስለ ሰሜኑ የሰላም ስምምነት ትግበራ መረጃ እየተለዋወጡ ነው]

  እኔ ምልህ፡፡ አቤት ክቡር ሚኒስትር? የሰሜኑ ተዋጊዎች ከሠራዊታችን ጋር መቀራረብ ጀመሩ የሚባለው እውነት ነው?  አዎ። እውነት ነው ክቡር ሚኒስትር።  ከማንም ትዕዛዝ ሳይጠብቁ ነው ከእኛ ሠራዊት ጋር መቀላቀል ጀመሩ...