Friday, December 9, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትአፍሪካ ለዓለም ዋንጫ ተሳታፊነት የጠየቀችው አሥር ኮታ

  አፍሪካ ለዓለም ዋንጫ ተሳታፊነት የጠየቀችው አሥር ኮታ

  ቀን:

  በዓለም እግር ኳስ ዋንጫ አፍሪካን የሚወክሉ አገሮች ቁጥር ከአምስት ወደ አሥር ከፍ እንዲል የአህጉሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች መሪዎች መጠየቃቸውን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል፡፡

  ከዘጠኝ ዓመት በኋላ በሚተገበረውና 48 አገሮች በሚወዳደሩበት የዓለም ዋንጫ፣ የአፍሪካ ቁጥር በእጥፍ እንዲጨምር መሪዎቹ የጠየቁት የፊፋ ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ለሁለት ቀን ስብሰባ ደቡብ አፍሪካ በተገኙበት አጋጣሚ ነው፡፡

  በ2018 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 2016) በ48 ቡድኖች መካከል ሊካሄድ ለታሰበው የዓለም ዋንጫ አዲሱ ቅጥ (ፎርማት) የአፍሪካ ቁጥር ከአምስት ወደ ዘጠኝ ከፍ እንደሚል ጭምጭምታ አለ፡፡

  አፍሪካ ከ1990 ዓ.ም. (1998) የፈረንሣይ ዓለም ዋንጫ ጀምሮ በአምስት አገሮች ማሳተፍ የጀመረች ሲሆን፣ አንድም ቡድን ከአህጉሪቱ ዋንጫውን ማሸነፍ አልቻለም፡፡ በየአራት ዓመቱ በሚካሄደው የዓለም ዋንጫ አንድም የአፍሪካ አገር ሩብ ፍጻሜን መሻገርም አልሆነለትም፡፡ በ2006 ዓ.ም. (2014) በተካሄደው የብራዚል ዓለም ዋንጫ ሁለት ቡድኖች ጥሎ ማለፍ ደረጃ ላይ መድረሳቸው ግን ይታወሳል፡፡

  አውሮፓ ከ13 ወደ 16 ከፍ እንዲልላት ፍላጎቷን ስታሳይ፣ እስያ በበኩሏ ከ4 ½ ወደ ስምንት ወይም ዘጠኝ እንዲያድግላት፣ ደቡብ አሜሪካም ከ4 ½ ወደ ስምንት ወይም ዘጠኝ እንዲያድግላት፣ ደቡብ አሜሪካም ከ4 ½ ወደ ስድስት እንዲጨመር ይፈልጋሉ፡፡

  ካሪቢያን፣ መካከለኛው ሰሜን አሜሪካ አገሮች ከ3 ½ ወደ 6 ½ በፓስፊክ ደሴት የምትገኘዋ ኦሺያና ከነበራት ½ ወደ ቀጥታ ተሳታፊነት እንድትገባ ፍላጎት አለ፡፡ የ1/2 ተሳታፊነት በአህጉሮች መካከል በሚሰጥ አንድ ዕድል በሚደረግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ የሚለይ ነው፡፡ የየአህጉራቱ ጥያቄና ፍላጎት እልባት የሚያገኘው የፊፋ ምክር ቤት በሚያደርገው ጉባኤው ነው፡፡

  አፍሪካ እስከ 1962 ዓ.ም. (1970) የሜክሲኮ የዓለም ዋንጫ ድረስ በቀጥታ ተወካይ አልነበራትም፡፡ በወቅቱ የፊፋ ቅጥ አፍሪካና እስያ በጋራ አንድ ቦታ ብቻ ሲኖራቸው የሁለቱ አሸናፊ ብቻ ይሳተፍ ነበር፡፡

  ‹‹የሁለቱ አህጉሮች ሻምፒዮኖች እርስ በርሳቸው ተጋጥመው አሸናፊው ይምጣ›› የሚለውን አሠራር ኢትዮጵያዊው የፊፋ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የነበሩት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ በ1958 ዓ.ም. በመሩት ተቃውሞ፣ ‹‹የፊፋ ውሳኔ ለሦስተኛው ዓለም ስድብ ነው›› በማለት በለንደኑ የዓለም ዋንጫ አፍሪካ አልካፈልም በማለቷና አቋም በመያዟ በተከታዩ ውድድር አንድ አንድ ቦታ ለሁለቱም አህጉራት ለመስጠት ፊፋ መገደዱ ይታወሳል፡፡ 

  R1756 Sport News T

  Tigist

  አፍሪካ ለዓለም ዋንጫ ተሳታፊነት የጠየቀችው አሥር ኮታ

  በጋዜጣው ሪፖርተር

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ጭፍጨፋና ሥጋቱ

  ኦሮሚያ ክልል ከቀውስ አዙሪት መላቀቅ ያቃተው ይመስላል፡፡ ከ200 በላይ...

  እናት ባንክ ካፒታሉን ወደ አምስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወሰነ

  መጠባበቂያን ሳይጨምር የባንኩ የተጣራ ትረፍ 182 ሚሊዮን ብር ሆኗል እናት...

  ቡና ባንክ ዓመታዊ ትርፉን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ማሻገር ቻለ

  ቡና ባንክ በ2014 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔውን ለመጀመርያ...