‹‹ሰዎች ስለ አብዮት እያወሩ ነው፡፡ በአሜሪካ ሴት ፕሬዚዳንት የማግኘት አብዮት ምን ይመስል ይሆን?››
የቀድሞዋና የመጀመሪያዋ የአሜሪካ ሴት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማድሊን ኦልብራይት፣ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሴት ተማሪዎች ለሒላሪ ክሊንተን ድምጻቸውን እንዲሰጡ በኒውሀምሻየር ተገኝተው ካደረጉት ንግግር የተወሰደ፡፡ ኦልብራይት በኒውሀምሻየር ለበርካታ መራጮች በተለይም ለሴት ተማሪዎች ባደረጉት ንግግር ሴቶች ለሒላሪ ድጋፋቸውን ማሳየት እንዳለባቸው ሲያሳስቡ፣ ‹‹ለሴት ድጋፍ ለማያደርጉ ሴቶች በሲኦል የተለየ ቦታ አለ›› እስከማለት ሁሉ ደርሰው ነበር፡፡