Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ​​​​​​​የክትባት ሽፋን መጨመሩ ተገለጸ

​​​​​​​የክትባት ሽፋን መጨመሩ ተገለጸ

ቀን:

– የ2015 ዓለም አቀፍ የክትባት ግብን በሚመለከት የዓለም የጤና ድርጅት አስጠነቀቀ

አምስተኛው የአፍሪካ የክትባት ሳምንት እንዲሁም የዓለም የወባ ቀን ከሚያዝያ 16 እስከ 21 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ በተለያዩ ቦታዎች እንደሚከበር ባለፈው ረቡዕ ያስታወቀው ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ የክትባት ሽፋን እየጨመረ መሆኑንና ከ53 በመቶ ወደ 91 በመቶ ማደጉን አስታውቋል፡፡ ይህን ለጋዜጠኞች የገለጹት በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሕፃናት ጤና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ኤፍሬም ተክሌ ናቸው፡፡

የክትባት ሳምንቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎችም የአፍሪካ አገሮች የሚከበር ሲሆን፣ በዚሁ ሳምንት ለሚደረገው የክትባት ዘመቻ 2.1 ቢሊዮን ብር በጀት መያዙ ተገልጿል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በተመሳሳይ መልኩ የዓለም የወባ ቀንም በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ እንቅስቃሴዎች ታስቦ እንደሚውል ተገልጿል፡፡ ይህ የክትባት ሳምንት በማኅበረሰቦች ዘንድ የክትባት አስፈላጊነትን በሚመለከት ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራዎችን በማጠናከር በከፍተኛ ሁኔታ ለበሽታዎች ተጋላጭ ለሆኑ ክትባትን ተደራሽ ማድረግን ያለመ ነው፡፡ በይበልጥም ሩቅና ገጠራማ ቦታዎች ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በሌላ በኩል የእናቶችና የሕፃናት ጤና ላይ ያተኮሩና ሌሎችንም መሰል እንቅስቃሴዎችን በተለያየ መንገድ ሊያግዝና ሊደግፍ እንደሚችል ይታመናል፡፡

በአፍሪካ በየዓመቱ በክትባት መከላከል በሚቻሉ በሽታዎች ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ሦስት ሚሊዮን የሚገመቱ ሕፃናት ሕይወታቸውን እንደሚያጡ የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል፡፡ ምንም እንኳ ከክትባት ሽፋንና ተደራሽነት ጋር በተያያዘ መሻሻሎች ቢኖሩም አሁንም ብዙ መሥራት እንደሚያስፈልግ እየተገለጸ ነው፡፡

በቅርቡ የፀደቀው የአፍሪካ አህጉራዊ ስትራቴጂክ ፕላን (እ.ኤ.አ. 2014 እስከ 2020) እንደሚያሳየው፣ ዕቅዱ በአገራቱ ቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቶት ወደ ተግባር ሲለወጥ፣ በ2020 ክትባት ለሁሉም ሰው በተለይም ተጋላጭ ለሆኑ ሕዝቦች ተደራሽ እንዲሆን ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሌላ በኩል የዓለም ጤና ድርጅት የ2015 (እ.ኤ.አ.) የዓለም የክትባት ግብን በመምታት ረገድ ያሉ ሥራዎች ከመስመር ውጪ እንዳይሆኑ አስጠንቅቋል፡፡ ምክንያቱም ከአምስት ሕፃናት አንዱ ሕይወት አድን ክትባት ሳያገኝ እየቀረ ለህልፈት እየተዳረገ ነውና፡፡ የድርጅቱ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በየዓመቱ 1.5 ሚሊዮን ሞትን ሊያስቀር የሚችል ክትባት ሳይሰጥ እየቀረ ነው፡፡

ይህ የዓለም የጤና ድርጅት ማስጠንቀቂያ፣ በተለይም በዓለም አቀፍ ደረጃ በብዙ አገሮች ባለፉት ዓመታት የኩፍኝ ወረርሽኝን መቀስቀስ ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ‹‹የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የተቀናጀ ጥረት በማድረግ ስድስቱ ግቦች እንዲሳሱ ማድረግ ወሳኝ ነው›› ያሉት በዓለም ጤና ድርጅት ረዳት ጠቅላይ ዳይሬክተር ዶ/ር ፍላቪያ ራስትሪዮ ናቸው፡፡

እሳቸው እንዳሉት፣ የዓለም የክትባት ሳምንት እያንዳንዱ ሕፃን ክትባት እንዲያገኝ የሚያስችሉ ዕርምጃዎች እንዲጠናከሩና በአዲስ ኃይል እንዲቀጥሉ ዓለም አቀፍ መድረክ ይሆናል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...