Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ሥነ ፍጥረትዕንቁላል ምንድን ነው?

ዕንቁላል ምንድን ነው?

ቀን:

የዕንቁላል አሠራር በተለያዩ ሒደቶች ይከናወናል፡፡ በመጀመርያ አስኳሉ ዕንቁል ዕጢ ውስጥ ይሠራል፡፡ ከዕንቁል ዕጢ ይወጣና ወደ ማህፀን የሚወስደው ቱቦ  (ቦየ ዕንቁል ዕጢ) ውስጥ ይገባል፡፡ እዛም ነጩ የዕንቁላል ክፍል ይጨመርበታል፡፡ ከዛም ወደታችኛው ቱቦ በመውረድ ሜምብሬንና ቅርፊት በነጩና ቢጫው ክፍል ላይ ይደረብበታል፡፡ ከዚህ በኋላ ነው ዕንቁላሉ ለመጣል የሚደርሰው፡፡ የምታሽካካው ዶሮ ልክ በዚህ ጊዜ ነው፡፡

ሕይወት ያለው የዕንቁላል ክፍል ጥቂቱ ብቻ ነው፡፡ ያም ቢጫው ላይ ያለ ነጭ ነጥብ ሲሆን፣ በግንኙነት ጊዜ ከወንዱ ነባዘር ሲመጣ ውሑዱ ሕዋስ የሚሠራው ከዛው ነው፡፡ ዕንቁላሉ ከመፈልፈሉ በፊት ባለው ጊዜም የሚሠራው ከዛው ነው፡፡ ዕንቁላሉ ከመፈልፈሉ በፊት ባለው ጊዜም አስኳሉና ነጩ ክፍል ለሚያድገው ሽል እንደምግብነት ያገለግላል፡፡ ስለዚህም ሽሉ የተለያዩ አካላዊ ዕድገት ኖሮት ጫጩት ሆኖ እንዲፈለፈል ይረዳል፡፡ ይህም ሁኔታ የአዕዋፍን አረባብ ከአጥቢዎች ለየት ከሚያደርጉት አንዱ ነው፡፡ ምክንያቱየም አጥቢዎች በደማቸው አማካይነት ለሽሉ ማደጊያ ምግብ ሲያቀብሉ፤ አዕዋፍ ግን በዕንቁላል ውስጥ የሚያስፈልገውን የምግብ ግብዓት ሰንቀው ነው ዕንቁላል የሚጥሉት፡፡

ለ) ጥንድ እንቁላል እንዴት ይሠራል?

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

አልፎ አልፎ ዶሮዎች ጥንድ ዕንቁላል ይጥላሉ፡፡ ይህም ትልቅ መጠን ያለውና ሁለት አስኳል የያዘ ነው፡፡ እንዲህ የሚሆነው ከዕንቁላል ዕጢ ውስጥ ሁለት አስኳል በአንድ ጊዜ በሚወጡበትና ወደ ማህፀን የሚወስደው ቱቦ (ቦየ ዕንቁላል ዕጢ)  በሚሄዱበት ጊዜ ነው፡፡ አንድ ላይ ሆነው ስለሚጓዙ (ተጠጋግተው ከሁለቱም ላይ በአንድነት ነጩ ክፍል ቅርፊትና ሜምብሬን ይደረብባቸውና ጥንድ ዕንቁላል በሌላ በራሱ ቅርፊት በተሸፈነ ሌላ ዕንቁላል ውስጥ ይገኛል፡፡ ይህም ሊሆን የሚችለው ሁሉን ነገር ያጠናቀቀ ሙሉ ዕንቁላል ከመጣል ይልቅ ወደ ዕንቁላል ዕጢው ይለቀቅና በአንድነት ወደ ታች ሲወርዱ ነው፡፡ ይህንን ተከትሎም ሁለቱንም ዕንቁላሎች ቅርፊት፣ ሜምብሬንና ነጩ ክፍል ይሸፍናቸዋል፡፡ አንዱ በአንዱ ውስጥም ጥንድ ዕንቁላል ይሆናሉ፡፡

ሐ) አውራ ዶሮ ዕንቁላል ይጥላል?

አንዳንዴ ከመደበኛው አንድ አሥረኛ መጠን ያለው በጣም ትንሽ ዕንቁላል በወፍ ጎጆ ውስጥ ይገኛል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ዕንቁላልም በአውራ ዶሮ የተጣለ ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ ይህ ግን ከሐቅ የራቀ ነው፡፡ እኒህ ትንንሽ ዕንቁላልም የሚጣሉት በሴት ዶሮዎች ነው፡፡ ይህም የሚሆነው ከመጠን ያነሰ አስኳል ያልሆነ ቁርጥራጭ ኅብረ ሕዋስ ከዕንቁል-ዕጢ ተለቆ አስፈላጊዎቹን መሸፈኛ በሚያገኝበት ጊዜ ነው፡፡

መ) የዕንቁላሎች መጠን

      የሰጎን ዕንቁላል ከሁሉም ይበልጣል፡፡ ባዶው የሰጎን ዕንቁላል ቅርፊት ከ12 እስከ 18 የዶሮ ዕንቁላል ሊይዝ ይችላል፡፡ ቁመቱ ከ15 እስከ 17 ሳ.ሜ፣ ዙሪያው ከ12 እስከ 15 ሳ.ሜ. ሲሆን ተቀቅሎ ለመብሰል 40 እና ከዛ በላይ ደቂቃ ይፈልጋል፡፡

እዝዝ ወፎች ደግሞ ትንሹን ዕንቁላል ይጥላሉ፡፡ የእዝዝ ወፍ ዕንቁላል በቁመት ከግማሽ ሳንቲ ሜትር ብዙም ያልበለጠ ይሆናል፡፡ ኪዊ የሚባሉት ደግሞ የአካል ክብደታቸውን አንድ አራተኛ የሚያክል ዕንቁላል ይጥላሉ፡፡ የኪዊ ክብደት 3.3 ኪ.ግ. በመሆኑ አካላቸው ከብዶ እንዲንገዳገዱ ያደርጋቸዋል፡፡ በዚህም በቀላሉ ለጠላቶቻቸው ይጋለጣሉ፡፡ ኪዊ በኒውዝላንድ ብቻ የሚገኝና ብሔራዊ ምልክታቸው ሆኖ የሚያገለግል ነው፡፡ ኪዊን አብዛኞቻችን የምናውቀው የጫማ ቀለም ምልክት ሆኖ ነው፡፡ ኪዊ ከማይበሩት አዕዋፍ ይመደባል፡፡

  • ማንይንገረው ሸንቁጥ ‹‹ባለአከርካሪዎች›› (2004 ዓ.ም.)

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...