Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየሁለት ፋሲካዎች ወግ

የሁለት ፋሲካዎች ወግ

ቀን:

ከሁለት ወር ዓቢይ ጾም በኋላ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችና በዓለም ዙርያ ያሉ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ዛሬ (ሚያዝያ 4 ቀን 2007 ዓ.ም.) ፋሲካን (ትንሣኤ) እያከበሩ ነው፡፡ ምዕራባውያኑና ተከታዮቻቸው ደግሞ ከሳምንት በፊት አክብረዋል፡፡ ፋሲካ በተመሳሳይ ምክንያት የሚዘከር በዓል ሆኖ ሳለ በተለያየ ቀን መከበሩ የብዙዎች ጥያቄ ነው፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት ተለይቶ የተነሣበት ቀን በካቶሊክ ሃይማኖት (ምዕራባውያኑ) ከኦርቶዶክሳውያኑ (ምሥራቃውያኑ) ቀናት ቀድሞ ይከበራል፡፡ ሊቃውንት እንደሚያስረዱት፣ በሁለቱ ሃይማኖቶች መካከል ክብረ በዓሉ የሚውልበት ቀን ልዩነት የመጣው አንድም በሚከተሉት የቀን መቁጠሪያ ነው፡፡

በኦርቶዶክስ ክርስትና ሃይማኖት ፋሲካ የሚውልበት ቀን የሚሰላው በጁልያን ቀን መቁጠሪያ ሲሆን (ኢትዮጵያና ኮፕት በራሳቸው ባሕረ ሐሳብ ያሰላሉ)፣ የተቀሩት የክርስትና ሃይማኖቶች ግሪጐሪያን ቀን መቁጠሪያ ይከተላሉ፡፡ በሁለቱ አቆጣጠሮች መካከል የ13 ቀናት ልዩነት ያለ ሲሆን፣ ግሪጐሪያኑ ከጁልያን ቀድሞ ይመጣል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ሌላው ምክንያት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በ325 ዓ.ም. በኒቂያ የተካሔደው የመጀመሪያው ኢኩሜኒካል ጉባኤ ያወጣውን መርህ መከተሏ ነው፡፡ መርሁ ፋሲካ ከአይሁዳውያን ፍሥሕ (ፓስኦቨር) በኋላ አንዲከበር ይደነግጋል፡፡ ይህም መጽሐፍ ቅዱስ የሚያትተውን ታሪካዊ አካሔድ በመከተል ነው፡፡ ከኦርቶዶክስ ውጪ ያሉ የክርስትና እምነቶች በዚህ መርህ ስለማይተዳደሩ የክርስቶስ ፋሲካ ከአይሁዳውያኑ ፍሥሕ ቀድሞ ወይም አብሮ ይከበራል፡፡

በተጠቀሱት ምክንያቶች መሠረት የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከተቀሩት በተለየ ፋሲካን ከሦስት እስከ አምስት በሚደርሱ ሳምንታት ልዩነት ብታከብርም፣ አንዳንዴ በተመሳሳይ ቀን ይውላል፡፡ ከዚህ ቀደም ፋሲካ ተመሳሳይ ቀን የዋለው በ2002 ዓ.ም.፣ በ2003 ዓ.ም. እና በ2006 ዓ.ም. ሲሆን፣ በቀጣይ በ2009 ዓ.ም. ፋሲካ በአንድ ቀን ይከበራል፡፡ ከዚያ በኋላ እስከ 2022 ዓ.ም. በተመሳሳይ ቀን አይውልም፡፡

ፋሲካ አንድ ቀን የሚውለው በጁልያንም ግሪጐሪያንም ቀን አቆጣጠር መሠረት ጨረቃ ሙሉ ስትሆን ነው፡፡ ይህ በተደጋጋሚ አይከሰትም፡፡ የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ሆነው ኦርቶዶክስ በሆኑና ባልሆኑ መካከል ፋሲካ የሚከበርበት ቀን መለያየቱ ብዙዎችን ግራ የሚያጋባ ቢሆንም፣ በሁለቱም የፋሲካ ቀን የሚታወቅበት የተለያየ ቀመር አላቸው፡፡

አባ ጆን ማጉሊያስ ‹‹Why Orthodox Christian Easter is Later than the Catholic One›› በሚል ርእስ እንደጻፉት፣ የክርስትና እምነት በመጀመርያዎቹ ሦስት አሠርታት ላይ ፋሲካ የሚከበርበት ወጥ ቀን አልነበረውም፡፡ አንዳንድ የእምነቱ ተከታዮች የአይሁዳውያን ፍሥሕ አልፎ በሚመጣው የመጀመርያው እሑድ ያከብሩ ነበር፡፡ ሌሎች ደግሞ ከፍሥሕ ጋር በተመሳሳይ ወቅት ያከብራሉ፡፡ ወጥ ቀን ለበዓሉ ለመስጠት ያሰቡ ቅዱሳን አባቶች በ325 ዓ.ም. የመጀመርያውን ኢኩሜኒካል ጉባኤ አካሔዱ፡፡ በቀደምት ክርስቲያኖች አካሔድና በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮት መሠረት ወጥ የሆነ ቀን ለማግኘት ተማከሩ፡፡

የደረሱበት ቀመር ፋሲካ ጨረቃ ሙሉ በሆነችበት የመጀመርያው እሑድ ማለትም ከአይሁድ ፍሥሕ በኋላ እንዲከበር ነው፡፡ ይህም ከፀደይ እኩሌ (ቨርናል ኢኩኖክስ) (ቀንና ሌሊት እኩል እኩል 12 ሰዓት ከሚሆኑበት ቀን) በኋላ ነው፡፡ ይህ ቀን ግራ መጋባት እንዳይፈጥር ቀኑ በግሪጐሪያን ማርች 21 እና በጁልያን ቀን መቁጠሪያ ደግሞ ኤፕሪል 3 (በኢትዮጵያ መጋቢት 25) እንዲሆን ተወሰነ፡፡ በዓለም ላይ ፋሲካ የሚከበርበት ቀንም አንድ ሆነ፡፡ ይህን መርህ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተከትላው ብትዘልቅም፣ የምዕራባውያኑ ቤተ ክርስቲያን ቀመሩን ከጊዜ በኋላ አልተከተሉትም፡፡

የምዕራብ ነገረ መለኮት ምሁራን (ጥቂት ኦርቶዶክሶችን ጨምሮ) የጉባኤው ዓላማ ፋሲካ ምንጊዜም የአይሁዳውያንን ፍሥሕ ተከትሎ እንዲከበር ለማድረግ አይደለም በሚል ይቃወሙታል፡፡

የጉባኤውን ውሳኔ አለመቀበል ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት የተነሣበት ቀን ማለትም ከ325 – 1582 ዓ.ም. የተከበረበትን ደንብ መጻረር ይሆናል የሚሉ አሉ፡፡ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ተመራማሪዎችና ሊቃውንት እንደሚገልጹት፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ማንኛውም ጳጳስ ወይም ዲያቆን ቀንና ሌሊት እኩል 12 ሰዓት ከሚሆኑበት ቀን ቀድሞ ፋሲካን ከአይሁዳውያኑ ጋር ቢያከብር ይጋለጥ፤›› ይላል፡፡

እ.ኤ.አ. በ1582 ጳጳሱ ግሪጐሪ 13ኛ የጁልያን ቀን መቁጠሪያን ዳግም ከልሰውታል፡፡ በአብዛኛው የዓለም ክፍል ግልጋሎት ላይ የሚውልም ነው፡፡ ከምዕራባውያን ቤተ ክርስቲያኖች አብዛኞቹ ይህን ቀን መቁጠሪያ መጠቀም ሲጀምሩ፣ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ግን የግሪጐርያን ቀን አቆጣጠርን በጥብቅ ተቃውማለች፡፡

እ.ኤ.አ. በ1920 የኦርቶዶክስ ተከታዮች አጠቃላይ ጉባኤ በቁስጥንጥንያ (ኮንስታንቲኖፕል) ተካሒዶ ነበር፡፡ ጉባኤውን መላው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያኖች ባይካፈሉም ብዙዎች ተገኝተው ነበር፡፡

ጉባኤው በአወዛጋቢ ሁኔታ ከግሪጐሪያን ቀን መቁጠሪያ ጋር ተቀራራቢ የሆነና የተከለሰ ቀን መቁጠሪያ በሥራ ላይ ለማዋል ተስማምቷል፡፡ ይህ በተግባር የሚውለው ከፋሲካ ክብረ በዓል ዕለት ውጪ ላሉት ሲሆን፣ ፋሲካ ግን ዛሬም በኦርጅናሉ የጁልያን ቀን መቁጠሪያ ቀጥሏል፡፡

የቀን መቁጠሪያው መሻሻል የሚስተዋለው ልደትና ጥምቀትን የመሰሉ ክብረ በዓላትን ከምዕራባውያን ቤተ ክርስቲያኖች ጋር በተመሳሳይ ቀን በመከበሩ ነው፡፡ ከፋሲካ ጋር ጴንጤቆስጤና ዕርገት በጁልያን ቀን አቆጣጠር መሠረት በተለየ ቀን የሚከበሩ ሲሆን፣ ለኦርቶዶክሳውያን በዚህ መልክ የቀደመውን ሥርዓት መከተል ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው ነው፡፡    

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...