Thursday, March 23, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

አክሰስ ሪል ስቴት አቶ ኤርሚያስ አመልጋን የቦርድ ሰብሳቢ አድርጐ ሰየመ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ከሁለት ዓመታት በኋላ ከቆዩበት የሕግ ከለላ በማግኘት ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ (ዱባይ) በቅርቡ የተመለሱት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፣ በቅርቡ የአክሰስ ሪል ስቴት አክሲዮን ማኅበር የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መመረጣቸው ታወቀ፡፡

መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ባደረገው ድርድር ከ2,000 በላይ ከሚሆኑ ከአክሰስ ሪል ስቴት ቤት ገዢዎች ጋር በተደረሰ ስምምነት ከየካቲት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ በሪል ስቴቱ ውስጥ ሥራ የጀመሩት አቶ ኤርሚያስ፣ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መመረጣቸው ያልተጠበቀ ነው ተብሏል፡፡

ምንጮች እንዳረጋገጡት አቶ ኤርሚያስ የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነው የተሰየሙት የማኅበሩ ጠቅላላ ጉባዔ ተሰብስቦና ምርጫ ተካሂዶ ሳይሆን፣ በጐደለ የቦርድ አባል ምትክ እንደማንኛውም የማኅበሩ አባል አንድ ድምፅ ብቻ ይዘው መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይኼም የሆነው የቤት ገዢዎች ያቋቋሙት ኮሚቴ ከመንግሥት ተወካዮች ጋር ተወያይቶ አቶ ኤርሚያስ ቤቶችን የሚገነቡ ኮንትራክተሮችን ያመጡት የቦርድ ሊቀመንበር መሆናቸውን ነግረውና አሳምነው በመሆኑ፣ እንደማንኛውም የማኅበሩ አባል ሆነው ቢቀጥሉ በኮንትራክተሮቹ ላይ ብዥታ ሊፈጠር ይችላል በሚል ምክንያት ስምምነት ላይ ተደርሶ መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

አቶ ኤርሚያስ የቦርድ ሰብሳቢ ከመሆናቸው በተጨማሪ በድርጅቱ ሒሳብ አያያዝም ሆነ ሥራ አስኪያጅነት እንደማይሳተፉ ስምምነት ላይ መደረሱን የተናገሩት ምንጮች፣ በዋናነት ሥራውን በበላይነት ለመምራትና ኮንትራክተሮችን በመቆጣጠር ሥራው የተፋጠነ እንዲሆን በማድረግ ላይ እንደሚያተኩሩ ታውቋል፡፡

ከአቶ ኤርሚያስ ጋር በመደራደር ግንባታ ለመጀመር ጫፍ ላይ መድረሳቸው የተነገረው የቻይና ኮንትራክተሮች፣ ሪል ስቴቱ ገዝቶት የግንባታ ፈቃድና የይዞታ ማረጋገጫ ያገኘው ቦሌ ክፍለ ከተማ ፊት ለፊት በሚገኘው ቦታ ላይ ትኩረት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

በቦታው ላይ ባለአሥር ፎቅ ሕንፃ ለመገንባት ታስቦ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን ባለ23 ፎቅ ሕንፃ ለመገንባት በሌላ አካባቢ ያሉ ቦታዎችን በመሸጥ ለዚህኛው ግንባታ ግብዓት ለማድረግ መታሰቡን ምንጮች አስረድተዋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች