Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊጣሊያናዊው ግብረሰዶም በመፈጸም ወንጀል ተጠርጥረው ታሠሩ

ጣሊያናዊው ግብረሰዶም በመፈጸም ወንጀል ተጠርጥረው ታሠሩ

ቀን:

  • ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ማረሚያ ቤት መውረዳቸው ተጠቁሟል

የጣሊያን ዜግነት አላቸው የተባሉት ራንቺፍ ፎክቲዎሊ የተባሉ ግለሰብ፣ በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ዙርያ በሚገኝ ወላጅ አልባ ለሆኑና ለአካባቢው ልጆች የትምህርትና ዕርዳታ በሚሰጥ ድርጅት ውስጥ፣ በታዳጊ ወንድ ሕፃናት ላይ የግብረሰዶም በመፈጸም ወንጀል ተጠርጥረው መታሰራቸውን የሪፖርተር ምንጮች አረጋገጡ፡፡

ተጠርጣሪው መጋቢት 17 ቀን 2007 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ውለው ሻሸመኔ 03 ፖሊስ ጣቢያ ከታሰሩ በኋላ፣ ፍርድ ቤት ቀርበው የ14 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ሻሸመኔ ማረሚያ ቤት መውረዳቸውንም ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ጣሊያናዊ ናቸው የተባሉት ተጠርጣሪ ድርጊቱን ሲፈጽሙ የሚያሳይ ሲዲ በመገኘቱና ድርጊቱ ተፈጽሞበታል የተባለው ታዳጊ ተጠይቆ በማመኑ፣ በፍርድ ቤት ማዘዣ ግለሰቡን መያዝ እንደተቻለም ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ ግለሰቡ ጭምጭምታ በመስማታቸው ከአገር ሊወጡ መሆኑን ፖሊስ በመስማቱ፣ ቀሪ ክትትሎችን በማድረግና መረጃዎችን በማጠናቀር እሳቸውን በቁጥጥር ሥር አውሎ የምርመራ ሥራውን መቀጠሉንም አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...