Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአሜሪካ የሰላም ጓዶች በጾታ እኩልነት ላይ ያተኮረ ስብሰባ ጀመሩ

የአሜሪካ የሰላም ጓዶች በጾታ እኩልነት ላይ ያተኮረ ስብሰባ ጀመሩ

ቀን:

የአሜሪካ የሰላም ጓዶች የሥነ ጾታና የልማት ኮሚቴ፣ ‹‹የጾታ እኩልነት በተግባር›› የተሰኘ መርሐ ግብር ሁለተኛውን አገር አቀፍ ስብሰባ ከመጋቢት 8 እስከ መጋቢት 12 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ስብሰባው የወጣት አመራርን አቅም በመገንባት ላይ በማተኮር ለሦስት ወራት ሲካሄድ የቆየው ሥልጠና የሚጠናቀቅበት ሲሆን፣ ሥልጠናው በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች የሚገኙ ወጣቶች የተሳተፉበት፤ ወጥ የሆነና ወጣቶችን ያማከለ የሥነ ጾታና የልማት መርሐ ግብር አካል ነበር፡፡

ለአምስት ቀናት በሚቆየው ፕሮግራም መክፈቻ ላይ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ፓቲሪሺያ ሃስላክ እንደተናገሩት፣ ‹‹ወጣቱ ትውልድ በመጪው ጊዜ የተሳካ ሕይወት መምራት ይችል ዘንድ ከወንድም ሆነ ከሴት ወጣቶች ጋር ተቀራርቦ መሥራት አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህ ረገድ የሰላም ጓዶች ከፍተኛ ሚና አላቸው፡፡››

የጾታ እኩልነት በተግባር የተሰኘው ፕሮጀክት ከ14 እስከ 18 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ፣ ላለዕድሜ ጋብቻ፣ ለጾታዊ ጥቃት፣ ለኤችአይቪ ኤድስና ለሌሎችም የአባለዘር በሽታዎች በተጋለጡና በገጠር የሚኖሩ ወጣቶች ላይ ያተኩራል፡፡

የሰላም ጓዶች በዓለም ዙሪያ በተለያዩ አካባቢዎች በጾታ እኩልነትና ሴቶችን በማብቃት ዙሪያ፤ በተለይ በታዳጊ አገሮች የተለያዩ ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ የሰላም ጓዶች የሥርዓተ ጾታና ልማት ኮሚቴ በተለያዩ የአገሪቱ የካባቢዎች እነዚህን ሥራዎች ያስተባብራል፡፡ ኮሚቴው የሰላም ጓዶች በሚገኙባቸው ማኅበረሰቦች ውስጥ ሥልጠና በመስጠት፣ ወርኮሾፖችን በማዘጋጀትና የተለያዩ ግብዓቶችን በማቅረብ ቀጣይነት ያለው የሥርዓተ ጾታ ልማት የሚረጋገጥበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡

በስብሰባው ተማሪዎች በጾታ እኩልነት፣ በጤና፣ በኤችአይቪ ኤድስና ወጣቶችን በማብቃት ዙሪያ በሚቀርቡ የተለያዩ ዐውደ ውይይቶች ላይም ይሳተፋሉ፡፡ የሚያገኙትን ክህሎትም ወደ የክልላቸው ሲመለሱ ለአቻዎቻቸው የሚያካፍሉ ይሆናል፡፡

የስብሰባው ተሳታፊዎች፣ ባለፈው እሑድ (መጋቢት 6) በአዲስ አበባ ከተማ መነሻና መድረሻውን ዳያስፖራ አደባባይ ባደረገው ‹‹ቅድሚያ ለሴቶች›› 5 ኪ.ሜ. ሩጫ ላይ መካፈላቸው ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...