Saturday, November 26, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  ሰብዓዊ ተግባራት ሲወደሱ እኩይ ድርጊቶች ይወገዙ!

   ሰብዓዊነት ዕድሜ፣ ፆታ፣ ዘር፣ ሃይማኖት፣ የፖለቲካ አመለካከትና ሌሎች ልዩነቶች ሳይገድቡት የሚከናወን የተቀደሰ ተግባር ነው፡፡ ሰብዓዊነት ማንኛውም ሰብዓዊ ፍጡር ሰው በመሆኑ ብቻ የሚከበርበትና ከአድልኦና ከመገለል የሚጠበቅበት፣ ከጥቃትና ካልተገባ ተግባር የሚታደግበት የመልካም ነገሮች ሁሉ ነፀብራቅ ነው፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃም እጅግ የተመሰገነ ተግባር ነው፡፡ ለዚህም ነው ሰብዓዊ ተግባራት ሁሌም ይወደሱ የሚባለው፡፡

  በአገራችን በጦርነት፣ በድርቅ፣ በረሃብ፣ በተለያዩ ተፈጥሮአዊና ሰው ሠራሽ አደጋዎች ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች የታደጉ አንቱ የተባሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ታሪክ መዝግቦአቸዋል፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎችም ተወድሰዋል፡፡ ወላጅ አልባ ሕፃናትን በመንከባከብ፣ ጧሪ ቀባሪ የሌላቸውን አረጋውያን ከወደቁበት በማንሳት፣ የአዕምሮ ሁከት ገጥሟቸው ሥቃይ ውስጥ የነበሩ ወገኖችን በመታደግ ሰብዓዊ ግዴታቸውን የተወጡና በመወጣት ላይ ያሉ አሉ፡፡ ክብር ምሥጋና ይድረሳቸው፡፡

  በ1977 ዓ.ም. በአገሪቱ በደረሰው አሰቃቂ ረሃብ ምክንያት ኑሮአቸውንና የተመቻቸ ሕይወታቸውን ሰውተው አንፀባራቂ ታሪክ የሠሩት ወ/ሮ አበበች ጎበና (ኢትዮጵያዊቷ እማሆይ ቴሬዛ)፣ ምንጊዜም ቢሆን የማይዘነጋና ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ አሻራ አኑረዋል፡፡ እንደ እሳቸው ዓይነት ቁጥራቸው የማይናቅ ኢትዮጵያውያን በመከራ ጊዜ ሰብዓዊ ተግባራትን ፈጽመዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ መቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል በሰብዓዊ ተግባሩ ስሙ እየተነሳ ሲሆን፣ ለዚህ ሰብዓዊ ዓላማ የምሥጋናና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም አዘጋጅቷል፡፡ ለሚንከባከባቸው ወገኖች የተሻለ ማዕከል ለመገንባት በዝግጅት ላይ መሆኑም ታውቋል፡፡ ሕዝቡም ድጋፉን እያበረከተ ነው፡፡ ሰብዓዊ ተግባራት ይወደሱ፡፡

  ሰብዓዊ ተግባራት ሲጠናከሩ በተለያዩ ምክንያቶች ችግር ውስጥ የወደቁ ዜጎች ያለምንም አድልኦና መገለል ድጋፍ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ በድህነት ውስጥ የሚኖሩ ቤተሰቦች ሕፃናት ምግብ፣ ልብስ፣ የትምህርት ቤት ክፍያና የትምህርት መርጃ መሣሪያዎች አግኝተው ተረጋግተው እንዲማሩ ይጠቅማል፡፡ የነገ አገር ተረካቢ ናቸውና ሰብዓዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ወላጅ አልባ ሕፃናት መጠለያን ጨምሮ ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች ተሟልተው ሲያገኙ ተስፋቸው ይለመልማል፡፡ ጧሪ ቀባሪ የሌላቸው አረጋውያን ሰብሳቢ ያገኛሉ፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች ዕድላቸው የተሰናከለባቸው ዜጎች ተሃድሶ ያገኛሉ፡፡ ሰብዓዊ ተግባራትን የሚያከናውኑ ሰዎች በብዛት ሲኖሩ የአገር ጫናና ሸክም በመጠኑም ቢሆን ይቀላል፡፡ ለእንዲህ ዓይነቶቹ የተከበሩ ዜጎች ምሥጋናና ውዳሴ መቸር አለበት፡፡

  ዜጎች ሰብዓዊ ተግባራትን ሲደግፉ የሚያበረክቱት ገንዘብም ሆነ ቁሳቁስ ለትክክለኛው ዓላማ መዋሉን የማረጋገጥ መብት ሊኖቸው ይገባል፡፡ ሰብዓዊ ተግባራትን በንፅህና የሚያከናውኑ ያሉትን ያህል፣ የረከሰ ተግባር የሚፈጽሙ እኩዮችም ሞልተዋል፡፡ አሳዳጊ የሌላቸው ሕፃናት መንከባከቢያ ማዕከል ከፍተው ሕፃናቱን የሚያስርቡና ለበለጠ ችግር የሚዳርጉ አሉ፡፡ በአረጋውያንና በሕሙማን ስም ከአገር ውስጥና ከውጭ የሚያጋብሱትን ዕርዳታ ከመሰሎቻቸው ጋር የሚዘርፉ እኩዮች ሞልተዋል፡፡ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት (NGO) አቋቁመው በሰብዓዊነት ስም የተገኙ የተለያዩ ድጋፎችን እንደ ግል ኩባንያቸው ለራሳቸው፣ ለቤተሰባቸውና ለጥቅም ሸሪኮቻቸው የሚያከፋፍሉ ህሊና ቢሶች ብዙ ናቸው፡፡ ከቀረጥ ነፃ የገቡ የዕርዳታ ቁሳቁሶችን በጠራራ ፀሐይ ይቸበችባሉ፡፡ ታክስ የማይከፈልበትን የዕርዳታ ገንዘብ ያለ ይሉኝታ ይዘርፋሉ፡፡  በድሆች ሕፃናት ስም ያጋበሱትን ዕርዳታ የቢጤዎቻቸውን ልጆች ውድ ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ አሉ፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ፀረ ሰብዓዊነት ተግባር ፈር የሚያሲዘው በመጥፋቱ በድሆች ስም የተገኘን ምፅዋት ህሊና ቢስ ሀብታሞች ይቀራመቱታል፡፡ መወገዝ አለባቸው፡፡

  በአገሪቱ ሙስና ፀንቶ ከሚታይባቸው መስኮች መካከል ይህ የዕርዳታ ማሰባበሲያ ዘርፍ ዋነኛ ነው ቢባል የተጋነነ አይደለም፡፡ ይህ ዘርፍ በሚፈጸምበት እኩይ ተግባር ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ ብዙ የተባለበት በመሆኑና ሀብታሞች የበለጠ የሚከብሩበት ስለሆነ፣ በአገራችን ሰብዓዊ ተግባራትን የሚያከናውኑ ወገኖችን ጭምር የሚያሸማቅቅ ነው፡፡ ወላጅ አልባ ሕፃናትና አቅመ ደካማ አዛውንቶችን አስጠግተው መከራ እያዩ የሚንከባከቡ እንዳሉ ሁሉ፣ ሰብዓዊነትን የዘረፋ ምንጭ ያደረጉ እኩዮች ሞልተዋል፡፡ ለሰብዓዊ ተግባር የሚተጉትን ስናወድስ እኩዮችን ደግሞ ማውገዝ አለብን፡፡ መፋረድም ይኖርብናል፡፡

  መንግሥት ድህነትን ለማስወገድ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የዜግነት ግዴታቸውን በአኩሪ መንፈስ የሚወጡትን እየደገፈና እያበረታታ፣ በደሃ ወገኖቻችን ስም የሚመጣውን ዕርዳታ የሚዘርፉ ኃይሎችን ሕግ ፊት የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ ጠንካራ ቁጥጥርና ፍተሻ እየተደረገ እነዚህ ዘራፊዎች ተመንጥረው ለሕግ መቅረብ አለባቸው፡፡ የሚተባበሩዋቸው የመንግሥት ሹማምንት ሳይቀሩ ፍትሕ ፊት እንዲቆሙ የማድረግ ኃላፊነት የመንግሥት ነው፡፡ የጥቅም ግንኙነት ያቆራኛቸው እኩዮች በድሆች ስም የተገኘ ዕርዳታ እየዘረፉ ሕንፃና ቪላ ሲገነቡ፣ ቢጤዎቻቸውን በሀብት ሲያጥለቀልቁና ሕግን ሲዳፈሩ ማየት ያሳፍራል፡፡ እነዚህ ተወግዘው ሕግ ሊፋረዳቸው ይገባል፡፡

  አሁንም ደግመን ደጋግመን የምንለው ሰብዓዊ ተግባራት ክብርና ዋጋ ይሰጣቸው ነው፡፡ ያለምንም አድልኦና መድልኦ የሚከናወኑ ሰብዓዊ ተግባራት ሰላምን፣ መተሳሰብን፣ አብሮነትንና ፍቅርን የሚያሰፍኑ በመሆናቸው በእኩዮች ድርጊት መበላሸት አይኖርባቸውም፡፡ ሰብዓዊ ተግባራት የልማት አካል በመሆናቸው መንግሥትም ሆነ ሕዝቡ ሊደግፋቸው ይገባል፡፡ የሒሳብ መዛግብቶቻቸው ከእንከን የፀዱ፣ በጠንካራ ኦዲት ንፅህናቸው የተመሰከረላቸውና በዕርዳታ ተቀባዮች ጭምር አንቱታ የተቸራቸው ከእኩዮቹ ተለይተው ይወደሱ፡፡ ይመስገኑ፡፡ ተምሳሌትነታቸው በአደባባይ በግልጽ ይነገርላቸው፡፡ ሽልማት ይሰጣቸው፡፡ በእኩይ ድርጊቶቻቸው የሚጋለጡት ደግሞ ይወገዙ፡፡ በሕግ ይጠየቁ፡፡

    

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  ሰርጌ ላቭሮቭ ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ በአዲስ አበባ በሰጡት መግለጫ ምዕራባውያንን አጣጣሉ 

  የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ለአፍሪካ አገሮች ላደረጉት...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...

  አሜሪካ ሕወሓትን በማሳመንና በመጫን በሰላም ሒደቱ ትልቅ ሚና መጫወቷን የኢትዮጵያ ዋና ተደራዳሪ አስታወቁ

  የተመድና የአውሮፓ ኅብረት አበርክቶ አሉታዊ እንደነበር ጠቁመዋል በመንግሥትና በሕወሓት መካከል...

  የአየር መንገድ ተጓዦች በሻንጣ የሚያስገቡትን የልብስና የጫማ ብዛት የሚገድብ ረቂቅ መመርያ ተዘጋጀ

  ከቀረጥ ነፃ ይገቡ የነበሩ ዕቃዎች 87 በመቶ እንዲቀንሱ ተደርጓል መንገደኞች...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን 55 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ወሰነ

  የአዋሽ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ዛሬ ህዳር 17 ቀን 2015...

  ከብሔራዊ ባንክ እውቅና ያገኘው ፔይሊንክ አክሲዮን ማህበር ምሥረታውን አካሄደ

  ከገንዘብ ንክኪ ነፃ የሆነ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ለመተግበር ያቀደው...

  የተወሳሰበው ሰላም የማስፈን ሒደት

  የደቡብ አፍሪካ የሰላም ስምምነት ተፈርሞ ብዙም ሳይዘገይ የኬንያው ቀጣይ...

  በግብርና ዘርፍ ለመሰማራት ያቀደው ድርዜማ

  ከፋይናንስ ተቋማት ውጪ ባሉ የተለያዩ የቢዝነስ ዘርፎች በአክሲዮን ኩባንያ...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊ ይደረግ!

  የሰላም ስምምነቱ ‹‹ታጥቦ ጭቃ›› ሊሆን የሚችልባቸው ምልክቶች እየተስተዋሉ ነው፡፡ ሚሊዮኖችን ለዕልቂት፣ ለመፈናቀል፣ ለከፍተኛ ሰብዓዊ መብት ጥሰትና መሰል ሰቆቃዎች የዳረገው አውዳሚ ጦርነት በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት...

  ዘረፋ የሚቆመው በተቋማዊ አሠራር እንጂ በዘመቻ አይደለም!

  ኢትዮጵያ ውስጥ ሌብነት ከመንግሥት አቅም በላይ ሆኖ ለያዥ ለገናዥ ሲያስቸግር ከማየት በላይ አሰቃቂ ነገር የለም፡፡ በፌዴራል፣ በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች መረን የተለቀቀው ሌብነት አስነዋሪ መሆኑ...

  ሰላም ዘላቂ የሚሆነው ቃል ሲከበር ብቻ ነው!

  እንደ አለመታደል ሆኖ የሰሜን ኢትዮጵያ አውዳሚ ጦርነት ውስጥ ለሁለት ዓመታት ከተከረመ በኋላ የሰላም መንገድ ተጀምሯል፡፡ በአገር በቀል ሽምግልና ማለቅ የነበረበት ከአገር ውጪ አስጉዞ፣ በባዕዳን...