Tuesday, May 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊገንዘብ ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲዎች የገዛቸውን አውቶብሶች ተረከበ

ገንዘብ ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲዎች የገዛቸውን አውቶብሶች ተረከበ

ቀን:

  • አግታ አውቶብሶችን አገር ውስጥ ሊገጣጥም ነው

በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ሥር ያለው የመንግሥት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ኤጀንሲ፣ ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች 120 አውቶብሶችን ለመግዛት ያወጣውን ጨረታ ያሸነፈው አግታ ኩባንያ፣ 70 አውቶብሶችን የካቲት 3 ቀን 2007 ዓ.ም. አስረከበ፡፡

የአግታ ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ግርማይ ገብረ አረጋዊ የአውቶብሶቹን ቁልፍ ለመንግሥት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይገዙ ዳባ አስረክበዋል፡፡ አግታ ኩባንያ ያስረከበው 70 አውቶብሶችን ሲሆን፣ የተቀሩት 50 አውቶብሶች ወደ አገር ውስጥ እየተጓጓዙ መሆናቸውንና በቅርቡ ርክክብ እንደሚካሄድ አቶ ግርማይ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የቻይና ሥሪት የሆኑት ‹‹ሰንሎንግ›› በሚል ስያሜ የሚታወቁት አውቶብሶች፣ 61 ሰዎችን የመያዝ አቅም አላቸው፡፡ አቶ ግርማይ እንዳሉት እነዚህ አውቶበሶች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የተሟሉላቸው ናቸው፡፡

- Advertisement -

በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ሥር የመንግሥት ትልልቅ ግዢዎችን እንዲፈጸም የተቋቋመው የመንግሥት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ኤጀንሲ፣ የአውቶብሶቹን ግዢ ለመፈጸም ከሦስት ወራት በፊት ጨረታ አውጥቶ ነበር፡፡

በዚህ ጨረታ አግታን ጨምሮ አራት ኩባንያዎች የተወዳደሩ ቢሆንም፣ አግታ ባቀረበው የፋይናንስና የቴክኒክ መሥፈርቶች የተሻለ ሆኖ በመገኘቱ ሥራው ተሰጥቶታል ተብሏል፡፡

አቶ ይገዙ አውቶብሶቹን በተረከቡበት ወቅት፣ ‹‹አውቶብሶቹ በአስቸኳይ ይፈለጉ ነበር፡፡ አግታ በአስቸኳይ አቅርቧል፤›› በማለት ተናግረዋል፡፡ አውቶብሶቹ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የያዙ በመሆናቸው አግታ ለአሽከርካሪዎች ሥልጠና እንደሚሰጥ አቶ ይገዙ አስረድተዋል፡፡

ኤጀንሲው እነዚህን አውቶብሶች ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚያከፋፍል ታውቋል፡፡ አንዱ አውቶብስ 1.7 ሚሊዮን ብር እንደሚያወጣ አቶ ግርማይ ገልጸዋል፡፡ አግታ እነዚህን አውቶብሶች አገር ውስጥ የመገጣጠም ዕቅድ እንዳለውም አስረድተዋል፡፡

እነዚህን አውቶብሶች በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ አካባቢ መገጣጠም የሚያስችል ፋብሪካ ለመገንባት 48 ሚሊዮን ብር በጀት መያዙን አቶ ግርማይ ገልጸው፣ ፋብሪካው ለመገንባት ከቻይናው ኩባንያ ሰንሎንግ ጋር ንግግር እንደተጀመረና ከአዲስ አበባ አስተዳደርም ለግንባታ የሚያስፈልግ ሁለት ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ መገኘቱን  አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...