አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ቅምሻ የተሰኘ አዲስ ጦማር (Blog) በአማርኛና እንግሊዝኛ መጀመሩን አስታወቀ፡፡
ኤምባሲው በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ የጦማሩ ዓላማ ወቅታዊ የሆኑ የኤምባሲውን ተግባራት፤ እንዲሁም ከአሜሪካ ባሕል ጋር ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ለታዳሚው ማድረስ ነው፡፡
ጦማሩ https://usembassyaddis.wordpress.com/ በየሳምንቱ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ቅርበት ያላቸውን የአሜሪካ እሴቶች፣ ባህልና የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ዓላማዎችን የሚያቀርብ ሲሆን፣ ከአንባቢዎቹ ጋር ተቀራርቦ የሚነጋገርበት መድረክም ነው፡፡