Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ፍሬከናፍር‹‹አንዳንድ ጊዜ ስለሰብዓዊ መብት ጉዳዮች መናገር ስንፈልግ ሚዛናችንን መጠበቅ ይኖርብናል››

‹‹አንዳንድ ጊዜ ስለሰብዓዊ መብት ጉዳዮች መናገር ስንፈልግ ሚዛናችንን መጠበቅ ይኖርብናል››

ቀን:

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በህንድ ያደረጉትን የሦስት ቀናት ጉብኝት አጠናቀው ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ማክሰኞ ዕለት ሲያመሩ ከተናገሩት የተወሰደ፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ በሰብዓዊ መብት ጥበቃ ረገድ ደካማ ከሆነችው ሳዑዲ ዓረቢያ ጋር የሚደረገው ግንኙነት መጠናከር አለበት ብለው፣ ነገር ግን ስለሰብዓዊ መብት ጉዳይ ከሳዑዲ ገዥዎች ጋር ንግግር ለማድረግ ሲፈለግ በአካባቢው ያለው አለመረጋጋትና ፀረ ሽብርተኝነት ዘመቻ ታሳቢ መደረግ እንዳለበት አስታውቀዋል፡፡ የሰብዓዊ መብትን ጉዳይ በተመለከተ አንዳንድ ወዳጅ አገሮች ምቾት እንደማይሰማቸውና እንደሚያበሳጫቸው ተናግረው፣ አንዳንዶቹ ቢሰሙም ሌሎቹ ደግሞ ጭራሽ መስማት አይፈልጉም ብለዋል፡፡ የቀድሞ የግብፅ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከማይሰሙት አንዱ እንደነበሩ ጠቅሰው፣ በኋላ ውጤቱ ምን እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ አሁንም ወዳጆችና ተባባሪ አገሮች እየተለወጠ ከሚሄደው ዓለም ጋር አገራቸውን እንዲለውጡ ጥረታቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡ በሳዑዲ ዓረቢያ ላይም ተመሳሳይ አቋም እንዳላቸው ለሲኤንኤን አረጋግጠዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...