Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየፕሪሚየር ሊጉ አንደኛ ዙር በማስተካከያ ጨዋታ እሑድ ይጠናቀቃል

የፕሪሚየር ሊጉ አንደኛ ዙር በማስተካከያ ጨዋታ እሑድ ይጠናቀቃል

ቀን:

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2007 ግማሽ የውድድር ዓመት እሑድ ጥር 24 ቀን 2007 ዓ.ም. ሐዋሳ ላይ ሐዋሳ ከነማ ከደደቢት፣ በድረ ላይ ወላይታ ድቻ ከቅዱስ ጊዮርጊስና በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ኢትዮጵያ ቡና ከመብራት ኃይል ጋር የሚቀሩት ተስካካይ ጨዋታዎች ተደርገው ይጠናቀቃል፡፡ የፕሪሚየር ሊጉ ሁለተኛው ዙር ጨዋታ በመጋቢት ወር መጀመርያ በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚቀጥልም የፌዴሬሽኑ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ወንድምኩን አላዩ ገልጸዋል፡፡ እስካሁን ባለው ፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ሲዳማ ቡና በ27 ነጥብ ሲመራ ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀየረው በ24 ነጥብ ይከተላል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ እሑድ ወላይታ ድቻን የሚያሸንፍ ከሆነ ግን ሲዳማ ቡና በጎል ክፍያ ስለሚበለጥ መሪነቱን ያስረክባል፡፡ በተመሳሳይ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው ኢትዮጵያ ቡና ወላይታ ድቻን በጎል ክፍያ በልጦ ሦስተኛና አራተኛ ሲሆኑ፣ አዳማ ከነማ በ19 አምስተኛ፣ አርባ ምንጭ ከነማ በ19 ነጥብ በጎል ክፍያ ተበልጦ ስድስተኛ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባነክ በ16 ነጥብ ሰባተኛ፣ ዳሸን ቢራና መከላከያ በተመሳሳይ 16 ነጥብ በጎል ክፍያ ተበልጠው ስምንተኛና ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ ደደቢት በ15 ነጥብ 10ኛ፣ መብራት ኃይል በ14፣ ሙገር ሲሚንቶ በ13፣ ሐዋሳ ከነማ በ10 እና በመጣበት አኳኋን ለመመለስ እያኮበኮበ የሚገኘው ወልዲያ ከነማ በ5 ነጥብ ከ11ኛ እስከ 14ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው እንደሚገኙ አቶ ወንድምኩን አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...