Wednesday, June 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየኢትዮጵያዊው የመሐል ዳኛ ብቃት የተመዘነበት 90 ደቂቃ

የኢትዮጵያዊው የመሐል ዳኛ ብቃት የተመዘነበት 90 ደቂቃ

ቀን:

ባለፈው ሐምሌ ወር ላይ ነበር የቱኒዚያው ኢትዋልደ ሳህልና የዛምቢያው ንካና ክለቦች በሉሳካው ኪዊት ስታዲየም በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የጥሎ ማለፍ ግጥሚያ ላይ የተገናኙት፡፡ በመኪና አደጋ ሕይወቱ ላለፈው አሠልጣኛቸው ማሳውሶ ምዋሌ መታሰቢነያነት የኮንፌዴሬሽን ዋንጫውን ማሸነፍ እንዳለባቸው ተገንዝበው ከኢትዋል ደሳህል ጋር የመጀመርያውን የጥሎ ማለፍ ጨዋታ በቱኒዚያ አድርጎ ያለ ውጤት የተመለሰው ንካና፣ በሜዳው የሚያደርገውን ጨዋታ በድል ለመወጣት ታላቅ ተስፋን ሰንቆ ነበር የተመለሰው፡፡ የዚህ ወሳኝ የመልስ ጨዋታ ዳኝነት ደግሞ በኢትዮጵያዊው አርቢትር ባምላክ ተሰማ ላይ የተጣለ ኃላፊነት ነበር፡፡ በከፍተኛ ውጥረት ጨዋታው መካሄዱን ተከትሎ ባለሜዳው ንካና የቱኒዚያውን ቡድን 4 ለ3 በሆነ ውጤት ቢያሸንፍም፣ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ባለመቻሉ ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ የገቡት የዛምቢያ ስፖርት ሚኒስትር ቺሺምባ ካዎብ ዊሊ በጨዋታው ላይ ሁለት አጨቃጫቂ የፍጹም ቅጣት ምት ሰጥተዋል ያሉዋቸውን የመሀል ዳኛ ለድብድብ ተጋበዙ፡፡ የፀጥታ ኃላፊዎች ግን ዳኛውን ከጥቃት ተከላክለው በሰላም ወደ ማረፊያ ክፍላቸው ተሸኝተዋል፡፡ ሆኖም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሸን (ካፍ) የዛምቢያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለኢትዮጵያዊው አርቢትር ተገቢውን ጥበቃ አላደረገም በሚል 10,000 ዶላር የገንዘብ ቅጣት እንደጣለበትም ተዘግቧል፡፡ ይህ ታሪክ በ30ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ አገራቸውን በብቸኝነት ወክለው ባለፈው ሳምንት በምድብ ሁለት ከተካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች መካከል በካሜሩንና በጊኒ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል የተካሄደውን ጨዋታ የመሩትና በ30ዎቹ መጨረሻ ላይ የሚገኙት አርቢትር ባምላክ ተሰማ ናቸው፡፡ ዘለግ ባለ ቁመና ቀጠን ባለ የሰውነት አቋም የሚለዩት አርቢትሩ በፈጣን እንቅስቃሴያቸውም ይታወቃሉ፡፡ አንድ የቢጫ (ማስጠንቀቂያ) ካርድ ብቻ እንደመዘዙበት በተዘገበው የምድብ ሁለት ሁለተኛ ጨዋታ ላይ ያሳዩት ብቃት በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ አድናቆትን አትርፎላቸዋል፡፡ ‹‹በየጨዋታው እንቅስቃሴ ሁሉ የነበራቸው ፍጥነትና ሜዳን ያማከለ ብቃት ልዩ ነበር፤›› ሲል አስተያየቱን የሚሰጠው ጋሻሁን ዓለማየሁ፣ እንደ ስፖርት ተመልካችነቱ ‹‹ምርጥ ብቃት›› ሲል ስለገለጸው የአልቢትሩ ዳኝነት ይናገራል፡፡ ከዚህ በተቃራኒው ግን የአርቢትሩን የተጋነነ እንቅስቃሴና በተለየ በጭማሪ ደቂቃዎች ላይ ሊሰጡ ይገባ ነበር የተባለውን የፍጹም ቅጣት ምት መንስዔ የሚያስታውሱ ተመልካቾች፣ አርቢትሩ መልካም ዳኝነትን ቢያሳዩም ግልጽ ስህተት ፈጽመዋል፤›› ሲሉ ተችተዋል፡፡ በጭማሪው ሰዓት የመሐል ዳኛው ከፍጹም ቅጣት ምት ክልል ብዙ ርቀው በመሄዳቸው በፍጥነት የተመለሰችውን ኳስ ይዞ በካሜሩን የግብ ክልል ውስጥ የገባውን የጊኒ ተጨዋች ጠልፎ የጣለውን የካሜሩኑን ተከላካይ ጥፋት መመልከት ባለመቻላቸው ጊኒዎች የሚገባቸውን ሦስት ነጥብ እንዳያገኙ አድርገዋቸዋል ሲሉም ይተቻሉ፡፡ ይሁንና እኚሁ ተመልካች በጠቅላላ የመዘኑትን የአርቢትሩን ብቃት ሲገልጹ፣ ‹‹መልካም የሚባል›› በሚል ድምዳሜ ነው፡፡ በተለይ ለብዙኃኑ የእግር ኳስ ተመልካች ተለይቶ የተገለጠለት የአርቢትሩ ብቃት ሜዳ ሙሉ አካሎ የመሮጥ አቅም ሲሆን፣ ይህም በሠለጠነው አህጉር አውሮፓ እንኳን ተዘውትሮ የሚታይ ባለመሆኑ ሊያስመሰግናቸው ይገባል ባይ ናቸው፡፡ ሆኖም ግን የአርቢትሩ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በስህተት ኳስ እንዲነኩና ይህም ወሳኝ እንቅስቃሴዎችን እንዳያስገታቸው ሥጋት እንዳደረባቸው የሚገልጹት ደግሞ ‹‹ሩጫውን መጠን በማድረግ በቆሙበት ቦታ አብዛኛውን የሜዳ ክፍል አካቶ የማየትን ልምድ ሊያካብቱ ይገባል፤›› ሲሉ አስተያየታቸውን ይቋጫሉ፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ ከሚገኙ ጥቂት አርቢትሮች አንዱ የሆኑት ባምላክ ተሰማ፣ በዕለቱ ጨዋታውን ያስተላልፉ በነበሩት ዘጋቢዎችም አድናቆት የተቸራቸው ሲሆን፣ ከፍተኛ እንቅስቃሴያቸውንም ከምሥራቅ አፍሪካውያን የአትሌቲክስ ተክለ ሰውነት ጋር አነፃፅረውት ነበር፡፡ አርቢትሩ በቀጣይ ሌላ የሚዳኙት ጨዋታ ይኑር አይኑር በትክክል ማወቅ ባይቻልም፣ በዕለቱ ከነበራቸው ጥሩ የሚባል ብቃት ጋር ተያይዞ ተጨማሪ ጨዋታውን እንደሚዳኙ ይጠበቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...