Wednesday, June 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰሞኑን አዘጋጅቶት በነበረው የውጪ ንግድ ቀን ላይ 8100 A...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰሞኑን አዘጋጅቶት በነበረው የውጪ ንግድ ቀን ላይ 8100 A ሲልኩ

ቀን:

ከግራ ወደቀኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዓለም አቀፍ ንግድ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ መሐመድ ኑረዲን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት በቃሉ ዘለቀ እንዲሁም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ታደሰ ኃይሌ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰሞኑን አዘጋጅቶት በነበረው የውጪ ንግድ ቀን ላይ 8100 A ሲልኩ

******

መቼም የማይሻር ታላቅ ንጉሥ ሁሉንም የሚጥል ሁሉን የሚያነሳ ጊዜ ነው፣ ወቅት ነው፡፡ ከወደቁ ኋላ ዳግም ለመነሳት ምክንያቱ ዘመን ነው፡፡ ነገር ግን በጊዜ ምክንያት ሕይወት የምንላት ለአንደኛው ድህነት ለሌላኛው ሀብት መሆኗን ሲያስተውል ባለ ፀጋ ያርምም አብዝቶ ዝም ይበል!! ምክንያቱም በሀብቱ በከብቱ ትምክህትን ሊያደርግ ለርሱ አይገባም፡፡ (ደግሞም) በጊዜ ምክንያት ፍፁም የቸገረው ያጣ ድሀም ቢኖር አይዘን አያልቅስ አምላኩን አያማር፡፡ በዚህ መሀል ግና ለምንድን ነው ብሎ የሚጠይቅ ሰው ካለ እኛም እንላለን ዘመን እንዳነሳ ዘመን እንደ ጣለ ያነሳውን ሲጥል የጣለን ሲያነሳ መቼም የማይሻር ጊዜ የምንለው ታላቅ ንጉሥ አለ፡፡ – ኤፍሬም ሥዩም ተሰማ ‹‹ተዋነይ ብሉይ የግዕዝ ቅኔያት ፍልስፍና›› (2006)

******

ሐሳብ እና ባሕር ‹‹ሰው በልቡ የሚያስበውን ነው የሚሆነው›› ይህ አባባል የሰውየውን አጠቃላይ ማንነት ብቻ ሳይሆን የሚያቅፈው በሰውየው ሕይወት ውስጥ ያሉትን ማንኛቸውንም ሁኔታዎችና ክስተቶች በሙሉ ያጠቃልላል፡፡ ሰው የሚያስበውን ነው የሚሆነው፣ ባህሪውም የሁሉም ሐሳቦቹ አጠቃላይ ድምር ውጤት ነው፡፡ ተክል ከዘር እንጂ ያለ ዘር እንደማይበቅል ሁሉ የሰውም እያንዳንዱ ድርጊት ከተደበቀው የሰውየው የሐሳብ ዘር ይመነጫል፡፡ ከነዚህ ሐሳቦችም ውጭ ሊገለጥ አይችልም፡፡ ይህም ነገር ሆን ተብሎ በሚደረጉ ነገሮች ላይ ተግባራዊ የሚሆነውን ያህል ሳይታሰብ በድንገት በሚደረጉና ባለማወቅ በሚደረጉ ነገሮች ላይ እኩል ተግባራዊ ይሆናል፡፡ ድርጊት የሐሳብ ችግኝ ነው፤ ደስታና ስቃይም የሐሳብ ፍሬዎች ናቸው፤ የሰው ልጅም መራራውንም ሆነ ጣፋጩን ፍሬ ከራሱ የሐሳብ እርሻ ይሰበስባል፡፡ የሠራን በአዕምሮአችን ውስጥ ያለ ሐሳብ ነው፣ እኛ የተሠራነውና የተገነባነው በሐሳብ ነው፣ የሰውየው አዕምሮ መጥፎ ሐሳብ ካለው፣ ጋሪው ከፈረሱ ኋላ እንደሚመጣው፣ ሕመም በእርሱ ላይ ይመጣበታል፡፡ ነገር ገን በንፁህ ሐሳብ ፀንቶ ለሚኖር ሰው፣ በእርግጠኝነት ደስታ እንደጥላ ከኋላው ይከተለዋል፡፡ የሰው ልጅ በሕግ የሚያድግ እንጂ ሰው ሠራሽ ውጤት ስላልሆነ በተደበቀው የሐሳቡ ማዕቀፍ ውስጥ የሚገኙት ምክንያቶችና ውጤቶች በሚታየው ዓለምና በቁሳዊ ነገሮች ላይ ፍፁም ሆነውና ሳይዛነፉ ይከሰታሉ፡፡ ታላቅና አምላካዊ ባህሪ ያለማቋረጥ ከሚደረግ የትክክለኛ አስተሳሰብ ጥረትና ከአምላካዊ ሐሳቦች ጋር ለረዥም ጊዜ በሚደረግ ጥምረት የሚመጣ ተፈጥሮአዊ ውጤት እንጂ እንዲሁ በአጋጣሚ ወይም በዕድል የሚገኝ አይደለም፡፡ ሰው ትክክለኛ የሆነ ሐሳብን በመምረጥና በትክልል ተግባራዊ በማድረግ ወደ መለኮታዊነት ያደርጋል፤ የተበላሸና የተሳሳተ ሐሳብን በመተግበርም ከእንስሳነት ወደ አነሰ ደረጃ ይወርዳል፡፡ ሁሉም ዓይነት የባህሪ ደረጃዎች በእነዚህ ሁለት ጽንፎች መካከል ውስጥ ይገኛሉ፤ የእነዚህ ባህሪዎች ፈጣሪና አዛዥ ደግሞ ሰው ነው፡፡ ከነብስ ጋር በተያያዘ ካሉ መልካም ነገሮች ሁሉ ይህንን ዘመን ብሩህ ለማድረግ ተመልሰው ተግባራዊ መሆን ካለባቸው ነገሮች ሁሉ ከዚህ የተሻለ አስደሳች፣ ውጤታማና አስተማማኝ የሆነ መለኮታዊ ተስፋ የለም፡፡ ይህ የሰው የሐሳብ አዛዥ፣ የባህሪ ቀራፂ፣ የሁኔታዎች፣ የአካባቢና የዕጣ ፈንታ ሠሪና ቅርፅ አስያዥ መሆኑ ነው፡፡ ሰው እንደሚኖረው ኃይል ዕውቀትና ፍቅር እንዲሁም የሐሳቡ ጌታ እንደመሆኑ የማንኛውም ሁኔታ ቁልፍ ይዟል፤ እንዲሁም የፈለገውን ለማድረግ ራሱን የሚያሸጋግርበትና ተሐድሶ የሚያካሂድበትን ድርጅትም በውስጡ ይዟል፡፡ ሰው ሁሌም በደካማና ብቸኛ በሆነበት ሁኔታ ውስጥ እንኳ ሆኖ የራሱ ባለቤት ነው፡፡ ነገር ግን ከክብሩ በወረደበት ጊዜ ቤቱን በትክክል ማስተዳደር እንዳልቻለ ጅላጅል አዛዥ ነው፡፡ የራሱን ሁኔታ ማንፀባረቅ በሚጀምርበትና ማንነቱ የተመሠረተበትን ሕግ ለማግኘት በትጋት ለመፈለግ ሲጀምር ግን ኃይሉን በዕውቀት የሚመራና ሐሳቦቹን ውጤታማ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሚያደርግ ጥበበኛ አዛዥ ይሆናል፡፡ ሰው እንደዚህ ዓይነት ንቁ አለቃ መሆን የሚችለው በውስጡ ያሉ የሐሳብ ሕጎችን ሲያገኝ ብቻ ነው፡፡ በአጠቃላይ ይህን ሕግ ማግኘት ግን የተግባራዊነት፣ ራስን የመፈተሽና የልምድ ጉዳይ ነው፡፡ ወርቅና አልማዝ በብዙ ፍለጋና ቁፋሮ እንደሚገኙት ሁሉ ሰውም ከራሱ ጋር በተያያዘ ማንኛውንም እውነት ማግኘት የሚችለው በነብሱ የማዕድን ሥፍራ ላይ በጥልቀት ሲቆፍር ነው፡፡ ይህም ማለት ሰው የራሱን ባህሪ ሠሪ፣ የሕይወቱ ቀራፂ፣ የወደፊት ዕጣ ፈንታው ገንቢ መሆኑን በትክክል ማረጋገጥ የሚችለው፤ ሐሳቦቹን ሲያስተውል፣ ሲቆጣጠርና መለዋወጥ ሲችል፣ እንዲሁም ሐሳቦቹ በራሱ፣ በሌሎች ሰዎች፣ በሕይወቱና በሁኔታዎች ላይ የሚኖራቸውን ተፅዕኖ ምክንያትና ውጤትን በመመርኮዝ በሚያደርገው ትዕግሥታዊ ትግበራና ምርምር ለይቶ ሲያውቅ ብቻ ነው፡፡ እንዲሁም ማንኛውም ልምዱን በጣም ተራና የዕለት ከዕለት ክስተት የሆነውንም ቢሆን በመጠቀም ስለ ራሱ ጥበብና ኃይል ያለውን ዕውቀት የሚያገኝበትን መንገድ ይፈጥራል፤ ‹‹ፈልጉ ታገኛላችሁ አንኳኩ ይከፈትላቹኋል›› የሚለው ሕግ ፍፁም የሚሆነው በዚህ እንጂ በሌላ በየትኛውም አቅጣጫ አይደለም፡፡ ሰው ወደ ዕውቀት ቤተ መቅደስ መግባት የሚችለው በትዕግሥት በሚያደርገው ልምምድና ያለ ማቋረጥ በሚያደርገው ጥረት ብቻ ነው፡፡ – መክብብ አበበ ‹‹ሰውና ሐሳቡ›› (2007)

******

ጆርጅ ኢሊዬት ብዙ ሰዎች ‹‹ጆርጅ ኢሊዬት›› የሚለውን ስም ሲያነቡ የወንድ ስም ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን የሜሪ አን በኋላም የማሪያም ኢቫንስ የብዕር ስም ነው፡፡ በዓለም ዝናዋ ገኖ የሚነገርላት የብዙ መጻሕፍት ደራሲ የሆነችው ጆርጅ ኢልዬት የሮበርት ኢቫንስ የመጨረሻ ልጅ ስትሆን ከ1819 እስከ 1880 የኖረች እንግሊዛዊት ናት፡፡ ጆርጅ ኢሊዬት በብዙ ነገሮች የምትጠቀስ ብትሆንም የሚከተሉን ጥቅሶችዋ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡ – ማንኛውም ቱርቂ (ፈሪ) እንደሚያሸንፍ ሲያውቅ ሊዋጋ ይችላል፡፡ እኔ ግን የምሻው ለመሸነፍ ዝግጁ የሆነውን ነው፡፡ – ተቃውሞ ለሰው ልጅ የምትጣፍጠው የምታስከትለውን ሰቆቃ እንደሰማዕት የተቀበለ እንደሆነ ነው፡፡ – በዚሁ ዓለም ላይ ተጠቃሚ የሚሆኑት ብልጦች ናቸው፡፡ – ሰዎችን ፈጣሪ ይቅርታ እንዲያደርግላቸው ለእርሱ አሳልፈን እንሰጣቸዋለን፡፡ እኛ ግን ይህንን አናደርግም፡፡ – ደስተኛ ሴት እንደ ደስተኛ አገር ታሪክ የላትም፡፡ – አንድ ነገር በመጀመርያ ስናየው የሚመስለንን ያህል በኋላ አይሆንም፡፡ – የአገራችን ሰዎች ችግር ከማወቂያ ዘዴዎች አንዱ ደስታን ከሚያሳልፉበት ቦታ ሄዶ ማየት ነው፡፡ – ተሾመ ብርሃኑ ከማል ‹‹የዓለማችን ታላላቅ ሰዎች እና ጥቅሶቻቸው›› (2007)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ በተመደበው ኢትዮጵያዊ ዳኛ ላይ ሥጋት እንዳለው የግብፅ ክለብ አስታወቀ

ክለቡ ዳኛው ‹‹የጡረታ መውጫው የመጨረሻ ጨዋታ›› መሆኑ አሳስቦኛል ብሏል የ2023...

የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ከሕገ መንግሥቱ ውጪ በተግባር እንደሌለ ፓርቲዎች ተናገሩ

ብልፅግና ስለመድበለ ፓርቲ ለውይይት ጥሪ ቢደረግለትም አልተገኘም በኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ...

ሒዩማን ራይትስዎች ያወጣው ሪፖርት የዕርቅና የምክክር ሒደቱን እንደሚያደናቅፍ መንግሥት አስታወቀ

በትግራይ የሰላም ስምምነት ተግባራዊ በሚደረግበት ወቅት የዘር ማፅዳት እየተካሄደ...

የመጪው ዓመት አገራዊ በጀት ሁለት በመቶ አድጎ ለፓርላማ ተመራ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2016 ዓ.ም. በጀት እየተጠናቀቀ ካለው በጀት...