Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅከአዲስ አበባ በ600 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በኦሮሚያ ክልል በመቱ ከተማ...

ከአዲስ አበባ በ600 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በኦሮሚያ ክልል በመቱ ከተማ ለአምስተኛ ጊዜ የቡናና ማር ቀን ተከብሯል::

ቀን:

ከአዲስ አበባ በ600 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በኦሮሚያ ክልል በመቱ ከተማ ለአምስተኛ ጊዜ የቡናና ማር ቀን ተከብሯል:: በዚሁም ዕለት 54 ሌትር ውኃ፣ 11 ኪሎ ግራም ቡና እንዲሁም 432 ሲኒ የሚይዝ ረከቦት ተሠርቶ ቀርቧል:: በጅማ ተሠርቶ የነበረውን 400 ሲኒ የሚይዘው ረከቦት ሪከርድ የመቱ ከተማው ሰብሯል:: ፎቶ በመስፍን ሰለሞን * * * አስማታዊ ኃይል አገኛለሁ ብሎ አባት አምስት ልጆቹን ገደለ በፓኪስታን ከካራቺ 230 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሳይድካሀን በሚሰኝ መንደር ነዋሪ የነበረው አሊ ናዋዝ ለግሀሪ የስድስት ልጆች አባት ሲሆን፣ አስማታዊ ኃይል እንድላበስ ያስችለኛል ብሎ በማመን አምስት ልጆቹን መግደሉን ባለፈው ሳምንት ማብቂያ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ የአርባ ዓመቱ አሊ ናዋዝ የኑሮ ሁኔታው ጥሩ እንዳልነበርና አስማት መሥራት ሲሠለጥን መቆየቱን የተናገሩት የፖሊስ ኦፊሰር ካማሩሲን ራሒም በመጨረሻም የተሻለ አስማታዊ ብቃት ይጨምርልኛል በሚል ልጆቹን ሳይገድል እንዳልቀረ አብራርተዋል፡፡ ለገሪሀሪ መጀመሪያ ቤተሰቡን ለመግደል አቅዶ የነበረው እራት ላይ ቤተሰቡ የሚመገበውን ምግብ በመመረዝ ነበር፡፡ ነገር ግን መርዙን ምግብ ላይ ለመጨመር ሲሞክር ባለቤቱ ስላየችው ኃይለኛ ግጭት ተፈጠረ፡፡ በዚህም ሚስትየው የመጀመሪያ ወንድ ልጃቸውን ይዛ ከቅርብ ጎረቤት ዘንድ አደሩ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ነበር ለገሀሪ ከቤት የቀሩትን አምስቱን ልጆች እያነቀ የገደላቸው፡፡ ነርሱ 30 ሕሙማንን መግደሉን አመነ ነርስ የነበረ የ38 ዓመት ግለሰብ ከመጠን ያለፈ የልብ መድኃኒት በመስጠት 30 የሚሆኑ ሕመምተኞችን እንደገደለ ለፍርድ ቤት ማመኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ግለሰቡ ይህን የተናዘዘው ለፍርድ ቤቱ ሳይካትሪ ነበር፡፡ ነርሱ ለህልፈት የዳረጋቸወ ሕመምተኞች ከመጠን ያለፈ የልብ ህመም መድኃኒት ተወግተዋል የተባለው እ.ኤ.አ. ከ2003 እስከ 2005 ጊዜ ውስጥ ሲሆን፣ ተጨማሪ 60 ሰዎችን መድኃቱን ወግቶ የነበረ ቢሆንም ሕይወታቸው ሊተርፍ ይችላል፡፡ ፖሊስ ከነርሱ ጋር በተያያዘ የመቶ ሰዎችን አሟሟት በማጣራት ላይ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡ ተከሳሹ ሕሙማኑ በዋነኝነት የልብ ምታቸውን የሚያፋጥንና ከፍተኛ የደም ግፊት እንዲፈጠር የሚያደርግ መርፌ ይሰጣቸው እንደነበረም ዘገባው ይጠቁማል፡፡ * * * ለምን ያለቅሳሉ እንዲያው ስንከራተት እንደውም ስማቅቅ በጣሙን ጓጉቼ በሽታዬን ላውቅ መታከሚያ ሳጣ ያልጠየቀኝ ሁሉ ከሞትኩኝ በኋላ ለምን ያለቅሳሉ እኛ ዘመዶቼ ወንድሜም እህቴ ቢያሳዝንም እንኳ እጅግ አሟሟቴ ኡኡታ እዬዬ! ምንም አይረባኝም ለመንገዴ ቢሆን ስንቅም አይሆነኝም ለኔ የሚረባኝ የሚጠቅመኝ ነገር ታምሜ ስተኛ በጠየቁኝ ነበር ከድንጋይ መወርወሩ አፈር መከመሩ አሁን ምን ያደርጋል አልቅሶ መቅበሩ ለኔ የሚረባኝ የሚጠቅመኝ ነገር ታምሜ ስተኛ ቢጠይቁኝ ነበር ታምሜ ስተኛ ያልጠየቁኝ ሁሉ ከሞትኩኝ በኋላ ለምን ያለቅሳሉ መቅደስ ተስፋዬ ‹‹አፍላ ብዕር›› 2002 ዓ.ም. ከበረራ በፊት በረራ ከማድረግዎ አንድ ቀን ቀደም ብለው የዘወትር ፕሮግራምዎን ይቀይሩና ተግባርዎን ሁሉ ከሚሄዱበት አገር የሰዓት አቆጣጠር ጋር በአንድ ሰዓት አቀራርበው (One Hour Closer) ያከናወኑ፡፡ የምግብ፣ የመኝታ፣ ወዘተ ጊዜዎን ሁሉ በዚሁ መሠረት ያስተካክሉ፡፡ በበረራ ላይ ልክ አውሮፕላኑ ውስጥ እንደገቡ ሰዓትዎን በመድረሻው አገር ሰዓት ያስተካክሉ፡፡ አልኮልና የሰውነትን ውኃ ውግደት የሚያባብሱ መጠጦችን አይጠጡ፣ ይልቁንም በየአንድ ወይም ሁለት ሰዓት አንዳንድ ብርጭቆ ውኃ ይጎንጩ፡፡ ቅባት የበዛባቸውና የሚከብዱ ምግቦችን ከመመገብ ይቆጠቡ፣ ከተቻለም ድረስ ቢተኙ መልካም ነው፡፡ መድረሻ ካቀዱበት አገር በደረሱበት ዕለት ሥራ ባይሠሩና አርፈው ቢውሉ ይመረጣል፡፡ ለረዥም ሰዓት ባይተኙም የሻለ ነው፡፡ መኪና የሚነዱም ከሆነ በጥንቃቄ ያሽከርክሩ፡፡ እግረኛም ከሆኑ መንገድ ሲያቋርጡ በሚገባ ያስተውሉ፡፡ አቪዬሽን፣ 1982 ዓ.ም. * * * ጉብኝት በመገናኛ ብዙኃን አልያም በሌላ መንገድ የሚተዋወቁ ሥፍራዎች አንዳንዴ እንደሚወራላቸው ሆነው አለመገናኘታቸው እሙን ነው፡፡ በኢንዲፔንደንት ድረ ገጽ ላይ የተለያዩ ግለሰቦች ጐብኝተዋቸው ከጠበቁት በታች የሆኑባቸው ቦታዎች ዘርዝረዋል፡፡ – ፓሪስ – የጉዞ እክል የገጠማቸውን ጃፓናዊ ቱሪስቶች መልዕክት ያነበበ ግለሰብ ‹‹እጅግ አበሳጭ ከመሆኑ የተነሳ በሽታ ያስይዛል፤›› ብሏል፡፡ – ባሊ – ቦርሳ በጀርባቸው ያነገቡ ሰዎች ለመመልከት ለሚወድ ሰው ካልሆነ ተስፋ አስቆራጭ ነው፡፡ – ማቹ ፒቹ – ማራኒ አቀማመጥ ቢኖረውም ሕንፃዎቹ የተበላሸ መንደር እንደሚመስሉ የገለጸ ጐብኚና ያረጁና የማያስደስቱ ድንጋዮች የጐብኚ ቁጥር በቀላሉ ሊበልጣቸው ይችላል የሚል አስተያየት የሰጠ ግለሰብ ይጠቀሳል፡፡ – የአየርላንዱ ጃሮንትስ ካውስዌይ – ሳሙኤል ጆንሰን የተባለ ግለሰብ ‹‹መታየት የሚገባው ቢሆንም ቦታው ድረስ ለመመልከት መሄድ አይመጥነውም፤›› ብሏል፡፡ – የኮሎምቢያው ካርታጌና – ሁለት ውብ መንገዶች ቢኖሩም በአንድ ጊዜ ወደ ርካሽ መገበያያ መንደር ይለወጣሉ – የኢየሩሳሌም ሆሊ ሴፑልቼሬ ‹‹እንኳንም ትልቅ ነገር ጠብቄ ያልነበረ›› ያለው ሮበርት ዚውተን ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...