Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናከሦስት ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩት የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ኃላፊዎችና ሠራተኞች...

ከሦስት ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩት የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ክስ ተመሠረተባቸው

ቀን:

  • በቁጥጥር ሥር የዋሉት በ53 ሚሊዮን ብር ጉዳት ተጠርጥረው ነበር

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋናና ምክትል ሥራ አስኪያጆችን ጨምሮ 26 ሠራተኞች ተጠርጥረው የታሰሩት ከ53 ሚሊዮን ብር በላይ በመንግሥትና ሕዝብ ላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው ቢሆንም፣ ዓርብ ጥቅምት 17 ቀን 2010 ዓ.ም. ግን ከሦስት ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ክስ የተመሠረተባቸው የኤጀንሲው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት አየለ (በሌሉበት)፣ ምክትል ሥራ አስኪያጁ አቶ ታደለ ደመኮ፣ የደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀምና ማስወገድ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ነጋ ፋንታሁን፣ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ዓለማየሁ ነሜ፣ የግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ኃላፊ አቶ ኤርሚያስ ግርማና ሌሎች 21 የተለያየ የሥራ ድርሻና ኃላፊነት ላይ የነበሩ ሠራተኞች ናቸው፡፡

ክሱን የሚመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ለተከሳሾቹ ክሱ እንዲደርሳቸው ካደረገ በኋላ በንባብ ለችሎቱ እንዳሰማው፣ ተከሳሾቹ የተሰጣቸውን ሥልጣንና ኃላፊነት ተጠቅመው የማይገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ ከመመርያ ውጭ ግዥ እንዲፈጸም አድርገዋል፡፡ የአስተዳደሩ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የግዥ አፈጻጸም መመርያ ቁጥር 3/2002 ቁጥር 5 መሠረት ግዥ መፈጸም አለመፈጸሙን ማረጋገጥ ቢኖርባቸውም፣ አለማድረጋቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ዘርዝሯል፡፡ ግዥ መፈጸም ያለበት በመመርያው አንቀጽ 14(2) መሠረት ሆኖ እያለ ያንን ሳያረጋግጡና የመወዳደሪያ ዋጋ ሳይቀርብ፣ ደረቅ ቆሻሻ ከምንጩ ለመለየት የፕሮጀክት ጥናት መረጃ ለማጠናቀር፣ ለመተንተንና የጥናት ጽሑፍ ለማዘጋጀት በማለት ያልተገባ ጥቅም ማግኘታቸውንም ክሱ ያስረዳል፡፡

ተከሳሾቹ የግዥ መመርያውን በመተላለፍ የተለያዩ ግዥዎችን በመፈጸም ለተለያዩ ድርጅቶች ከዋጋ ተመን በላይ ወይም ዕቃው ሊያወጣ ከሚችለው ዋጋ በላይ ክፍያ መፈጸማቸውንም ክሱ ይገልጻል፡፡ በተከሳሾቹ ላይ 12 ክሶች የቀረቡባቸው ሲሆን፣ ተከሳሾቹ የመንግሥትን ሥራ በማያመች አኳኋን በመምራት በአጠቃላይ ከሦስት ሚሊዮን ብር በላይ በመንግሥት ላይ ጉዳት በማድረሳቸው የሙስና ክስ ተመሥርቶባቸዋል፡፡

ተከሳሾቹ የተከሰሱበት ወይም የወንጀል ሕግ ዋስትና እንደማይከለክል በማስረዳት ዋስትና እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል፡፡ ዓቃቤ ሕግ ዋስትናውን ተቃውሟል፡፡ ፍርድ ቤቱ በችሎት ከተገኙት ውስጥ አቶ ታደለ ደመኮ፣ አቶ ነጋ ፋንታሁንና አቶ ዓለማየሁ ነሜን ዋስትና ነፍጎ ሌሎቹ በዋስ እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ የክስ መቃወሚያ ካላቸው ለመጠባበቅ ለጥቅምት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...