Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአክሰስ ሪል ስቴት ቤት ገዥዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቤቱታ ልናቀርብ ነው አሉ

የአክሰስ ሪል ስቴት ቤት ገዥዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቤቱታ ልናቀርብ ነው አሉ

ቀን:

  • የሞግዚት አስተዳደር እንዲቋቋም ሐሳብ ያቀርባሉ

በአቶ ኤርሚያስ አመልጋ መሥራችነት ከተቋቋመው አክሰስ ሪል ስቴት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሙሉ፣ ግማሽና የተወሰነ ክፍያ በመፈጸም ቤት የተመዘገቡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አቤቱታቸውን ለማሰማት ፊርማ እያሰባሰቡ መሆኑን ለሪፖርተር አስታወቁ፡፡

ከ300 በላይ የሚሆኑ ቤት ገዥዎች ፊርማቸውን እንዳሰባሰቡና ሌሎች ቤት ገዥዎችንም እያፈላለጉ መሆኑን የገለጹት አስተባባሪዎችና ቤት ገዥዎች እንደገለጹት፣ ከሰባት ዓመታት በፊት ክፍያ ፈጽመው ከነገ ዛሬ ቤት እናገኛለን እያሉ በጉጉት መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡

ከ2005 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ መንግሥት ጣልቃ በመግባት በትዕግሥት ጠብቀው አንድ ነገር ላይ ለመድረስ ሲጠባበቁ ቢቆዩም፣ ምንም ዓይነት ውጤት እንዳላገኙ ተናግረዋል፡፡ የአክሲዮን ማኅበሩ መሥራች አቶ ኤርሚያስ ከዚሁ የቤት ግዢ ጋር በተገናኘ ለእስር ተዳርገው እንደበር ያስታወሱት ቤት ገዥዎቹ፣ ከእስር ከተፈቱ በኋላ ቤቶቹን ገንብተው ለማስረከብ ጥረት ቢጀምሩም አደናቃፊዎች በመፈጠራቸው ተስፋቸው እንደጨለመባቸው ጠቁመዋል፡፡

አክሰስ ሪል ስቴት ኩባንያን በማመን ክፍያ መፈጸማቸውን የገለጹት ቤት ገዥዎቹ፣ የችግሩን ሁኔታ ተረድቶ ጣልቃ ገብቶ የነበረው መንግሥት ጉዳያቸውን ዳር እንዲያደርስላቸው ጠይቀዋል፡፡ በመሆኑም ሪል ስቴት ኩባንያው የገዛቸው ቦታዎችና የጀመራቸው ሕንፃዎች በመኖራቸው፣ መንግሥት በባለሙያዎች የተደራጀ ጊዜያዊ የሞግዚት አስተዳደር አቋቁሞ፣ ችግራቸውን እንዲቀርፍላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያምን እንደሚማፀኑ ገልጸዋል፡፡

አሁን ባለው የኮንስትራክሽን ዋጋ ያሉትን መሬቶች ተረክበው ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶች መገንባት እንደማይችሉ የሚናገሩት ቤት ገዥዎቹ፣ ከአክሰስ ሪል ስቴት ኩባንያ ጋር በጋራ ለማልማት ከቀረቡ ወይም ከሚጠይቁ የውጭ ኩባንያዎች ጋር በመዋሀድ፣ ያለምንም ተጨማሪ ወጪ ቤታቸው እንዲሠራላቸው እንደሚጠይቁም ገልጸዋል፡፡

ቤት ገዥዎቹ በስማቸው ‹‹የቤት ገዢዎች ዓብይ ኮሚቴና ቋሚ ኮሚቴ›› በማለት ተሰባስበው የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን እንደማያውቋቸው ተናግረው፣ በእነሱ ገንዘብና ወጪ ኑሯቸውን ከመምራት ያለፈ ተግባር ስለሌላቸው አርፈው እንዲቀመጡ መንግሥት ትዕዛዝ እንዲያስተላልፍላቸው እንደሚጠይቁም አስረድተዋል፡፡ እስካሁን የአክሰስንና የቤት ገዥዎችን ስም በመጠቀም ላባከኑት ገንዘብ በሕግ እንደሚጠይቁም አክለዋል፡፡

አቶ ኤርሚያስ ከወራት በፊት ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ መንግሥት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ዕድሉን ቢሰጣቸው፣ ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ ለቤት ገዥዎች ቤቱን ገንብተው ማስረከብ እንደሚችሉ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ ከመንግሥት ኃላፊዎች ጋር በተደጋጋሚ ባደረጉት ውይይት ችግሩን የሚያስተካክሉ ከሆነ ዕድሉ ሊሰጣቸው እንደሚችል መጠቆማቸው አይዘነጋም፡፡

ከአክሰስ ሪል ስቴት ቤት ለመግዛት ክፍያ የፈጸሙ ደንበኞች ከሁለት ሺሕ በላይ ሲሆኑ፣ በአጠቃላይ ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ መክፈላቸው ይታወቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...