Monday, December 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጣዊ ሹም ሽር አደረገ

  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጣዊ ሹም ሽር አደረገ

  ቀን:

  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለያዩ የዲፓርትመንት ኃላፊዎች ላይ ውስጣዊ ሹም ሽር ማድረጉን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

  በዚህም መሠረት የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ ከኃላፊነታቸው ተነስተው፣ የጎረቤት አገሮች ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ መለስ ዓለም በቃል አቀባይነት መሾማቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

  አቶ መለስ የጎረቤት አገሮች ዳይሬክተር ከመሆናቸው በፊት፣ የሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት አማካሪ ሆነው አገልግለዋል፡፡ አቶ መለስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ከመቀላቀላቸው በፊት በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት በኃላፊነት የሠሩ ሲሆን፣ ሪፖርተርን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ጋዜጦች ላይ የተለያዩ መጣጥፎችን ያበረክቱ ነበር፡፡

  ከዚህ በተጨማሪ በአውሮፓ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል አቶ ካሳ ገብረ ዮሐንስ ምትክ፣ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ መሾማቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በፊት አምባሳደር ተስፋዬ በቻይና የኢትዮጵያ ምክትል አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል፡፡ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት ደግሞ፣ በኮትዲቫር የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት ዶ/ር የሺመቤት መብራት መሆናቸው ታውቋል፡፡

  በአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል በነበሩት አቶ መታሰቢያ ታደሰ ምትክ ወ/ሮ ሉሊት ዘውዴ ተሹመዋል፡፡ ወ/ሮ ሉሊት ከዚህ በፊት የኢንስፔክሽን ዳይሬክተር ጄኔራል ሆነው ሲያገለግሉ ነበር፡፡

  በኡጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አምባሳደር ደግፌ ቡላ ደግሞ የዕቅድ ዳይሬክተር ጄኔራል ሆነው ሲሾሙ፣ በአየርላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌላዓለም ገብረ ዮሐንስ የግዢ ዳይሬክተር ጄኔራል ሆነው ተሹመዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በግብፅ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አምባሳደር መሐመድ ድሪር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አማካሪ ሆነው ተሹመዋል፡፡

  በሌላ በኩል የኢጋድ ጉዳዮች ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ብርሃነ ፍሰሐ የጎረቤት አገሮች ጉዳይ ዳይሬክተር ጄኔራል ሆነው ተሹመዋል፡፡ ከዚህ ቀደም የጎረቤት አገሮች ጉዳይ ዳይሬክተር ጄኔራል ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አምባሳደር ግርማ ተመስገን ደግሞ፣ በኮትዲቫር የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል፡፡

  (ለዚህ ዘገባ ዮሐንስ አንበርብር አስተዋጽኦ አድርጓል)

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...