Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናአቶ በረከት ስምኦን ያቀረቡትን መልቀቂያ መንግሥት እየተመለከተው ነው

አቶ በረከት ስምኦን ያቀረቡትን መልቀቂያ መንግሥት እየተመለከተው ነው

ቀን:

ላለፉት 26 ዓመታት በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት በኃላፊነት የቆዩት ነባሩ የኢሕአዴግ አመራር አቶ በረከት ስምኦን፣ ሰኞ ጥቅምት 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ከኃላፊነተቸው በገዛ ፈቃዳቸው ለመልቀቅ ያቀረቡትን ጥያቄ መንግሥት እየተመለከተው መሆኑ ተገለጸ፡፡

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳረጋገጡት፣ በሚኒስትር ማዕረግ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙት አቶ በረከት ከኃላፊነታቸው ለመነሳት ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ደብዳቤ አስገብተዋል፡፡ ከኃላፊነታቸው ለምንና በምን ምክንያት እንደሚለቁ ግን አለመታወቁን ሚኒስትሩ አክለዋል፡፡

አቶ በረከት የማስታወቂያ ሚኒስትር፣ የመጀመርያው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር የጠቅላይ ሚኒስትር አማካሪ ሆነው የሠሩና አሁን ደግሞ በሚኒስትር ማዕረግ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው በማገልገል ላይ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

አቶ በረከት ለሰባት ዓመታት የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ሲያገለግሉ ከነበሩበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጥቅም 20 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በመንግሥት የፋይናንስ ተቋማት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ስንታየሁ ወልደ ሚካኤል (ዶ/ር) ጥቅምት 2 ቀን 2010 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ ስለመነሳታቸው መዘገባችን ይታወሳል፡፡  እሳቸውን ተክተው የተሾሙት ደግሞ የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽነሩ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) መሆናቸው ይታወቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...