Wednesday, July 24, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በአራት ዓመት ይጠናቀቃል የተባለው ርብ የመስኖ ግድብ ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ ሊመረቅ ነው

ተዛማጅ ፅሁፎች

  • በወቅቱ 1.6 ቢሊዮን ብር በጀት ቢያዝለትም 3.7 ቢሊዮን ብር ፈጅቷል

በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን በአብነትና በፋርጣ ወረዳዎች መካከል በሚገኝ ሰፊ መሬት ላይ ገንብቶ በአራት ዓመት ውስጥ ለማጠናቀቅ በ2000 ዓ.ም. ግንባታው የተጀመረው ርብ የመስኖ ግድብ ፕሮጀክት፣ ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ ጥቅምት 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ሊመረቅ ነው፡፡

ግድቡ 1,000 ሔክታር ስፋትና 234 ሺሕ ሜትር ኩብ ውኃ የሚይዝ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግንባታውን አካሂዷል፡፡ የውኃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ብዙነህ ቶልቻ ለሪፖርተር እንደተናገሩት በዲዛይን ለውጥ፣ በኮንትራክተሩና አማካሪ ድርጅቶች የአቅም ውስንነትና ልምድ ማነስ ምክንያት ፕሮጀክቱ ይጠናቀቃል ተብሎ በታሰበበት ጊዜ ሊጠናቀቅ አልቻለም፡፡ የሚኒስቴሩ አስተዳደራዊ ችግርም ለመዘግየቱ ተጠቃሽ መሆኑንም አክለዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ፎገራ አካባቢ ለሚገኝ ሰፊ መሬት ማልሚያ ከመጥቀሙም በተጨማሪ፣ በሚሄድበት አካባቢ ያሉ አርሶ አደሮችንም ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል፡፡

ግድቡ በአሁኑ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ውኃ መያዙን የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ ጥቅምት 25 ቀን 2010 ዓ.ም. በይፋ ተመርቆ ሥራ ለማስጀመር ቅድመ ሁኔታዎች መጠናቀቃቸውን አስረድተዋል፡፡

ርብ የመስኖ ግድብን ፕሮጀክት በ2000 ዓ.ም. በ1.6 ቢሊዮን ብር ለመገንባት ውል የተፈጸመ ቢሆንም፣ ግድቡ ሲጠናቀቅ 3.7 ቢሊዮን ብር መፍጀቱንም አቶ ብዙነህ ጠቁመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች