Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ልዩነቶቻቸውን በሽምግልና ለመፍታት ጫፍ መድረሳቸው ተጠቆመ

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ልዩነቶቻቸውን በሽምግልና ለመፍታት ጫፍ መድረሳቸው ተጠቆመ

ቀን:

የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ይልቃል ጌትነት (ኢንጂነር) እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ አመራሩን የተረከቡት አቶ የሽዋስ አሰፋ፣ ልዩነቶቻቸውን በሽምግልና ለመፍታት ጫፍ ላይ እንደደረሱ ተጠቆመ፡፡

ምልዓተ ጉባዔ ሳይሟላና የምርጫ ዘመናቸው ሳይጠናቀቅ የምርጫ ሕግንና የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብ በመተላለፍ ጠቅላላ ጉባዔ መደረጉን ተቃውመው፣ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ክስ ያቀረቡት አቶ ይልቃል ሕጉን መሠረት ያደረገ ውሳኔ ሲጠባበቁ የቆዩ ቢሆንም፣ ምልዓተ ጉባዔው ተሟልቶና ሕጉን ባከበረ መንገድ የተካሄደ ጉባዔ መሆኑን በማረጋገጥ፣ ቦርዱ ለአዲሱ አመራር ለእነ አቶ የሺዋስ ዕውቅና መስጠቱ ይታወሳል፡፡

ሁለቱም ወገኖች በየፊናቸው ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ›› የእነሱ እንደሆነ ለዓመት ያህል የየራሳቸውን እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩ ቢሆንም፣ በአቶ የሺዋስ የሚመራው ፓርቲ ሕጋዊ ዕውቅና ተሰጥቶታል፡፡ አቶ የሺዋስ ከመኢአድ ጋር አብረው ለመሥራት ጥምረት ፈጥረው እየሠሩ ይገኛሉ፡፡ አቶ ይልቃልን የሚደግፉ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት፣ ‹‹የፓርቲው መሥራች አባሎች እኛ ነን›› በማለት እየተንቀሳቀሱ ባሉበት ሁኔታ፣ በሁለቱ አመራሮች መካከል ያለውን ልዩነት በሽምግልና እንፈታዋለን ያሉ የአገር ሽማግሌዎች እያደራደሩ ቆይተው፣ ለማስማማት ጫፍ ላይ መድረሳቸውን ሪፖርተር ለማወቅ ችሏል፡፡

የሕግ ጠበቃው አቶ ተማም አባቡልጉ ሰብሳቢ ሆነው ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለ ማርያም፣ የሕግ ጠበቃው አቶ ብርሃነ ሞገስ፣ አቶ ታዲዎስ ታንቱና የአቶ ከተማ ይፍሩ ወንድም አቶ ይልማ ይፍሩ የተባሉ ግለሰቦች ሁለቱን ወገኖች እያደራደሩ መቆየታቸው ታውቋል፡፡

እንደ አቶ ይልቃል ገለጻ፣ የሽምግልናው መሠረት ፓርቲው አካሂዶታል የተባለው ጠቅላላ ጉባዔ ነው፡፡ ፓርቲውንና አመራሮቹን ወደነበሩበት መልሶ በሥርዓትና በሕግ የሚመራ መዋቅር መፍጠር አስፈላጊ እንደሆነ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲን ችግር እንደሚፈቱ ተስፋ ያደረጉት ሽማግሌዎቹ ፓርቲው ከዕውቀት ማነስ፣ ከሥልጣን ጥመኝነት፣ ከኢሕአዴግ ጣልቃ ገብነትና ከሌሎችም ጋር የተያያዙ ችግሮች እንዳሉበት በመግለጽ ሥራ መጀመራቸው ተጠቁሟል፡፡

በእነሱ በኩል ሽምግልናውን እንደሚቀበሉና የመፍትሔ ሐሳቦችንም በጽሑፍ መስጠታቸውን የገለጹት አቶ ይልቃል፣ ከእነ አቶ የሺዋስ በኩልም ሽምግልናውን የመቀበል ፍላጎት ቢኖራቸውም የመፍትሔ ሐሳቡን ዘግይተው መስጠታቸውን አስረድተዋል፡፡

የሽማግሌዎቹ ዓላማ እከሌ ከእከሌ የተሻለ ነው የሚል ውሳኔ ለመስጠት ሳይሆን ሕዝባዊ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ የሆነ የፓርቲ አመራር እንዲፈጠር ለማድረግ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

‹‹እኛ ሙሉ ነን፡፡ አባሉ በሙሉ ከእኛ ጋር ነው፡፡ ከእነሱ (ከነአቶ የሺዋስ) ጋር ያለው አባልም ቢሆንም አመራር መሆን አትችልም ሊባል ይችላል እንጂ አባል መሆን አትችልም ሊባል አይችልም፤›› ያሉት አቶ ይልቃል፣ ሌላ ፓርቲ መመሥረት ቢፈልጉ ሙሉ መዋቅር እንዳለና እንደሚችሉም ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን የፓርቲ አባላት በተጋጩ ቁጥር አዲስ ፓርቲ መመሥረት የኢትዮጵያን ሕዝብ ስለሰለቸው፣ ባለው ተስማምተን ማስቀጠሉን እንደ አማራጭ ለመውሰድ በመፈለግ ሽምግልናውን መቀበላቸውን አስረድተዋል፡፡

ሪፖርተር የአቶ የሺዋስንና የሽምግልና ቡድኑ አባላትን ለማነጋገር የተደረገው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም፡፡ የሽምግልና ቡድኑ ሰብሳቢ አቶ ተማም በጉዳዩ ላይ በቅርቡ መግለጫ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...