Thursday, March 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊግንባታ እያደናቀፉ ነው በተባሉ የፍርድ ቤት ዕግዶች ላይ መፍትሔ እንዲቀርብ ታዘዘ

ግንባታ እያደናቀፉ ነው በተባሉ የፍርድ ቤት ዕግዶች ላይ መፍትሔ እንዲቀርብ ታዘዘ

ቀን:

ግንባታ እያደናቀፉ ነው በተባሉ የፍርድ ቤት ዕግድ ትዕዛዞች ላይ ውሳኔ ለመስጠት፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ በጋራ እንዲሠሩና የመፍትሔ ሐሳብ እንዲያቀርቡ ኃላፊነት ተሰጣቸው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መካከለኛውን የከተማው ክፍል በመልሶ ማልማት ፕሮጀክት በድጋሚ ለማልማት የሚነድፈው ዕቅድ፣ በተለይ በፍርድ ቤቶች የዕግድ ትዕዛዝ ምክንያት ወደ ሥራ መግባት አለመቻሉን በተደጋጋሚ በመግለጽ ላይ ነው፡፡

መንግሥት ይህንን ችግር በማጤን የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ የመፍትሔ ሐሳብ እንዲያቀርቡ ወስኗል፡፡ በዚህ መሠረት ሁለቱ ተቋማት ኮሚቴ አዋቅረው በጉዳዩ ላይ እየሠሩ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ለልማት የተመረጡ ቦታዎችን ነፃ አድርጎ ለመሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽሕፈት ቤት የማስረከብ ኃላፊነት የተጣለበት የመልሶ ማልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሚሊዮን ግርማ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ፍርድ ቤቶች የሄደላቸውን የመሬት ጉዳይ በሙሉ እየተመለከቱ ነው፡፡ ‹‹የፍትሕ አካላት የመሬት ጉዳዮች ማለፍ ያለባቸውን ሒደት በሙሉ አሟጠው መጠቀማቸውን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡ ይህ ሳይሆን በመቅረቱ በአስተዳደሩ የልማት ዕቅድ ላይ ጫና ፈጥሯል፤›› ሲሉ አቶ ሚሊዮን ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ 186 ሔክታር መሬት ለመልሶ ማልማት ፕሮግራም ቢወስንም፣ በፍርድ ቤቶች ዕግድና ለተነሺዎች በቂ ካሳና ምትክ ማቅረብ ባለመቻሉ ምክንያት ታጥረው ለዓመታት ዘልቀዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ 360 ሔክታር መሬት ለመልሶ ማልማት ፕሮግራም ነፃ አድርጎ ግንባታ ለማስጀመር ታቅዷል፡፡

በተለይ የፍርድ ቤት ዕግዶች ለእነዚህ ፕሮግራሞች ዋነኛ እንቅፋት መሆኑ ተገልጿል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ለዓለም ተሠራ በቅርቡ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ የፍርድ ቤት ዕግድ ለመልሶ ማልማት ሥራዎች እንቅፋት እየሆነ በመምጣቱ የፌዴራል መንግሥት መፍትሔ እንዲሰጥ ተጠይቋል፡፡

እንደ አቶ ለዓለም ሁሉ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ በቅርቡ በተካሄደ ስብሰባ ላይ፣ የፍርድ ቤቶች ዕግድ በመንገዶች ግንባታ ላይ እየፈጠረ ያለው ተፅዕኖ በቀላሉ የሚታይ አይደለም ብለዋል፡፡

የፍርድ ቤቶች ዕግድ በከተማው ልማት ላይ እያደረሰ ያለውን ተፅዕኖ በመገንዘብ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና የከተማው ፍትሕ ቢሮ መፍትሔ እንዲያቀርቡ አዟል፡፡

ከዚህ ጋር ችግር ሆኖ የቆየው ባሉት ሕግጋት መስተናገድ ያልቻሉ ተነሺዎች የሚስተናገዱበትን አዲስ መመርያ፣ የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ከሁለት ወራት በፊት ማውጣቱ ይታወሳል፡፡

የመልሶ ማልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ የወጣውን መመርያ ክፍላተ ከተሞች ተግባራዊ እንዲያደርጉ ከሁለት ሳምንት በፊት አሠራጭቷል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...