Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትኢትዮጵያን በዓለም ቴኳንዶ ሻምፒዮና ለሚወክሉ ስፖርተኞች በውጭ ባለሙያዎች ሥልጠና ተሰጠ

ኢትዮጵያን በዓለም ቴኳንዶ ሻምፒዮና ለሚወክሉ ስፖርተኞች በውጭ ባለሙያዎች ሥልጠና ተሰጠ

ቀን:

ኢትዮጵያን በተለያዩ ዓለም አቀፍ የቴኳንዶ ሻምፒዮናዎች ላይ ለሚወክሉ ተወዳደሪዎች የሦስት ቀናት ሥልጠና ተሰጠ፡፡

የሠልጣኞች የቴክኒክ ችሎታን ማሻሻል ላይ ትኩረቱን ያደረገው ሥልጠና በጥር  2010 ዓ.ም. በአርጀንቲና ለሚከናወነው የዓለም ቴኳንዶ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፉትን ያማከለ መሆኑን የኢትዮጵያና የአፍሪካ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ማስተር ኪሮስ ገብረመስቀል ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ሐምሌ 20 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ለሦስት ቀናት በተከናወነው ሥልጠና ዳኞች፣ አሠልጣኞችና ተወዳዳሪዎች ተሳትፈውበታል፡፡ ከእንግሊዝ በመጡና በአገር ውስጥ ባለሙያዎች በተሰጠው ሥልጠና ከድሬዳዋ በስተቀር ሁሉም ክልሎችና ከአዲስ አበባ የመጡ ተሳትፈውበታል፡፡

- Advertisement -

ክልል ላይ ያለው የሠልጣኝ ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የሚናገሩት ማስተር ኪሮስ፣ ‹‹ቀደም ብሎ ጎልቶ የሚወጡት ጥቂት ክለቦች ነበሩ፤ አሁን ግን አብዛኛው ክልል ተፎካካሪ የሆኑ ተወዳዳሪዎችን እያፈራ መጥቷል፤›› ብለዋል፡፡

በአርጀንቲና አዘጋጅነት የሚከናወነው የዓለም የቴኳንዶ ሻምፒዮና ላይ ለመሳተፍ ኢትዮጵያን የሚወክሉ ተወዳዳሪዎችን ለመምረጥ በነሐሴ መጨረሻ የክልሎች ሻምፒዮና በአዲስ አበባ እንደሚከናወንም ተጠቅሷል፡፡

በአሶሴሽን ደረጃ ተዋቅሮ እንቅስቃሴ ከጀመረ 11 ዓመታትን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን፣ ሦስት ኢንተርናሽናል ውድድሮች ላይ መሳተፍ ሲችል በኢትዮጵያ ደግሞ አንድ የአፍሪካ ሻምፒዮና ማዘጋጀት ችሏል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...