Saturday, March 25, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበደቡብ ሱዳን ባገረሸው ጦርነት ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ቀጥለዋል

በደቡብ ሱዳን ባገረሸው ጦርነት ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ቀጥለዋል

ቀን:

በደቡብ ሱዳን መንግሥትና በአማፅያኑ ጦር መካከል ዳግም ባገረሸው ጦርነት፣ በርካታ ሲቪል ደቡብ ሱዳናውያን ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ መሆኑ ታወቀ፡፡

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በደቡብ ሱዳን እየተካሄደ ባለው ጦርነት ንፁኃን ዜጎች ድንበር አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው፡፡ ነገር ግን ሚኒስትሩ ጨምረው እንደገለጹት፣ የታጠቁ ኃይሎች ወደ ኢትዮጵያ (ጋምቤላ) እየገቡ ነው የሚለው መረጃ ትክክል አይደለም፡፡

ሰሞኑን በደቡብ ሱዳን መንግሥትና በአማፂው ኃይል መካከል እንደ አዲስ ውጊያ መከፈቱ ይታወሳል፡፡ ሁለቱም ኃይሎች ጦርነቱን ድል እያደረጉ መሆኑን እየገለጹ ሲሆን፣ አማፂው ኃይል ፓጋክ የተሰኘውን ከተማ መቆጣጠሩን አስታውቋል፡፡  የደቡብ ሱዳን መንግሥት ግን ይኼ መረጃ  ትክክል እንዳልሆነ ገልጿል፡፡

በዚህ መካከል ሕይወታቸው አደጋ ውስጥ የገባ የደቡብ ሱዳን ሲቪል ዜጎች አካባቢያቸውን እየለቀቁ ወደ ጋምቤላ እየተሰደዱ መሆኑ ታውቋል፡፡ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የስደተኞችና የስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳዳር የኮሙዩኒኬሽንና ኢንፎርሜሽን ቡድን መሪ አቶ ሱሌይማን አሊ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ከደቡብ ሱዳን በርካታ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው፡፡

አቶ ሱሌይማን እንደገለጹት፣ እስካሁን ከ380 ሺሕ በላይ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ኢትዮጵያ ገብተዋል፡፡ አሁንም በመግባት ላይ ናቸው፡፡ የሚገቡት ስደተኞች በጋምቤላና በኦሮሚያ ድንበር ላይ በሚገኙ ሰባት የስደተኞች ካምፕ ውስጥ እየተስተናገዱ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

‹‹አብዛኛዎቹ ስደተኞች ሕፃናትና ሴቶች ናቸው፡፡ ተዋጊ ኃይል ወደ ካምፖቹ እንዳይገባ የመለየት ሥራ ይካሄዳል፤›› ሲሉ አቶ ሱሌይማን አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኩባንያ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ባንኮች ውጤታማነት

የጠቅላላ ጉባኤ፣ የጥቆማና ምርጫ ኮሚቴ፣ የተቆጣጣሪ ቦርድ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...