Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊተራድዖ፣ ልማትና ሰላምን የሚያስተሳስረው ፍኖተ ካርታ

ተራድዖ፣ ልማትና ሰላምን የሚያስተሳስረው ፍኖተ ካርታ

ቀን:

የሥርዓተ ምግብ ውጤትን ለማሻሻል በአዲስ መንገድ በጋራ መሥራት የሚል ትልም ያለው ተራድዖ፣ ልማትና ሰላምን አስተሳስሮ የሚተገብር መመሪያና የአፈጻጸም ፍኖተ ካርታ መዘጋጀቱ ተገለጸ፡፡

ፍኖተ ካርታው የተራድዖ፣ ልማትና ሰላም ዘርፎች የሕዝብን ፍላጎት በብቃት ለማሟላት፣ ሥጋቶችና ተጋላጭነቶችን ለመቅረፍ ብሎም ወደ ፊት ለመሄድ በጋራ ለመሥራት የሚያመላከት ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ፍኖተ ካርታው ይፋ ሲደረግ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሮ ፍሬሕይወት አበበ ተራድዖ፣ ልማትን እና ሰላምን አስተሳስሮ በመተግበር ሥርዓተ ምግብን ለማሻሻል እንዲቻል ከወትሮው የተለየ አቀራረብ ይጠይቃል ብለዋል፡፡

የትገበራ መመሪያውና የአፈጻጸም ፍኖተ ካርታው በፕሮግራሙ የሚሳተፉ ባለድርሻ አካላት ለፕሮግራሙ ተፈጻሚነት የሚደረጉትን ጥረቶች በማስተባበር ለፍሬ ለማብቃት ታስቦ መዘጋጀቱንም አስረድተዋል፡፡

በሰው ሠራሽና በተፈጥሮ አደጋዎች ጉዳት ላይ የሚገኙ ማኅበረሰቦችን ተደራሽ ለማድረግ የተቀናጀ ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል፡፡

 የተዘጋጁት ሁለቱ ሰነዶች ለፕሮግራሙ የኢንቨስትመንት አቅጣጫ፣ የትብብር መዋቅር፣ ስልታዊ ትግበራና የአፈጻጸም ምዕራፎችን በግልጽ ያስቀመጡ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

ይህ መመርያና ፍኖተ ካርታ የምግብ ዕርዳታ ሰጥቶ መውጣት ብቻ ሳይሆን ኅብረተሰቡ ከተረጂነት አስተሳሰብ ወጥቶ ዘላቂነትንም ለማረጋገጥ የሚያስችለው ነው ብለዋል፡፡

አንዳንድ ጊዜ የፀጥታ ችግር ባለበት አካባቢ የሚፈጸሙ ድጋፎች በተቀናጀ አግባብ እንደማይከናወኑ፣ ይህ ዓይነቱም ሁኔታ ድጋፎች ከብክነትና ለአላስፈላጊ ዓላማ ሊውሉ እንደሚችሉ ነው የተናገሩት፡፡

አዲሱ አሠራር ከዚህ በፊት በተበተነ መልኩ ሲተገበሩ የነበሩትን የሰብዓዊ ዕርዳታ፣ የልማትና የሰላም ተግባር በተቀናጀ መልኩ ለማከናወን የሚያግዝ መሆኑንም ተመልክቷል፡፡

የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም በበኩላቸው፣  ፕሮግራሙ ሁሉንም ባለድርሻ አካላትን ለማስተባበር የሚያስችል መልካም አቅጣጫ መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህንኑ በማኅበረሰብ ደረጃ ለማስፈጸም በትብብር እየተሠራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ መሥሪያ ቤታቸው ከጤና እና ከግብርና ሚኒስቴሮች ጋር በመተባበር የሥርዓተ ምግብ ችግሮችን የአገር ውስጥ የግብርና ምርትን በመጠቀም ለመፍታት እየሠራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

መመርያውና ፍኖተ ካርታው በአረንጓዴ አሻራ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በኩታ ገጠም የግብርና ልማትና የሥራ ዕድል ፈጠራ የታየውን ስኬት ለማስቀጠል አጋዥ እንደሚሆንም ጠቅሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ የሥርዓተ ምግብ ማሳደግ ንቅናቄን ዋና የልማትና ዕድገት አጀንዳ በማድረግ እስከ 2022 ዓ.ም. የሥርዓተ ምግብ ችግሮችን ለመግታት እየሠራች መሆኗን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የተፈጥሮ አደጋዎች ለሥርዓተ ምግብ ችግሮች ዋነኛ መንስኤ መሆናቸውን ያስረዱት ደግሞ የሕፃናት አድን ድርጅት ካንትሪ ዳይሬክተር ድራጋና ስትሪኒክ ናቸው፡፡ ተቋማቸው ከሥርዓተ ምግብ ፖሊሲዎች ጋር በተያያዘ በክልልና በፌደራል ደረጃ እየደገፈ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ሕፃናትን ሥርዓተ ምግብ ለማረጋገጥ የተባበሩት መንግሥታት ሕፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) እየሠራ እንደሚገኝም የዩኒሴፍ ተወካይ ስታንሊ ቺትዌካ በመድረኩ አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...